የባሕር ዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • የባሕር ዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት

የባሕር ዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ

“በ2018 በጀት ዓመት ሁለንተናዊ የማስፈጸም አቅምን በማሳደግ የሕዝብን አደራ በላቀ ኃላፊነት የሚወጣ አመራር በማረጋገጥ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል”አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣውበብልፅግና ፓርቲ ...
26/08/2026

“በ2018 በጀት ዓመት ሁለንተናዊ የማስፈጸም አቅምን በማሳደግ የሕዝብን አደራ በላቀ ኃላፊነት የሚወጣ አመራር በማረጋገጥ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል”

አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው
በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

ፈተና ያልበገረው፣ በድል የታጀበ ውጤት !     ~~~~//~~~~የአማራ ክልል ባለፉት ዓመታት የተከሰተው የፀጥታ ችግር ከጎዳቸው ተቋማት አንዱ የትምህርት ዘርፉ ነው። የፀጥታ ችግሩ በተማሪዎ...
23/08/2026

ፈተና ያልበገረው፣ በድል የታጀበ ውጤት !
~~~~//~~~~
የአማራ ክልል ባለፉት ዓመታት የተከሰተው የፀጥታ ችግር ከጎዳቸው ተቋማት አንዱ የትምህርት ዘርፉ ነው። የፀጥታ ችግሩ በተማሪዎች፣ በመምህራን እና በወላጆች ከፍተኛ የስነልቦና ጫና አሳድሯል፤ በዘርፉ ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳትንም አስተናግዷል።

ይሁን እንጂ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤት የአማራ ክልል ከክልሎች መካከል ቀዳሚ በመሆን ፈተና ያልበገረው፣ በድል የታጀበ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ ውጤት የክልሉ ትምህርት በፈተና ውስጥ ሆኖ የተመዘገበ በመሆኑ ለቀጣይ የትምህርት ስራ ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር ነው።

ከተባበርን፣ ከተደጋገፍን እና ትምህርት የትውልድ መቅረጫ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ከተረዳን የማናስመዘግበው ውጤት፣ የማናልፈው ፈተና አይኖርም። የተመዘገበው ውጤትም ክልሉ በትምህርት ፍትሐዊነት እና ጥራት ላይ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ጥረት በተግባር ያረጋገጠ ነው።

"እየተመካከርን ሀገር እንገነባለን፣ ሀገር እየገነባንም እንማከራለን" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ...
22/08/2026

"እየተመካከርን ሀገር እንገነባለን፣ ሀገር እየገነባንም እንማከራለን" ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል። በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በደማቅ ቀለም ኢትዮጵያን ወክላችሁ ተወያይታችሁ እና ተነጋግራችሁ ለዚህ ቀን በመድረሳችሁ ምስጋና ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንድትመክር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። በኢትዮጵያዊ ታጋሽነት ምክክሩ እንዲካሄድ በማድረጋችሁ በእርግጥም የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ምክክር በባሕላችን የቆዬ ቢኾንም የችግሮቻችን መድኅን እንዲኾን የማድረግ ድፍረት እንዳልነበር አንስተዋል።

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የቀረቡ ሃሳቦች ለፖለቲካ ልምምድ እና ለሀገር ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ትልቅ መኾኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ያለውን ስጋት እና ተስፋ በመመካከር ይበጃል ያሉትን ማቅረባቸውን አንስተዋል።

ምክክሩ የሁላችንም የኾነችውን ኢትዮጵያን የሚገልጡ እና የሚያጸኑ የጋራ መሻትን፣ ርእይ እና እጣ ፋንታን በአንድ ላይ ለማራመድ የሚያስችል ዕውቀት የተንሸራሸረበት መኾኑን ገልጸዋል።

ምክክሩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ከተቃርኖ ወጥቶ በይቅርታ እና በስርየት ጎዳና እንዲራመድ መሠረት የጠላ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

ከአምባጓሮ፣ ከነፍጥ እና ከአመጽ አዙሪት የፖለቲካ ልምምድ በመላቀቅ ፖለቲካው በሰላም እና በመደማመጥ እንዲመሠረት በር የከፈተ እንደኾነ ነው ያነሱት።

ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት፣ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው፣ ኢትዮጵያ ልትበተን ነው ያልተባለበት ጊዜ አልነበረም፣ ነገር ግን ይህ ኢትዮጵያን የማይገልጽ እንደኾነ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት። እነዚህ አገላለጾች ለኢትዮጵያ የማይኾን እና ኢትዮጵያ የማታውቃቸው ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚኾነው ቀጥ ያለ፣ ርእቱ እና ብርቱ ነው ብለዋል።

ምክክሩን በትዕግሥት ለተከታተለው የኢትዮጵያ ሕዝብም ምስጋና አቅርበዋል። ሀገር የሚገነባው በፖለቲካ ውል ብቻ አይደለም፤ ሀገር የሚገነባው በማኅበራዊ ትስስር ነው ብለዋል። የቀረቡ ምክረ ሃሳቦች የቀጣይ ፍኖተ ካርታዎች መኾናቸውን አንስተዋል።

ፈተናዎቻንን በራሳችን ጥበብ ለመፍታት ውስጣችንን የፈተሽንበት የታሪክ ባለቤትነታችንን ያረጋገጥነበት ታላቅ አፍሪካዊ ክንውን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ጎዳና መኾኑን ገልጸዋል። "እየተመካከርን ሀገር እንገነባለን፣ ሀገር እየገነባንም እንማከራለን" ነው ያሉት።

22/08/2026

እንኳን ለሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በክልላችን ከነሐሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ በዋግኽምራ፣ በሰሜን ውሎና አካባቢው በድምቀት የሚከበሩት ሻደይ፣ አሸንድየና ሶለል ረጅም ዘመናትን የተሻገሩ የሕዝባችን መገለጫ በዓላት ናቸው፡፡

የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በልጃገረዶችና በወጣቶች ባሕላዊ ጨዋታ ደምቀው በአደባባይ ይከበራሉ።

ልዳገረድችና ወጣቶች በክረምቱ የለመለሙ ዕፅዋትን በመጠቀም ባሕልና እሴታቸውን የሚገልጹበት እንዲሁም ወደ ብርሃኑ የመስከረም ወር እና አዲስ ዓመት ለመሸጋገር የተስፋና የደስታ ማብሰሪያቸው ነው፡፡

ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን የሚስቡ የሕዝባችን ማህበራዊ ቁርኝትና አብሮነት የሚያጠናክሩ የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶቻችን ናቸው።

በዓላቱን ስናከብር ሕዝባችን ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን ባህላዊ እሴቶች በማክበርና በማሳደግ፣ ለተከታዩ ትውልድ ትውፊታዊ ይዘታቸውን ጠብቀን ለማስተላለፍ በጋራ በመሥራት ሊሆን ይገባል፡፡

መልካም የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል!

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሶለል፣ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ቡሄ እና የእንግጫ ነቀላ በዓላትን በተለያዩ ደማቅ ባህላዊ ዝግጅቶች አከበረ።
18/08/2026

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሶለል፣ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ቡሄ እና የእንግጫ ነቀላ በዓላትን በተለያዩ ደማቅ ባህላዊ ዝግጅቶች አከበረ።

የአማራ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸለመ።የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመታት  አፈፃፀም ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።...
17/08/2026

የአማራ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸለመ።

የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመታት አፈፃፀም ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።

በበጀት አመቱ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ በአመቱ በፈርጅ አንድ አጠቃላይ ምዘና ከሁሉም ክልሎች የአማራ ክልል የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን በጣም ከፍተኛ (95.86) ውጤት በማምጣትና 1ኛ ደረጃ በመውጣት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) በጋራ መድረኩ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት የፓርቲውን የፖለቲካና የስነ ምግባር ጤንነት በመጠበቅ ብዙ ውጤቶች መገኘቱን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ ከማዕከል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የፓርቲው መመሪያዎችና አሠራሮች እንዲሁም የሀገራችን የምርጫ ሕጎች እንዲከበሩ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል፡፡

የኢንስፔክሽን ግኝቶችን ለፓርቲው በማቅረብ የሚታዩ ግድፈቶችን እንዲያርም በማድረግ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ የቀረቡ አቤቱታዎችን በማጣራትና ምላሽ በመስጠት የአባላት መብት እንዲከበር መድረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ደስታ ገለጻ የኮሚሽኑን አቅም በመገንባት በርካታ ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም ከተልዕኳችን አኳያ ብዙ መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበለዋል፡፡

የተገኙ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም አሁን የተገኘውን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም የኮሚሽኑ 3ኛው ዓመታዊ የእውቅና መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት፣ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የፌደራል ተቋማት የአደረጃጀት ጸሃፊና የኮሚሽኑ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ለዚህ ውጤት መሳካት ከክልል ጀምሮ እስከ ህብረት ያለው የኮሚሽን መዋቅር ባለቤት በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል።

"ጠንካራ ኮሚሽን ለጠንካራ ፓርቲ"

የፓርቲው የፖለቲካና የስነ ምግባር ጤንነት በመጠበቅ ብዙ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ደስታ ተሰፋው(ዶ/ር)የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም...
17/08/2026

የፓርቲው የፖለቲካና የስነ ምግባር ጤንነት በመጠበቅ ብዙ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ ደስታ ተሰፋው(ዶ/ር)

የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 እቅድ ትውውቅ 10ኛ የጋራ መድረክ ተካሄደ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) በጋራ መድረኩ እንደገለጹት ባሳለፈው ዓመት የፓርቲው የፖለቲካና የስነ ምግባር ጤንነት በመጠበቅ ብዙ ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከማዕከል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የፓርቲው መመሪያዎችና አሠራሮች እንዲሁም የአገራችን የምርጫ ሕጎች እንዲከበሩ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል፡፡

የኢንስፔክሽን ግኝቶችን ለፓርቲው በማቅረብ የሚታዩ ግድፈቶችን እንዲያርም በማድረግ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ የቀረቡ አቤቱታዎችን በማጣራትና ምላሽ በመስጠት የአባላት መብት እንዲከበር ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ደስታ ገለጻ የኮሚሽኑን አቅም በመገንባት በርካታ ውጤቶች የተገኙ ቢሆን ከተልዕኮአችን አኳያ ብዙ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የተገኙ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም አሁን ተገኘውን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመድረኩ በኮሚሽኑ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የጸደቁ የኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የተጠቃለለ ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው የጋራ መግባባት ተፈጥሯል፡፡

በመጨረሻም የኮሚሽኑ 3ኛው ዓመታዊ የእውቅና መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት፣ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የፌደራል ተቋማት የአደረጃጀት ጸሃፊና የኮሚሽኑ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

17/08/2026
የኮሚሽኑ ተቋማዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡ ደስታ ተስፋው(ዶ/ር)የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በፓርቲ ዋና ጽ/ቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄዶ የ2018 በጀት ዓመት የእ...
16/08/2026

የኮሚሽኑ ተቋማዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡ ደስታ ተስፋው(ዶ/ር)

የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በፓርቲ ዋና ጽ/ቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄዶ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ላይ በመወያየት አፅድቋል፡፡

የኮሚሸኑ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ደስታ ተስፋው እንደገለጹት ከማዕከል ጀምሮ እስከ ብልጽግና ህብረት ኮሚሽን ድረስ በቅንጅት በመሰራቱ እና አደረጃጀቶችን ማጠናከር በመቻሉ የኮሚሽኑ የመፈጸም አቅም ከግዜ ወደ ግዜ እያደገ እንዲመጣ አስችሏል ብለዋል፡፡

እንደዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ ወጥነት ባለው መልኩ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት በመቻሉ የተሻለ አፈጸጸም ለማስመዝገብ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

የፓርቲውን ፖለቲካዊ ጤንነት ከማስጠበቅ አኳያ አባላት በፓርቲው ውስጥ መብታቸው እንዲከበርና ሃሳባቸውነ በነጻነት እንዲያንሸራሽሩ በማድረግ እንዲሁም የፓርቲውን የአሰራር ስርዓቶችን እንዲከበሩ በማስቻል የተሻለ ውጤት እንዲመጣ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር አቶ ያሲን ሀቢብ በበኩላቸው የፓርቲው ሃብትና ንብረት ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተቋማዊ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ እንዲሆንም ሚናውን ሲወጣ እንደነበር የገለጹት አቶ ያሲን አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮችን በማረም ለጠንካራ ፖርቲ ግንባታ ኮሚሽኑ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ እና የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እንደገለጹት ከኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶችን የተጠናከረ ክትትል ድጋፍና ግምገማ ሥርዓት ባህል እየሆነ በመምጣቱ ለፓርቲ አሰራሮች ተግባራዊነት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የኮሚሽኑን አሰራር ሥርዓት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የተቀናጀ የኮሚሽን ሥራዎች ሥርዓት እና አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት (KPI) ሥርዓት በማልማት ተግባራዊ መደረጉ ለዲጅታል ብልጽግና አካል መሆን ተችሏል ብሏል።

በመጨረሻም በኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት የለማው የተቀናጀ የኮሚሽን ሥራዎች ዲጅታል ሥርዓት(ICODiS) በባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎ በይፋ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይጫወታል። 🏟️የባሕር ዳር ስታዲየም በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ጊዜያዊ ፍቃድ ማግኘቱ...
16/08/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይጫወታል። 🏟️

የባሕር ዳር ስታዲየም በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ጊዜያዊ ፍቃድ ማግኘቱን ተከትሎ፤ መስከረም ወር ላይ የሚያደርገውን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን በሀገሩ ማድረግ እንደሚያስችለው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረገውን ፍተሻ እና ግምገማ ተከተሎ ብሔራዊ ቡድናችን በመስከረም ወር 2019 በሜዳው ለሚያደርገው ጨዋታ የሚያገለግል ጊዜያዊ የካቴጎሪ 3 (CAT 3) ፈቃድ መስጠቱን ነው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ያሳወቀው።

ካፍ በስታዲየሙ የተመዘገቡ መሻሻሎችን በማድነቅ በላከው ደብዳቤ አሁንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጿል። የተቆጣጣሪ ቡድኑን ግኝቶች እና የሚቀሩ የማስተካከያ እርምጃዎችን የያዘ ሙሉ ቴክኒካዊ ሪፖርት በቅርቡ ለፌዴሬሽኑ እንደሚላክም ገልጿል።

ጨዋታው በሚደረግበት ቀን የስታዲየሙን ዝግጁነት እና የደንቦች አተገባበር ለመከታተል የስታዲየም ተቆጣጣሪ ሊመድብ እንደሚችልም ካፍ አስታውቋል።

#አሚኮ

Address

6000
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባሕር ዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share