Amhara Region Mines Bureau/የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ

Amhara Region Mines Bureau/የአማራ ክልል ማዕድን  ቢሮ Welcome to the Amhara Region Mines Bureau!
(1)

Discover regional mineral potential, news, and investment updates.

እንኳን ወደ አማራ ክልል ማዕድን ቢሮ ገጽ በደህና መጡ! የክልሉን የማዕድን ሀብት፣ ልማትና ወቅታዊ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ።

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!የመውሊድ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የመልካም ተግባር መልእክትን የምናድስበት ይሁን።     የአማራ ክልል ማ...
24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ!

የመውሊድ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የመልካም ተግባር መልእክትን የምናድስበት ይሁን።

የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ
~~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

  ÷ የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ስልጠና በባህር ዳር ተጀመረ---------------------------ባህር ዳር (ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.) — የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕድን ቢ...
24/08/2026

÷ የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ስልጠና በባህር ዳር ተጀመረ
---------------------------
ባህር ዳር (ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.) — የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማዕድን ቢሮ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለቢሮው ባለሞያዎች ያዘጋጀው የሥነ-ምድር ካርታ ሥራ፣ የማዕድን ፍለጋና የጂኦሳይንስ ናሙና አወሳሰድ የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠና ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በይፋ መካሄድ ጀምሯል።

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ታምራት ደምሴ (የምክትል ቢሮ ኃላፊ) እንደተናገሩት "ቢሯችን የባለሙያዎችን የሙያ ብቃት፣ የቴክኒክ ክህሎት እና የአፈጻጸም አቅም ለማሳደግ ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በስፋት ሲያከናውን ቆይቷል። በሥነ-ምድር ካርታ ሥራ እና በማዕድን ፍለጋ ጥናት ዘርፍ በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለን የሙያ ትብብርና ቅንጅት የሚታይና የሚጨበጥ ውጤት እያስገኘ ይገኛል። ይህ ስልጠና ባለሙያዎቻችን በዘመናዊ የጂኦሳይንስ ናሙና አወሳሰድ፣ በካርታ ዝግጅትና መዋቅራዊ ትንተና ላይ ያላቸውን እውቀት በማጎልበት በክልላችን የሚገኘውን የከርሰ-ምድር ፀጋ በሳይንሳዊ መንገድ ለመመርመርና ለማልማት የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያፋጥነዋል።" ያሉ ኢሆን ወ/ሮ አበባ ጌታሁን (የምክትል ቢሮ ኃላፊ )በበኩላቸው "በክልላችን የማዕድን ኢንቨስትመንት መስክ የሚፈለገውን ፈጣንና ዘላቂ እድገት ለማስመዝገብ አስተማማኝና ጥራት ያለው የጂኦሳይንስ መረጃ (Geoscientific Data) ማዘጋጀት ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታ ነው። የጅኦሎጅ ባለሙያዎቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ የካርታ ሥራ እና የኢንቨስትመንት ጥናት ቴክኒኮች ሲበቁ፣ ጥራት ያለው መረጃ ለባለሀብቶች በማቅረብ የማዕድን ኢንቨስትመንትን ማቀላጠፍና የሀብት ልማቱን ውጤታማ ማድረግ ይቻላል። ስለሆነም ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ለክልሉ ማዕድን ኢንቨስትመንት ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል”

ስልጠናው የክልሉን የማዕድን ሀብት በሳይንሳዊና በሙያዊ መሠረት ለመለየት፣ ለማጥናትና ለልማት በተገቢው መልኩ ለማዋል የሚያስፈልጉ የጂኦሎጂ ዕውቀትና የመስክ ሥራ ክህሎቶችን ለማጎልበት ያለመ ነው።
በስልጠናው የሚሸፈኑ ዋና ዋና ርዕሶች፡
History and geological settings of the Amhara Region in relation to Ethiopia and African geology (የአማራ ክልል ሥነ-ምድር ታሪክና አቀማመጥ ከኢትዮጵያና ከአፍሪካ ሥነ-ምድር አንጻር)

Construction of geological cross sections from geological maps (ከሥነ-ምድር ካርታዎች የሥነ-ምድር ጥልቅ ገጽታዎችን/Cross Sections ማዘጋጀት)

Structural Characterization and Standardized Geoscientific Sampling (መዋቅራዊ ሁኔታዎችን መለየት፣ የጂኦሳይንስ መደበኛ ናሙና አወሳሰድና የመስክ ልኬት ዘዴዎች)

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ ያለውን ሰፊ ልምድና ከፍተኛ የሰው ኃይል አቅም መሠረት በማድረግ የተመደቡ መምህራን ስልጠናውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ስልጠናው ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በስልጠናው ወቅት ባለሙያዎች የንድፈ ሐሳብ ዕውቀትን ከተግባራዊ የመስክ ልምምድ ጋር በማጣመር የሙያ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ትኩረት ይሰጣል።

~~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

24/08/2026

የተነቃቃው የማዕድን ዘርፍ

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ--------------------------የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
--------------------------
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል።

ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል።

በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል።

በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል።

ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል።
በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል።

የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል።

በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።

በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል።

የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
@ኢዜአ
~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

22/08/2026
19/08/2026
18/08/2026
ዕምቅ የማዕድን ፀጋን በሳይንሳዊ መንገድ ለህዝብ ብልፅግና!---------------------------በአማራ ክልል የሚገኘውን ከፍተኛ የማዕድን ሀብት በዘመናዊና ሳይንሳዊ ዘዴዎች በማልማት ለ...
18/08/2026

ዕምቅ የማዕድን ፀጋን በሳይንሳዊ መንገድ ለህዝብ ብልፅግና!
---------------------------
በአማራ ክልል የሚገኘውን ከፍተኛ የማዕድን ሀብት በዘመናዊና ሳይንሳዊ ዘዴዎች በማልማት ለሀገርና ለወገን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማዋል ተጀምሯል።

የማዕድን ልማት በዘመናዊና ሳይንሳዊ ሂደት ሲመራ የአካባቢ ጥበቃን ያረጋገጠ፣ ውጤታማ እና ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ይሆናል።

ሳይንሳዊ የማዕድን ልማት 5 ዋና ዋና ደረጃዎች

ጂኦሎጂካል ዳሰሳ እና ካርታ ስራ (Geological Mapping): የማዕድናትን ዓይነት፣ ስርጭትና የሥነ-ምድር/የጂኦሎጂ መዋቅር በመሬት ላይ በጥናት የመለየት ተግባር።

ጂኦፊዚካል እና ጂኦኬሚካል ፍለጋ (Geophysical & Geochemical Exploration): የላቀ ቴክኖሎጂ እና የላብራቶሪ ትንተና በመጠቀም የማዕድኑን ጥራትና መጠን (Reserve Estimation) በግልፅ የማወቅ ሂደት።

አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ (ESIA): አካባቢን ሳያበላሹና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘላቂ ስራ መኖሩን ማረጋገጥ።

ዘመናዊ የማውጣት እና የመለየት ቴክኖሎጂ (Extraction & Processing): ለብረት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለከሰልና ለከበሩ ማዕድናት የሚመጥኑ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን መጠቀም።

የተቆፈሩ መሬቶች መልሶ ማቋቋም (Mine Reclamation): ማዕድን ከወጣ በኋላ መሬቱን ለአካባቢ ጥበቃና ለሌሎች ልማቶች ዝግጁ ማድረግ።

የሳይንሳዊ አቀራረብ ውጤት በአማራ ክልል

በክልላችን የማዕድን ቢሮ ከአካዳሚክ ተቋማትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በሳይንሳዊ አሰራሮች በተደገፈ ጥናት በርካታ የወርቅ፣ የከሰል፣ የከበሩ ድንጋዮች፣ የብረትና የኢንዱስትሪ ማዕድናት ክምችት ተለይተዋል፡-

የውጭ ምንዛሬ እና የገቢ እድገት፡ በጥናት የተደገፈ ቁፋሮና ኤክስፖርት ለሀገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ይገኛል።

የስራ እድል ፈጠራ፡ ለብዙ ወጣቶች ዘላቂና ህጋዊ የስራ እድል ፈጥሯል።

አካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂነት፡ ህገ-ወጥ አሰራርን በማስቀረት የአፈርና የውሃ ሀብትን የጠበቀ ልማት እየተከናወነ ነው።

መልእክታችን: ሳይንሳዊ አሰራርን በመከተል ሀብታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ ህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮን በመከላከል የክልላችንን ብልፅግና እናፋጥን!

በ ዝናው አበበ(Applied Geologist) በአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ኃላፊ

📌 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ

#የማዕድንልማት #አማራክልል #ሳይንሳዊምርመራ #ዘላቂልማት #ኢትዮጵያ
~~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

በማዕድን ፍለጋና ልማት ሂደት ውስጥ የሥነ-ምድር (ጂኦሎጂ) ካርታ ሥራ ጥናት የመሠረት ድንጋይ ነው። --------------------------የንድፈ-ሐሳብ እውቀትን ከመሬት ተጨባጭ ሁኔታ ጋ...
17/08/2026

በማዕድን ፍለጋና ልማት ሂደት ውስጥ የሥነ-ምድር (ጂኦሎጂ) ካርታ ሥራ ጥናት የመሠረት ድንጋይ ነው።
--------------------------
የንድፈ-ሐሳብ እውቀትን ከመሬት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማያያዝ የማዕድን ሀብቶችን ጥቆማ፣ ስርጭትና ክምችት በጥራት ለመለየት የሚያስችል ቀዳሚና ወሳኝ የጅኦሳይንስ መሣሪያ ነው።
ከዚህ በታች የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ ጥናት ደረጃዎችን፣ ጥቅም ላይ የሚውሉ ስልቶችን እና ለአንድ አካባቢም ሆነ አጠቃላይ ለሀገር የሚኖረውን ዘለቄታዊ ፋይዳ የሚዳስስ ዘገባ ቀርቧል፦

1. የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ ጥናት ደረጃዎች (Phases of Geological Mapping)
የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ ጥናት በታቀደና ደረጃቸውን በጠበቁ ሂደት የሚያልፍ ሳይንሳዊ መንገድ ነው፦

ሀ) ከሜዳ ውጭ የሚደረግ የቅድመ-ጥናት ደረጃ (Office/Desktop Study Phase): ቀደም ሲል የተሰሩ የጂኦሎጂ፣ የሳተላይት እና የአየር ላይ ፎቶዎችን (Satellite Imagery & Aerial Photographs) መሰብሰብና መተንተን።
የጥናት አካባቢውን መልክዓ-ምድር (Topography) እና አጠቃላይ የጂኦግራፊ ሁኔታ መገምገም።

ለ) የሜዳ ላይ ምልከታና መረጃ ስብስብ (Field Mapping Phase): በአካል ወደ ጥናት ቦታው በመሄድ የድንጋይ/የዓለት ዓይነቶችን (Lithology)፣ አወቃቀራቸውን (Folds, Faults, Joints) እና እድሜያቸውን መለየት። የዓለት ናሙናዎችን (Rock Samples) ለላቦራቶሪ ምርመራ መሰብሰብ።
የጂኦሎጂካል ድንበሮችን በካርታ ላይ ማሳረፍና መመዝገብ።

ሐ) የላቦራቶሪና የመረጃ ትንተና ደረጃ (Laboratory & Data Analysis Phase): የተሰበሰቡት ናሙናዎች ኬሚካላዊ ይዘት (Geochemistry) እና የማዕድን ጥንቅር (Petrography/Mineralogy) በላቦራቶሪ መመርመር።
በሜዳ ላይ የተሰበሰቡትን መረጃዎች ማቀናጀት።

መ) የመጨረሻ ካርታና ሪፖርት ማዘጋጀት (Final Mapping and Reporting): ዲጂታል የጂኦሎጂ ካርታዎችን በጂ.አይ.ኤስ (GIS) ሶፍትዌር ማዘጋጀት። ዝርዝር ትንተና፣ የማዕድን አቅምና የውሳኔ ሃሳቦችን ያካተተ ሳይንሳዊ ሪፖርት ማጠናቀቅ።

2. በጥናቱ ጥቅም ላይ የሚውሉ ስልቶች (Mapping Methodologies & Techniques): የቴክኖሎጂ እድገት የጂኦሎጂ ካርታ ሥራን ፈጣንና ትክክለኛ አድርጎታል። ዋና ዋናዎቹ ስልቶች፦

ባህላዊ የመስክ ላይ ስልት (Traditional Field Mapping): የጂኦሎጂስት ኮምፓስ (Brunton Compass)፣ መዶሻ፣ ሌንስ (Hand Lens) እና ጂፒኤስ (GPS) በመጠቀም በአካል ውጣ ውረዶችን በመጓዝ መረጃ የመሰብሰብ ስልት።

የርቀት ዳሰሳ (Remote Sensing) እና ጂ.አይ.ኤስ (GIS): የሳተላይት ምስሎችን (እንደ Landsat, Sentinel, ASTER) በመተንተን የአለት ዓይነቶችንና የማዕድን መኖር ጠቋሚ ምልክቶችን (Hydrothermal Alteration Zones) ከርቀት መለየት።

የጂኦፊዚክስና ጂኦኬሚስትሪ ቅንጅት (Geophysical and Geochemical Mapping): ከመሬት ስር ያሉ ቀጣይነት ያላቸውን የድንጋይ አካላትና የማዕድን ስርጭት ለመለየት የአየር ላይ ወይም ከመሬት በላይ የሚደረጉ የጂኦፊዚክስ (ማግኔቲክ፣ ግራቪቲ) እና የጂኦኬሚስትሪ ጥናቶችን ማቀናጀት።

3. የሥነ-ምስር ካርታ ጥናት ፋይዳ (Significance & Benefits)
የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ ጥናት ለአንድ አካባቢም ሆነ ለአጠቃላይ ሀገር የሚሰጠው ጥቅም ዘርፈ-ብዙ ነው፦

ሀ) ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚኖረው ፋይዳ:-

አካባቢያዊ የማዕድን አቅምን መለየት: በአካባቢው የሚገኙ የካኦሊን፣ እብነ-በረድ፣ አሸዋ፣ የጌጣጌጥ ድንጋዮችና ሌሎች የግንባታና የኢንዱስትሪ ማዕድናትን ትክክለኛ ቦታ ያሳያል።

የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ: ማዕድናት ሲለዩ ባለሀብቶችና የባህላዊ አምራቾች በስፋት ስለሚሰማሩ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

የከርሰ-ምድር ውሃ አንፃር: የጂኦሎጂ ካርታዎች ውሃ ያዘሉ አለቶችን (Aquifers) ቦታ ስለሚጠቁሙ ለአካባቢው የመጠጥና የመስኖ ውሃ ለማውጣት መሠረት ይሆናሉ።

የተፈጥሮ አደጋ ስጋትን መቀነስ: ከመሬት መንሸራተት፣ ከመሬት መሠንጠቅና የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ነፃ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ደህንነቱ የተጠበቀ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲኖር ያግዛል።

ለ) በሀገር ደረጃ የሚኖረው ስትራቴጂካዊ ፋይዳ:-

የኢንቨስትመንት ሳቢነትን ማሳደግ: አለምአቀፍና ሀገር በቀል የማዕድን ኩባንያዎች ኢንቨስት ለማድረግ የመጀመሪያ ፍላጎታቸው አስተማማኝ የጂኦሎጂካል መረጃ ማግኘት ነው። ካርታው የሀገሪቱን የማዕድን ሀብት ካታሎግ አድርጎ ያቀርባል።

የኢኮኖሚ እድገትና የውጭ ምንዛሬ: ወርቅ፣ ሊቲየም፣ ታንታለም፣ የተፈጥሮ ጋዝና የመሳሰሉ ስትራቴጂካዊ ማዕድናት የሚገኙበትን ቀጠና በማሳየት የሀገርን የኤክስፖርት ገቢ ያሳድጋል።

ፖሊሲና ሀገራዊ እቅድ ማውጣት: ሀገር አቀፍ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች (እንደ ግድቦች፣ መንገዶች፣ የባቡር መስመሮች) በጠንካራ የጂኦሎጂ መሠረት ላይ እንዲገነቡ ያደርጋል።

ማጠቃለያ
በአጠቃላይ፣ የሥነ-ምድር (ጂኦሎጂ) ካርታ ሥራ ጥናት የማዕድን ዘርፍ መነሻና ዋና መሪ መሣሪያ ነው። ያለ ትክክለኛና ዘመናዊ የጂኦሎጂ ካርታ ጥናት የማዕድን ሀብትን በአግባቡ ማወቅ፣ መፈለግና ማልማት አይቻልም። በመሆኑም ለአንድ ሀገር የረጅም ጊዜ ዘላቂ ልማት፣ የኢኮኖሚ እድገት እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ምትክ የሌለው ወሳኝ እርምጃ ነው። በዚህም መሠረት ይህን ተግባር የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ልዩ ትኩረት ሠጦ በመስራት ላይ ይገኛል።

በ ዝናው አበበ(Applied Geologist) በአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ኃላፊ

~~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

ከሲሚንቶ ፉብሪካዎች ጋር በሲሚንቶ ምርት እና በግብኣት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡-----------------------የማዕድን ሚኒስቴር ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች ተወካዮች ጋር በ ...
17/08/2026

ከሲሚንቶ ፉብሪካዎች ጋር በሲሚንቶ ምርት እና በግብኣት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡
-----------------------
የማዕድን ሚኒስቴር ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች ተወካዮች ጋር በ በሲሚንቶ ምርት እና በግብዓት አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በዓመት የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ እና ፋብሪካውን በማስፋፋት ምርትን ማሳደግ በሚቻልባቸው ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርትን ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል። የሲሚንቶ ምርትን በማሳደግ ከሐገር ውስጥ ፍላጎት በተጨማሪ ወደ ውጭ መላክ ላይም መታሰብ እንዳለበት ተገልጿል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማንሳት መፍትሔዎች ላይ በቅንጅት መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የሚያጋጥሙ የጋራ ችግሮችን በጋራ ለመፍታትም ከተሻሉት የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ዘርፉ የድንጋይ ከሰልን በሃይል አማራጭ በዋናነት የሚጠቀም በመሆኑ ከድንጋይ ከሰል አምራቾች ጋር ተደጋግፎ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።

ሲሚንቶ የግንባታ ኢንዱስትሪው ዋና ምሰሶ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ትኩረት በመስጠት እየሰራበት እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን አምራቾችም ያጋጠሟቸውን ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አመላክተዋል።

( ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም @ማዕድን ሚኒስቴር)
~~~~~~~~~~~~
ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን!

ሳይንሳዊና ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮችን ይጠቀሙ!
Facebook: https://www.facebook.com/share/186NkWiv6D/
You Tube: https://youtube.com/?si=4YVA3CgcD1ShrOmT
Ticktock: tiktok.com/
Telegram ፡ https://t.me/AnrsMinesResourceDevelopment
Instagram: https://www.instagram.com/anrsmines2014?igsh=MWw0eHFqZ2MwYm8wcA
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBWQHTADTOFR35q0G0
X: https://x.com/AnrsMines

Address

University Road
Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region Mines Bureau/የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Region Mines Bureau/የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ:

Shortcuts

Share