ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office

  • Home
  • Ethiopia
  • Boditi
  • ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office

ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office ትጋት ለላቀ ስኬት ! https://t.me/Boditiprosperity

15/08/2026

ጊፋታ – ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ ነው!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋራ በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል

  በቦዲቲ ከተማ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የክረምት ስፖርት ሻምፒዮና ለማስጀመር በውድድርና ስነስርዓት ደንቦች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚያስችል መድረክ ተካሄደቦዲ...
15/08/2026

በቦዲቲ ከተማ የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የክረምት ስፖርት ሻምፒዮና ለማስጀመር በውድድርና ስነስርዓት ደንቦች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚያስችል መድረክ ተካሄደ

ቦዲቲ ፤ ነሐሴ ፤ 09/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የ2018 ልዩ ልዩ የክረምት ስፖርት ሻምፒዮና ለማስጀመር በውድድርና ስነስርዓት ደንቦች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የሁሉም ተሳታፊ ክለቦች ተወካዮችና የዳኞች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴዎች የተገኙ ሲሆን የጨዋታዎች እጣ ማውጣት ስነስርዓትም መካሄድ ችሏል።

በውድድሩ ተሳታፊ የሆነ ሁሉም ክለቦችና ስፖርተኞች በመተዳደሪያ ደንብ መሰረት የውድድር ስነ-ስርዓትንና ደንብን በመጠበቅ ጨዋታዎችን ማካሄድ እንዳለባቸው ግንዛቤ ትምህርት ተሰጥቷል ።

ህግና የውድድር ስነ-ስርዓት ደንብን የጣሰ ክለብም ሆነ ስፖርተኛ በተቀመጠው አሰራር መመሪያ መሰረት ተደርጎ የቅጣት ውሳኔዎች የሚተላለፍበት እንደሆነ በመድረኩ መልዕክት ተላልፏል።

የ2018 ክረምት ወራት ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና በከተማው ነገ እሑድ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም በቦዲቲ ሁለገብ ስታዲየም መካሄድ የሚጀምር በመሆኑ ሁሉም የከተማው ነዋሪና ስፖርት ወዳድ በስፍራው በመገኘት እንዲከታተሉ ዘንድ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ጥሪውን አስተላልፏል።

የቦዲቲ ከተማ አጠቀላይ አመራር ላለፉት 2 ቀናት ስካሄድ የነበረው የ2018  ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መጠናቀቁን በማስመልከት በግል ባለሀብት በአቶ አለምሰገድ ዋጃ...
14/08/2026

የቦዲቲ ከተማ አጠቀላይ አመራር ላለፉት 2 ቀናት ስካሄድ የነበረው የ2018 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መጠናቀቁን በማስመልከት በግል ባለሀብት በአቶ አለምሰገድ ዋጃና እየተገነባ ያለውን የአለሙኒዬም ፋብሪካ መስክ ጉብኝት አድርገዋል።

በመስክ ምልከታው የወላይታ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ፤ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ጻዲቁ ፈለቀ እንዲሁም የከተማ አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።

ነሐሴ ፤ 8/2018 ዓ.ም

14/08/2026
የመንግስትና የፓርቲ አጠቃላይ ተግባራት በታቀደው ልክ በውጤት ለመፈጸም የአመራር ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። አቶ ዘካሪያስ ታደሰቦዲቲ ፤ ነሐሴ ፤ 08/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦ...
14/08/2026

የመንግስትና የፓርቲ አጠቃላይ ተግባራት በታቀደው ልክ በውጤት ለመፈጸም የአመራር ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። አቶ ዘካሪያስ ታደሰ

ቦዲቲ ፤ ነሐሴ ፤ 08/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ ላለፉት 2 ቀናት ስካሄድ የነበረው የ2018 ዓ.ም የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም የአመራር ግምገማ መድረክ ተጠናቋል።

የወላይታ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ፤ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘካሪያስ ጃታ እና የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ግርማ የግምገማ ማጠቃለያ መድረኩን በጋራ መርተዋል።

የወላይታ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ ታደሰ እንደገለፁት የግምገማ መድረክ በተለይ በአመራሩ ዘንድ የተግባር ፤ የአመለካከት እንዲሁም የአስተሳሰብ አንድነት ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ መኖሩን ጠቁመዋል።

በ2018 በጀት አመት የህዝብን አዳጊ ፍላጎት ለማሟላት አመራር የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮ ተቀብሎ የሰራው ስራ አበረታች መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘካሪያስ በቀጣይ በግምገማ መነሻ እያንዳንዱን ተግባር በተሻለ ውጤት ለመፈጸም መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሁሉም ተግባራት በተቀመጠው ግብ አንጻር ቀጣይነት ባለው መልኩ የተሳካ ሆኖ እንዲፈጸም ዘንድ ግምገማው ለአመራሩ ትልቅ አቅመ የጨመረ እንደሆነ እምነታቸውን ገልጸዋል።

አቶ ዘካሪያ በቀጣይ የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰሩ ስራዎች አኳያም አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን በተለይም ቦዲቲ ከተማን በሚመጥን መልኩ የከተማው ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ገቢ አሟጦ መሰብሰብ ትኩረት ልደረግ እንደሚገባ አስረድተዋል።

እንደ ዞናችን ብሎም እንደ ክልል ካሉ ከተሞች አንጻር በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች የምትገኘው የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ለነዋሪዎቿ ውብና ጹዱ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ እንዲትሆን ማድረግ የመላው አመራር ሀላፊነት እንደሆነ የጠቆሙ ሲሆን በተለይ ህብረተሰቡን በሚገባ ባሳተፈ መልኩ ከጽዳት ጀምሮ ያሉ የአከባቢ ጥበቃ ስራዎች በትኩረት መመራት ይኖርባቸዋልም ብሏል።

ከመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተመራ የሚገኝ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እንዲያመጣ አመራሩ ኮሚትመንት ወስዶ መንቀሳቀስ አለበት ስሉም አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም አቶ ዘካሪያስ ሁሉም የፓርቲ አመራር በሂስ ግለሂስ ግምገማ ወቅት በድክመት የተነሱ ነጥቦችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብሎ ለውጤታማነን መዘጋጀት ይጠበቃል ስሉ አሳስበዋል።

የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ዘካሪያስ ጃታ በበኩላቸው ግምገማው አመራሩ ከእውቀት ፤ ከተግባር እንዲሁም ከአመለካከት አንጻር አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ እና ለሌሎች አረአያ በሚሆን መልኩ ለቀጣይ ተግባር ዝግጁ እንደሆን አቅም የፈጠረ ነው ብሏል።

በአመቱ አፈጻጸም ላይ በጥንካሬ የተገመገሙ ጉዳዮችን ማስቀጠል ከአመራሩ የሚጠበቅ እንደሆነ ማብራሪያ የሰጡት ክቡር ከንቲባው በድክመት የተገመገሙና በተለይ አስቸኳይ የሆነ የእርምት እርምጃ በመወሰድ ያለባቸውን ደግሞ በትክክል መዝግቦ በመያዝ ለተሻለ ውጤት በቁርጠኛነት መንቀሳቀስ እንደቀጣይ አቅጣጫ
አስቀምጠዋል።

ሁሉም አመራር በግምገማው ላይ እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ ሂስ የተደረገባቸውን ነጥቦችን ተቀብሎ በቀጣይ ለተሻለ ውጤታማ አፈጻጸም ዝግጁ ሆኖ መገኘት አለበት ብለዋል።

በምጣኔ ጥናት መነሻ የከተማ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ሁሉንም ገቢ የከተማን እድገት በሚመጥን ልክ አሟጦ መሰብሰብ አማራጭ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነም ተነግሯል።

የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ግርማ በበኩላቸው አመራሩ የመንግስት እና የፓርቲን አጠቃላይ ተግባራት በአግባቡና በፓርቲ ጥብቅ ዲሲፕሊን ተመርቶ በተመደበበት ውጤታማ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ ግምገማው አቅም የጨመረ ነው ገልጸዋል።

ፓርቲያችን የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ላይ የአመራሩ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተግባሩን ማዕከል አድርጎ ለቀጣይ ውጤታማ መሪነት ሚና በቂ እውቀትን ፤ አቋም የሚያሳድግ ምዘና መሆኑን አብራርተዋል።

በመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡ ዘርፈብዙ አገልግሎቶች ጤናማ ፤ የተገልጋይ እርካታን ያገናዘቡ እና ከመልካም አስተዳደር ችግሮች የጸዱ እንዲሆን ዘንድ አመራሩ በትክክል ሀላፊነቱን እንዲወጣም ግምገማው መነሳሳት የፈጠረ ነው ብሏል።

14/08/2026

አንጋፋው የወላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪ አቶ አብራሃም ባቾሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
******************

ስማቸው ከወላይታ ሕዝብ ታሪክ ጋር የሚነሣው የሀገር ሽማግሌ እና አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት አቶ አብራሃም ባቾሬ በገጠማቸው የጤና እክል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በወላይታ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የተከበሩ የነበሩት አቶ አብረሃም፣ በኢትዮጵያ በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተለያዩ ኃላፊነት ሀገርን እና ሕዝብን አገልግለዋል።

በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ በዓለም አቀፍ የሕፃናት ድርጅት፣ በወላይታ ልማት ማኅበር፣ በወላይታ ዞን ባሕል ቱሪዝም፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባነት እና በተለያዩ የሥራ መስኮች በኃላፊነት እና በባለሙያነት ሠርተዋል።

አቶ አብራሃም ባቾሬ የወላይታ ታሪክ በዓለም እንዲታወቅ የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን የሠሩ ሲሆን፣ በተለይ የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብም ከፍተኛ ሚናቸውን ተወጥተዋል።

አቶ አብራሃም ባቾሬ የወላይታ ሀገር ሽማግሌ ሆነውም የወላይታ አካባቢው እና ሀገራዊ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ በመፍታት እና አስታራቂ በመሆን ያገለገሉ የሰላም አምባሳደርም ነበሩ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በአቶ አብራሃም ባቾሬ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።

 #ጊፋታ የባህል ሀብታችንን ለዓለም የምንገልጽበት የትውልድ ውል ነው!!👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 #መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋራ በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል።
14/08/2026

#ጊፋታ የባህል ሀብታችንን ለዓለም የምንገልጽበት የትውልድ ውል ነው!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋራ በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል።

14/08/2026

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በጊፋታ በዓል አከባበር ላይ ያደረጉት ንግግር ።
#ጊፉታ

14/08/2026

Address

Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-Boditi Town Prosperity party office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share