የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Bati
  • የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office

የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office, Government Organization, Bati.

19/03/2020

ጠ/ሚ ዐቢይ በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

በኢትዮጵያ የፌስቱላ ህክምና መስራች የነበሩት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት፥ “በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈተ ሕይወት ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል” ብለዋል።

“ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ከ60 ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ክብራቸው የተነጠቀባቸውን በሺህዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ሴቶች ዳግም ቀና ብለው እንዲራመዱ ለፍተዋል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

እኒህን ብርቅዬ ጌጥ ኢትዮጵያ አጥታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ ለሚወዷቸው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና የሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ፤ ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ” ብለዋል።

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ለስራ ባልደረቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመጥቷል።

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ሐምሊን የፌስቱላ ሆስፒታል እና የካትሪን ሐምሊን የፌስቱላ ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት በዶክተር ካትሪን ሐምሊን ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ለኢትዮጵያ ከመቃብር በላይ የሚውል ታሪክን ሰርተው አልፈዋል ያለው የከተማ አስተዳደሩ፥ ለዶክተር ሀምሊን ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።

19/03/2020
18/03/2020

ግብርናን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ

● የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላት እየተገነቡ ነው

● ከ624 በላይ የእርሻ መሣሪያ ዓይነቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ተፈቅዷል
***********************************
(ኢ.ፕ.ድ)

የግብርና ምርት ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሠራሮች በመዘርጋት የብድር አገልግሎት ማመቻቸቱን እና የግብርና ሜካናይዜሽን ማዕከላት እየገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሊድ ቦምባ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ኤጀንሲው የግብርና ሥራ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንዲሁም የግብርና ምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶአደሮች በማቅረብ ምርታማነትን እየሰራ ነው።

ኤጀንሲው በአራት የኢትዮጵያ ክልሎች ለሚገነቡ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላት ግንባታ ወጪ የሚውል 91 ሚሊዮን ብር ከ10 የህብረት ሥራ ማህበራት እና ሥራ ፈጣሪዎች ጋር ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል።

አቶ ካሊድ እንደገለፁት፤ ከ10 የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላትና ሥራ ፈጣሪዎች ጋር ለእያንዳንዳቸው የዘጠኝ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ስምምነት የተፈራረ ሲሆን፤ 70 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ወጪ ኤጀንሲው ይሸፍናል። ቀሪውን 30 በመቶ ደግሞ ሥራውን የተረከቡት የህብረት ሥራ ማህበራትና ሥራ ፈጣሪዎች የሚሸፍኑት ነው።

መንግሥት ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎች ለአርሶአደሩ በማቅረብ ሰፊ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው፤ በተለይ ትኩረት የተሰጠው የሜካናይዜሽን አገልግሎት ምርታማነት ከማሳደጉ በተጨማሪ ጥራት ያለው ምርት ለመሰብሰብና የአነስተኛ አርሶ አደሮችን አኗኗር ለመቀየር ያግዛል ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ የኢትዮጵያ ግብርና በዋናነት በዝናብ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የግብርናው ምርት አስተማማኝ እንዳይሆን አድርጎታል። ከዚህም በተጨማሪ በየጊዜው የሚቀያየረው የአየር ንብረት ለውጥ ችግሩን አባብሶታል:: ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ዋነኛ ትኩረት ሊሆን ይገባል።

አሁን ላይ መንግሥት ልዩ ትኩረት እያደረገበት ያለው የሜካናይዜሽን አገልግሎት በትክክለኛውና በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል የግብርናው ዘርፍ ችግሮችን እንደሚቀርፍ ጠቅሰው፤ በተጨማሪም መካከለኛና አነስተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍና ምርቶቻቸውን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለገበያ እንዲያቀርቡ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የሚገነቡት የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በትግራይ ክልሎች ሲሆን፤ የህብረት ሥራ ማህበራና ገበሬዎቹ በክፍያ የሜካናይዜሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ኃላፊው አስታውቀዋል።

የሜካናይዜሽን አገልግሎቱ መሬት ማዘጋጀት፣ ሰብል መሰብሰብ እህሉን ከገለባው መለየት እና ወደ ጎተራ ማጓጓዝን እንደሚያካትት የገለጹ ሲሆን፤ ማዕከሉ ውስጥ የማሽነሪ ጥገና እና አጠቃቀም ሥልጠና እንዲሁም የማሽኖቹ መለዋወጫዎች እንደሚዘጋጅም ገልጸዋል።

የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላቱ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያከናውነው የሦስት ዓመት ፓይለት ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት በዴንማርክ መንግሥት እና በኔዘርላንድ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር መሆኑም ኤጀንሲው ገልጿል።

የፌዴራል የህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይክተር አቶ ኡስማን ስሩር፤ መንግሥት ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የግብርናውን ሥራ ለመደገፍ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ከ624 በላይ የእርሻ መሣሪያ ዓይነቶች ወደ ሀገር ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መፈቀዱን ትልቅ እርምጃ መሆኑ ጠቁመዋል።

የተለያዩ የሜካናይዜሽን አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት መገንባት ለህብረት ሥራ ማህበራትና ለገበሬዎች ትልቅ ዕድል የሚፈጥርና ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎች በቀላሉ ማግኘት እንደሚያስችላቸው ጠቁመው፤ አገልግሎቱ በምርት ዕድገት ላይ ትልቅ ለውጥ የሚመጣ መሆኑ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀድሞ የነበረው የብድር አገልግሎት ችግር መቀረፉን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በአሁኑ ሰዓት ለህብረት ሥራ ማህበራቱ በመንግሥት የተመቻቸው የብድር አገልግሎት በራሱ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስረድተዋል። የህብረት ሥራ ማህበራቱ ይህንን ዕድል በመጠቀም የተሻለ ስኬት ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የቴክኖሎጂ መሣሪያዎቹን በአግባቡ ከመጠቀም ጋር የሚነሳ ችግር እንዳለ ጠቅሰው፤ አርሶ አደሩ የራሱን ሕይወት የሚቀይሩለትና የአገርን ኢኮኖሚ የሚያሳድጉለትን መሣሪያዎች አውቆ መጠቀም የሚያስችላቸውን አቅም ለመፍጠር ሥልጠናዎችን ሊወስድ እንደሚገባና ለዚህም ምቹ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

አዲስ ዘመን መጋቢት 7/ 2012
ተገኝ ብሩ
ፎቶ ፋይል

18/03/2020

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት፡-

Address

Bati
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የባቲ ከተማ አስ/ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት/Bati Town Industry and Investment Office:

Shortcuts

Share