Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን

Worebabo  Communication   ወረባቦ  ኮሙኒኬሽን የወረባቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ለወረዳዉ ማህበረሰብ ፈጣንና ተአማኒ መረጃ ለመስጠት ይተጋል!!

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ! በወረባቦ ወረዳ 02 ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የማሽላ ሰብል አሁናዊ ገፅታ
06/09/2026

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
በወረባቦ ወረዳ 02 ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የማሽላ ሰብል አሁናዊ ገፅታ

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ! ከ19 ሚሊየን ወደ 155 ሚሊየን ያደገው የወረባቦ የገቢ አሰባሰብ ታሪካዊ እመርታ በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን▽▽▽▽▽▽ቢስቲማ - ጳጉሜ 1/2018 (ወረባቦ ኮ...
06/09/2026

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
ከ19 ሚሊየን ወደ 155 ሚሊየን ያደገው የወረባቦ የገቢ አሰባሰብ ታሪካዊ እመርታ በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን
▽▽▽▽▽▽
ቢስቲማ - ጳጉሜ 1/2018 (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን )

ሀገራችን ኢትዮጵያ የ13ኛዋ ወር ጳጉሜን የመጀመሪያ ቀን በሆነው የእመርታ ቀን የሁለንተናዊ እድገቷን ፍሬዎች እና የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችን በጋራ እያከበረች ትገኛለች።

በወረባቦ ወረዳም የእምርታ ቀን በወረዳው ያሉ ስኬቶችን መሰረት በማድረግ በተለያዮ ሁነቶች እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን የገቢ አሰባሰብ ላይ የታየው እምርታዊ ለውጥ አንዱ ስኬት ነው።

ከእነዚህም በወረዳችን የልማት እና የብልጽግና ስኬቶች መካከል በለውጥ ዓመታት የታየው የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ከ19 ሚሊየን ወደ 155 ሚሊየን ብር የወረዳችንን ማደግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት ማረጋገጫ ታላቅ እመርታ ነው።

የወረባቦ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይማም እንድሪስ ባለፉት ለውጥ አመታት የወረባቦ ወረዳ ገቢ አሰባሰብ ከአመት አመት በማሳደግ የወረዳውን የገቢ አቅም ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።

በወረባቦ ወረዳ በ2010 ይሰበሰብ የነበረው ገቢ 19 ሚሊየን ብር እንደነበር የሚናገሩት አቶ ይማም የገቢ አቅምን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በ2018 በጀት አመት ወደ 155 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ! "በወረባቦ ወረዳ 02 ቀበሌ በሀይቅ ዳር ዙሪያ እየለማ የሚገኘው የፍራፍሬ ልማት የአርሷደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው" የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ...
06/09/2026

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

"በወረባቦ ወረዳ 02 ቀበሌ በሀይቅ ዳር ዙሪያ እየለማ የሚገኘው የፍራፍሬ ልማት የአርሷደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው" የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም አህመድ

▽▽▽▽
ቢስቲማ - ጳጉሜ 1/2018 (ወረባቦ ኮሙኒኬሽን)

በወረባቦ ወረዳ ጳጉሜ 1 ቀን " እምርታ ለዘላቂ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል 02 ቀበሌ አህያ ገደል ሰፋፊ የአትክልትና ፍራፍሬ ክላስተር እየለማ የሚገኘውን ሙዝና ፓፓያ ተክል ጉብኝት በማድረግ ተከብሯል ።

የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም አህመድ ባለፉት አመታት እንደ ሀገር በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ እምርታዊ ለውጥ የምግብ ሉአላዊነታችን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ስራ የተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ወረዳም ዛሬ ላይ ያየናቸው የፍራፍሬ ልማቶች የአርሷደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የምግብ ሉአላዊነትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን የገለፁት አቶ አደም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቱ ብዙ የተደከመበት ፣ ብዙ የተለፋበት አሁን ላይ ባለው ቁመና በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝና ሀገራችንን ላለመቸው የስኬት ጉዞ የራሳችንን አሻራ ያሳረፍንበት በመሆናቸው እነዚህን የልማት ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የወረባቦ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ሁሴን በሀይቅ ዳር የገበታ ለትውልድ ግንባታ ምርቃት ላይ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ የሀይቁን ዙሪያ በአትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ምርትና ምርታማነትን በመጨምር የአርሷደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በወረባቦ ወረዳ 50 ሄክታር ሙዝ እና 18 ሄክታር ፖፖያ መተከሉን ገልፀዋል።

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ! የኢትዮጵያ ትንሳኤ በባዶ ምኞት ሳይሆን በታማኝ ሥራ፣ በቁርጠኝነትና በማይናወጥ ጽናት ላይ እየተገነባ ነው። ባልተረጋጋ ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ ነባራዊ ሁኔ...
06/09/2026

ጳጉሜ1- እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

የኢትዮጵያ ትንሳኤ በባዶ ምኞት ሳይሆን በታማኝ ሥራ፣ በቁርጠኝነትና በማይናወጥ ጽናት ላይ እየተገነባ ነው።

ባልተረጋጋ ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን፣ በማይናወጥ መሠረት ላይ የቆመ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ መፍጠር መቻላችን ዛሬ ለጀመርነው ታላቅ እመርታ ዋነኛ ማረጋገጫ ነው።

ዛሬ ሀገራችን ትላንት ከነበረችበት የጥገኝነትና የዕዳ ታሪክ በክብር እየተላቀቀች ነው። እጆቻችንን ለዕርዳታና ለምጽዋት መዘርጋት አቁመን፣ ወደሚመጥነን ታሪካዊ ከፍታና ሉዓላዊ ልዕልና እየተሻገርን እንገኛለን።

ሀገራዊ ሸክማችንን አቅልለን ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሸጋገርንባት፣ እያንዳንዱም ዜጋ የኢኮኖሚው እኩል ተጠቃሚና ባለቤት የሚሆንባት አካታች የፋይናንስ ሥርዐት የሰፈነባት አዲስ ኢትዮጵያን እየመሠረትን ነው።ይህንን የተጀመረ የከፍታ ጉዞ ዘላቂ ለማድረግ ግን የሁላችንም የዕለት ተዕለት ተግባራዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን የምናመርተው በምክንያት ነው፤ የምንሸምተውም የገዛ ራሳችንን ማንነትና ክብር ነው። "ኢትዮጵያ ታመርታለች፤ የኢትዮጵያን እንሸምታለን!" ስንል የሀገር ፍቅራችንን በገበያችንና በኢኮኖሚያችን ላይ በተግባር እያሳየን ነው።

በግብርናችንም ቢሆን በባሕላዊ አሠራርና በዝናብ መጠበቅ ብቻ አንወሰንም፤ ከዝናብ እስከ መስኖ፣ ከቀለብ እስከ መኖ በሰፊው በመትጋት የራስን በራስ የመቻል ትርጉም ለዓለም እናሳያለን።

ሀገር የምትገነባው በልጆቿ ጥረት ብቻ በመሆኑ፣ ሁላችንም በሙሉ አቅማችን እንሠራለን፣ በታማኝነትም በግብር ሀገር እንገነባለን። እጆቻችንን አጣጥፈን አንቀመጥም፤ በአንድነትና በኅብረት ቆመን ሁላችንም የምንመኛትንና የምንኮራባትን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌ ሀገር እውን እናደርጋለን!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ **************እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን...
06/09/2026

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ
**************
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡

ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡

የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡ በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ጳጒሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ወንጀልን መከላከል፤ የላይ አርማጭሆ ወረዳ የማኅበረሰብ ተሞክሮ !ወንጀልን የሚጸየፍ እና ለጸጥታ ኃይሉ የሚተባበር ማኅበረሰብ ሲኖር ወንጀልን መከላከል እና ወንጀለኛን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋል...
05/09/2026

ወንጀልን መከላከል፤ የላይ አርማጭሆ ወረዳ የማኅበረሰብ ተሞክሮ !

ወንጀልን የሚጸየፍ እና ለጸጥታ ኃይሉ የሚተባበር ማኅበረሰብ ሲኖር ወንጀልን መከላከል እና ወንጀለኛን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋል እንዲሁም የሚፈለገውን ሰላም ማስፈን እንደሚቻል በተግባር የተገለጠበት አኩሪ ሥራ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ተፈጽሟል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ በመክፈት የአንዲት መንገደኛ እናትን ሕይወት የቀጠፈ ተጠርጣሪ በአካባቢው የጸጥታ ኃይል እና በማኅበረሰቡ ፈጣን እና ጠንካራ ቅንጅት ከነጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጽሕፈት ቤቱ አዛዥ ኢንስፔክተር አበበ ወዝያለው ወንጀሉ የተፈጸመው በላይ አርማጭሆ ወረዳ ችራ ቀበሌ መኾኑን ገልጸዋል።

ተጠርጣሪው በተጓዦች ላይ እገታ ለመፈጸም ከጎንደር ወደ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወፍ አርግፍ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ከጫካ ውስጥ ኾኖ ተኩስ መክፈቱን ተናግረዋል። በተተኮሰው ጥይት የአንድ ንጹሃን መንገደኛ እናት ሕይወት ተቀጥፏል።

የአካባቢው ማኅበረሰብ ከወረዳው የጸጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት ወንጀሉ ወደተፈጸመበት ቦታ ተጉዞ ተጠርጣሪውን በተኩስ ልውውጥ ከነጦር መሣሪያው በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለ አስታውቀዋል። ተጠርጣሪው የተያዘው ማኅበረሰቡ ወንጀልን እና ወንጀለኛን በመጸየፍ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ ነው ብለዋል።

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ይስማው ጀምበሩ በበኩላቸው የወረዳው የጸጥታ መዋቅር እና ማኅበረሰብ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ሁልጊዜም በቅንጅት አኩሪ ገድል ሲፈጽም መቆየቱን አውስተዋል። በዛሬው ዕለትም ቅንጅቱን አጠናክሮ ይህንኑ ወንጀለኛን በቁጥጥር ሥር አውሏል ነው ያሉት።

ሰላም በሚያውኩ ወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ የሚገኘው ፈጣን እርምጃ ማኅበረሰቡ ለሰላሙ ዘብ ሲቆም፤ ወንጀልን እና ወንጀለኛን ሲጸየፍ እና ለጸጥታ ኃይሉ ሙሉ ድጋፍ ሲሰጥ ምንም ዓይነት ወንጀለኛ ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል ያሳየ መኾኑንም አብራርተዋል።

የተደራጀ እና ከሕዝብ ጋር የተሳሰረ የጸጥታ መዋቅር የሰላም ዋስትና መኾኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አሚኮ

የጽንፈኛው ቡድን አረመኔያዊ ጥቃት፡ በወላድ እናት አምቡላንስ ላይ በተከፈተ ተኩስ የሰው ሕይወት አለፈጽንፈኛው ቡድን በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ግድያ፣ እገታና እንግልት አሁንም አጠና...
05/09/2026

የጽንፈኛው ቡድን አረመኔያዊ ጥቃት፡ በወላድ እናት አምቡላንስ ላይ በተከፈተ ተኩስ የሰው ሕይወት አለፈ

ጽንፈኛው ቡድን በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ግድያ፣ እገታና እንግልት አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1:30 አካባቢ በደቡብ ወሎ ዞን ከለላ ወረዳ ከከለላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተሻለ ሕክምና ሪፈር የተባለች ነፍሰ ጡር እናትን ይዞ ይጓዝ በነበረ አምቡላንስ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።

አምቡላንሱ 01 ቲርቲራ ከተማ ሲደርስ ራሱን የሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ የሚያቀርበው ፅንፈኛ ቡድን ባደረሰው ጥቃት የሕክምና ባለሙያ የቆሰለ ሲሆን፣ ወላዷን ለማዳን አብራ ትጓዝ የነበረች አንዲት ንጹሕ ሴት ሕይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ሊያልፍ ችሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ ጉዳት የደረሰበትን አምቡላንስ ጠልፎ ወደ 07 ባከት ቀበሌ ይዞት የሄደ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ባለሙያ እና ወላዷ እናት በ01 ቲርቲራ ጤና ጣቢያ አስፈላጊው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለባቸው ዳውድ እንደገለጹት፤ ለአማራ ሕዝብ እታገላለሁ እያለ በስሙ የሚምለው ይህ ጽንፈኛ ቡድን፣ በንጹሃንና የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ባሉ አካላት ላይ እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ሰብአዊ ጥቃት በማድረስ ለሕዝብ ያለውን ጥልቅ ጥላቻ በተግባር እያሳየ ይገኛል።

አቶ አለባቸው በጥቃቱ ሕይወቷን ላጣችው እህታችን ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን የተመኙ ሲሆን፣ ጉዳት ለደረሰበት የጤና ባለሙያ ደግሞ ፈጣን ምሕረትና ማገገምን ተመኝተዋል።
ከለላ ወረዳ የሙዩኒኬሽን

*****

የደቡብ ወሎ ዞን የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናትን በልዩ ልዩ ሁነቶች ለማክበር መዘጋጀቱን አስታወቀ▽▽▽▽▽የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት “የኢትዮጵያ መንሠራራት”...
04/09/2026

የደቡብ ወሎ ዞን የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናትን በልዩ ልዩ ሁነቶች ለማክበር መዘጋጀቱን አስታወቀ
▽▽▽▽▽
የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት “የኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል አጠቃላይ መሪ ሐሳብ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በልዩ ልዩ ሁነቶች ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ገለጹ።

አቶ አሊ የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት አከባበርን አስመልክተው ለደቡብ ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በሰጡት መግለጫ፣ ዘንድሮ ቀናቱ “የኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል አጠቃላይ መሪ መልዕክት በልዩ ልዩ አገር አቀፍ፣ ክልላዊና ዞናዊ ሁነቶች እንደሚከበሩ አስታውቀዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው በሰጡት መግለጫ፣ የጳጉሜን ወር ያለፈውን ዓመት ስኬትና ጉድለት መገምገሚያ፣ የመጪውን አዲስ ዓመት ዕቅድ ለመተግበር የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ እንዲሁም የትግበራ ምዕራፍ ዋዜማ ሆኖ የሚያገለግል ልዩ ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል።

የአከባበሩ ዐቢይ ዓላማም ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ ከፍታ ማንሠራራት መጀመሯን በማብሰር፣ ለበለጠ ሀገራዊ ውጤት በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳትንና የተስፋ መንፈስ መፍጠር እንደሆነ ዋና አስተዳዳው አብራተዋል።

እንደ አቶ አሊ መኮንን ማብራሪያ፣ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ሁነቶችና ተያያዥ ጭብጦች ይከበራሉ፦

ጳጉሜን 1 (እመርታ ቀን)፦ ሀገራችን ከተረጂነትና ጥገኝነት ተላቃ ወደ አምራችነት እያደረገች ያለችውን ታሪካዊ ሽግግር ለማብሰር፣ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች፣ የምግብ ሉዓላዊነት ድሎች እና የ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄ ውጤቶች በሰፊው ይታወቃሉ።

ጳጉሜን 2 (መንሠራራት ቀን)፦ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ ሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደቶችና ማኅበራዊ ዕድገቶች በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ያመጧቸው አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ይበልጥ ይጎላሉ።

ጳጉሜን 3 (ጽናት ቀን)፦ የፀጥታ ተቋማትን ዘመናዊ ቁመናና ለሀገረ-መንግሥቱ ዘላቂነትና ሉዓላዊነት የተከፈለውን የጀግኖች መስዋዕትነት በመዘከር፣ የሀገር መከላከል ዓቅማችንና ሀገራዊ ፅናት ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት መሆናቸው ይበሰራል።

ጳጉሜን 4 (ኅብር ቀን)፦ ኅብረብሔራዊ አንድነትን፣ አብሮነትን፣ መረዳዳትንና በጎነትን ማዕከል ያደረጉ ሁነቶች በመከወን የወል ትርክትን የማጠናከርና ብዝኃነትን የማጎልበት ሥራዎች ይከናወናሉ።

ጳጉሜን 5 (ነገ ቀን)፦ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የሳይበር ሉዓላዊነት፣ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የ«5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ» ስኬቶችን በማሳየት ዲጂታልና በራስ አቅም የምትቆም አዲሷን ኢትዮጵያ የሚያመላክቱ ሁነቶች ይካሄዳሉ ሲሉም በዝርዝር አብራርተዋል።

በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው “መንሠራራት” የሚለው መሪ ሐሳብ ሀገራችን ችግሮችን ከመቋቋም ወደ ፈጣንና ዘላቂ የከፍታ ምዕራፍ የምትሸጋገርበትን ስትራቴጂካዊ ሂደት የሚያመለክት በመሆኑ፣ የዞኑ ማኅበረሰብና የመንግሥት አካላት ቀናቱን በላቀ ተነሣሽነትና በተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ!ብቁና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኮሙዩኒኬሽን ለተቋማዊ ማሻገር!የደቡብ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በአማራ ክልል ደረጃ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አበይ...
02/09/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

ብቁና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኮሙዩኒኬሽን ለተቋማዊ ማሻገር!

የደቡብ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በአማራ ክልል ደረጃ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አበይት ተግባራት፣ በፈጣንና ተስፋፊ የመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በዞኑ ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከክልሉ 1ኛ ደረጃ ተሸላሚ ለመሆን የበቃ ሲሆን፣ የዋንጫና የእውቅና ሽልማቱን ተጎናጽፏል።

ይህ አንፀባራቂ ስኬት የመምሪያው አመራሮች፣ የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎችና የየደረጃው የዞኑ መዋቅሮች በጋራ ባሳዩት የላቀ ትጋት፣ የተቀናጀ የቡድን ሥራ እና እውነትን መሠረት ያደረገ የመረጃ ተנגባቢነትን ለማረጋገጥ ባደረጉት ያልተቆጠበ ጥረት የተገኘ የውጤታማነት ማረጋገጫ ነው።

ላስመዘገባችሁት ታላቅና አርአያነት ያለው ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፣ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለውን የመረጃ ድልድይ አጠናክሮ በመቀጠል ለተጨማሪ ስኬቶች እንደምታበቁ አንጠራጠርም።
ደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን

Address

Bistima
Bistima

Telephone

+251332210032

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Worebabo Communication ወረባቦ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share