Goshu Endalamaw Wondimagegn

Goshu Endalamaw Wondimagegn Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Goshu Endalamaw Wondimagegn, Government Official, Bahir Dar.
(1)

10/08/2026
06/08/2026
06/08/2026
የከተማችንን ውበት ይበልጥ የገለጡ የኮሪደር ልማቶች፣ የዘመናዊ መሰረተ-ልማት ግንባታዎች እና የጽዳትና አረንጓዴ ልማት ስራዎቻችን ከተማችንን በየዕለቱ የበለጠ እያደመቋት ይገኛሉ። ይህ የሁላች...
05/08/2026

የከተማችንን ውበት ይበልጥ የገለጡ የኮሪደር ልማቶች፣ የዘመናዊ መሰረተ-ልማት ግንባታዎች እና የጽዳትና አረንጓዴ ልማት ስራዎቻችን ከተማችንን በየዕለቱ የበለጠ እያደመቋት ይገኛሉ። ይህ የሁላችንም የወል ስኬት፣ የነገዋን ባሕርዳር በጠንካራ መሰረት ላይ የመገንባት ጥረታችን ማሳያ ነው።

​ከተማችንን በሁሉም መስክ ስማርት የማድረግ ጉዞ አጠናክረን በመቀጠል፣ ባሕርዳርን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ፣ ለጎብኚዎች ደግሞ የማይረሳ ትዝታ የምታሳድር ውብ መዳረሻ ማድረጋችንን እንቀጥላለን።

የተዋበች ባሕርዳር
Smart City, Bright Future!

03/08/2026

እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመትመም ዛሬም አዲስ የአረንጓዴ ልማት ተአምር ሠርተናል።

በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር 805.3 ሚልዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ተአምር ሠርተናል። ባለፉት የአረንጓዴ ዐሻራ ዓመታት ዛሬን አስበን ምግብ አምርተናል፤ ለነገ ኃላፊነት ደግሞ ደን አልምተናል።

እንደ ሕዝብ የተጋነው ፍሬ አፍርቷል። ተራሮች አረንጓዴ ካባ ደርበዋል፣ ዉኆች እንደገና መንጭተዋል፡፡ የተራቆተወ ለብሶ፣ የጠፋው ተመልሶ፤ የደፈረሰው ጠርቶ፣ የነጠፈው አፍርቶ፤ የሀገር መልክ ተቀይሯል፡፡ ይሄንን ያየው ዓለምም ለትጋታችን ደጋግሞ ዕውቅና ሰጥቶናል።

በራዕይ ማቀድን፣ በትጋት ወዳሰቡት መራመድን፣ ጽፈው ብቻ ሳይሆን ከተናገሩት በላይ ኖረው፣ ቃላቸውን በአርአያነት ተግብረው ያሳዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአረንጓዴ ዐሻራ ለመጣው ስኬት ምስጋና ይገባቸዋል።

መሪ እና ሕዝብ ለአንድ ዓላማ ተሰለፉ፡፡ አፈር ነክተው፣ ጭቃ ረግጠው ተስፋን ተከሉ፡፡ እነርሱ ዝቅ ብለው ሀገርን ከፍ አደረጉ፡፡ ኢትዮጵያውያን የመሪያችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ፣ ከሠርቅ እስከ ሰርክ ተምማችሁ፡፡ የአየር ሁኔታውን አሸንፋችሁ፣ ዕቅዳችሁን አሳካችሁ፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
ዛፍ የሚተከለው ለትውልድ ነው፡፡ ስለዚህ ከጥላው ያረፉ፤ ከድርቅ የተረፉ፤ ከፍሬው የቀመሱ፤ ከልምላሜው የተቋደሱ ሁሉ ያመሰግኗችኋል፡፡

የዘንድሮውን የአንድ ጀንበር ሕልማችንን አሳክተናል፡፡ ለቀሪውም እንበርታ!
በሁለመናዋ የበለጸገች አረንጓዴ ኢትዮጵያን እንገንባ!

03/08/2026
የመንግሥትን ራዕይ ከሕዝባችን አቅምና ቁርጠኝነት ጋር አዋህደን፣ ባልተቆጠበ የተባበረ ክንድ የሰራነው ስራ ፍሬ እያፈራ ይገኛል።​ጉዞአችን እዚህ ላይ አያበቃም!​ነገም ቢሆን ለከተማችን ሁለንተ...
24/07/2026

የመንግሥትን ራዕይ ከሕዝባችን አቅምና ቁርጠኝነት ጋር አዋህደን፣ ባልተቆጠበ የተባበረ ክንድ የሰራነው ስራ ፍሬ እያፈራ ይገኛል።

​ጉዞአችን እዚህ ላይ አያበቃም!
​ነገም ቢሆን ለከተማችን ሁለንተናዊ እድገትና ሙሉ ስኬት አቅማችንን፣ እውቀታችንን እና ጉልበታችንን ሳንሰስት እንሰጣለን። የትጋታችን አሻራ በየቀኑ አዲስ ምዕራፍ ይጽፋል።

​ በአንድነት – ለላቀ ለውጥ፣ ለተሻለች ከተማ!
የተዋበች ባሕርዳር!
Smart City, Bright Future!

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goshu Endalamaw Wondimagegn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share