Akaki Kaliti Woreda 5 Communication

  • Home
  • Akaki Kaliti Woreda 5 Communication

Akaki Kaliti Woreda 5 Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Akaki Kaliti Woreda 5 Communication, Government Organization, Akaki Kaliti, .

08/09/2017

የሀገር ፍቅር ቀን ጷግሜ 03-13-09 ዓ.ም እጃችን እስኪሻክር እንሰ ራለን ምክንያቱም ሀገራችንን ስለምንወዳት በሚል መሪ ቃል በአ/ቃ/ክ/በወረዳ 05 አሰተዳደር በድምቀት ተከበረ፡፡የቀኑ መከበር ዋነኛ አላማ -ቀደምት መሪዎቻችን ያስቀመጡልንን ጅምር የልማት ስራዎች ከግብ ማድረስ:የልማትና የዴሞክራሲ ተግባራትን ማስቀጠል፡ጠንክሮ በመስራት ሀገራችንን ከድህነት ማላቀ ቅ፡ብዝሀነትን በማጎልበት አብሮነትን ማሳደግ፡የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና የማይሹ የውስጥና የውጪ ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመቆጣጠር ሁሉም ዜጋ ሀገሩን ዳር ድንበሩን በማስከበርና ጠንክሮ በመስራት ቤተሰቡንና ሀገሩን ከድህነት በማላቀቅ የሀገር ፍቅር ስሜቱን የሚገልፅበት ኘው ተብሏል፡፡

27/08/2016

ጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በጥቃቅን ተዋሕሲያን አማካኝነት የሚፈጠር ሲሆን መጠነ ብዙ ተከታታይ ውሃማ ተቅማጥ እና ትውከት የበሽታው ዋነኛ ምልክቶች ናቸው፡፡ ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሀ መጠጣት እንዲሁም በሚገባ ያልበሰለ እና በንጹህ ሁኔታ ያልተቀመጠ ምግብ መመገብ ለበሽታው ያጋልጣል፡፡

ማንኛውንም በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የተያዘን ሰው ወደ ጤና ጣቢያ በፍጥነት መውሰድ ፣ባሰቀመጠና ባስታወከ ቁጥር ብዙ ፈሳሽ እንደ ኦ.አር.ኤስ፣ ሻይ፣ አጥሚት፣ በመውሰድ የወጣውን ፈሳሽ መተካት ዋናውና ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።

27/08/2016

በኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ
ሳምንታዊ አቋም መግለጫ 
ነሀሴ 20 ቀን 2008 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መንግስት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚፈታተኑ ችግሮችን በመቅረፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማጎልበት ጠንክሮ መስራቱን ይቀጥላል!
የሀገራችን ህዝቦችና መንግስታቸው የበለጸገች ሀገርና ህዝብ ለመፍጠር ባለፉት ዓመታት ብዙ ሠርተዋል። በዚህም በሁሉም የህይወት ዘርፎች ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግበዋል። በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝቦች ፈቃድ ባጸደቁት ህገመንግስታዊ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትመገንባት ጀምረዋል። የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት ያረጋገጠ ፌዴራላዊ ስርዓት ገንብተዋል። ሁሉም ሃይማኖቶች፣ ባህሎችና አመለካከቶች እኩል የሚያስተናግዱበት ስርዓትን ፈጥረዋል።
የኢትዮጵያ ህዝቦችና መንግስታቸው በተለይም ባለፉት 15 ዓመታት ባደረጉት ርብርብ ለተከታታይ 13 ዓመታት ባለሁለት አሃዝና ተከታታይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ ችለዋል። ዕድገቱ የህዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲችልም ሰፊ ጥረት አድርገዋል። ይህ ዕድገት በገጠር አርሶ አደሩ ከመሬቱ ሳይፈናቀል በከተሞቹም የወጣቱ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት በሚጀምሩ አማራጮች ተረጋግጦ የተገኘ ነው። በትምህርትና በጤና የተደረሰበት ደረጃም የህዝቦችን ተጠቃሚነት ያሰፈነ ነው። ለቀጣይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶች ጭምር እንዲያግዙ የተገነቡ ሠፋፊ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችም የህዝቦችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና በቀጣይም የሚያሰፉ ናቸው።
ይህ ለውጥ በዓለም አቀፍና በአህጉራዊ መድረኮች ላይ የሀገራችንን ተሰሚነት ያሳደገ ነው። በ50 ዓመት ውስጥ የገጠመንን ከባድ ድርቅ በዋናነት በራሳችን አቅም ለመቋቋምም ያስቻለን ነው። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ለሀገራችን በጎ የሚያስቡ ወዳጅ ሀገራትና ህዝቦች ጭምር በጉጉት የሚያዩትና የሚጠብቁት ሁሉን አቀፍ ዕድገት ነው።
ይሁን እንጂ ይህን ዕድገት ወደሁሉም ዘርፍና አካባቢ በማስፋት ሂደት ውስጥ የመልካም አስተዳደር እጦትና ሌሎች በወቅቱ ምላሽ ያላገኙ ችግሮች ታይተዋል። ሀገራችንን የማይወዱ አካላት ይህን የህዝብና የመንግስት ውስጣዊ ችግር በመጥለፍ ለራሳቸው ዓላማ በሚፈበርኳቸው አጀንዳዎች ቀጣይ የዕድገት ግስጋሴያችንን ለማስተጓጎል ሞክረዋል። እነኚህ አካላት በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የመጀመሪያ ረድፍ ላይ የምትገኝ ሀገር ባለቤት የሆነውን ወጣት፡ ተስፋ እንደሌለው አስመስለውም ቀስቅሰዋል። ይህን ተከትሎም ህይወትና ንብረት ያጠፉ ሁከቶች ተፈጥረዋል።
የኢፌዴሪ መንግስት ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው በተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ እንደሚሰጥና ከህዝብ ጋርም እንደሚወያይ ቃል በገባው መሠረት የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በችግሩ ላይ ጥልቀት ያለው ግምገማ ማካሄድ ጀምረዋል። ለቀጣይ ትግል የሚያግዙና የሀገራችንን ብሩህ ተስፋ የሚያስቀጥሉ ውሳኔዎችንም በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ህዝቦችና መንግስት በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሱ ህዝባዊ ጥያቄዎች ለተሻለ ትግልና ለቀጣይ ስራ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆኑ ተረድተዋል። ከህዝብ ጥያቄዎች ጋር ሆን ተብሎ የተቀላቀለ የሀገራችን ጠላቶች አጀንዳ ደግሞ ተነጥሎ ሊከስም እንደሚገባ አቋም ይዘዋል። ይህም የሚሆነው ገዢው ፓርቲና መንግስት ወደውስጣቸው በመመልከት ውስጣዊ ችግሮቻቸውን በማጽዳትና የህዝብን ፍላጎት በሚያረካ ልክ የአመራር አቅም በመገንባት ነው፡፡
በመሆኑም የኢፌዴሪ መንግስት የበለፀገ ህዝብና ሀገር ለመፍጠር፡ ህዝብና መንግስት ባደረጉት ጥረት የተገኙ ውጤቶች በምንም ምክንያት ሊስተጓጎሉ እንደማይገባ ያምናል። ገዢው ፓርቲ ችግሮችን በጥልቀት አይቶ ለመፍታት የጀመረውን ግምገማም ያደንቃል። የኢትዮጵያ ህዝቦች በቅርብ ርቀት የሚያዩትን መፃኢ ተስፋቸውን ላለማስነጠቅ ከመንግስት ጎን መቆማቸውንም ያደንቃል። የተፈጠሩ የህዝብ ቅሬታዎችን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም መንግስት ራሱን ለመፈተሽ በወሰደው አቋም ልክ የኢትዮጵያ ህዝቦችም ከውሳኔው ጎን በመቆም አጋርነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም የኢፌዴሪ መንግስት በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያስተላልፋል።

03/04/2016

"ጥራት ያለው ትምህርት ለላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ፌስቲቫልና ኤግዚቪሽን ተካሄደ።
በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 5 "ጥራት ያለው ትምህርት ለላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ፌስቲቫልና ኤግዚቪሽን በቃሊቲ ቡልቡላ የመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት ቤት በቀን 21/07/08 አ/ም ተከበረ።በእለቱም በተማሪዎች የተሰሩ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎችና አውደ ርህዮች ፣ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ወድድር ቀርቦል።

25/11/2015
24/11/2015

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሴካፋ ውድድር የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ በእለተ ረቡዕ ከቀኑ 10 ሰአት ሲል ከሱማሊያ ጋር አቻው ጋር በሀዋሳ አዲሱ ስቴዲየም ያደርጋል። ቅዳሜም ከታንዛኒያ ጋር እዛው የሚጫወት ይሆናል ተብለናል ካልቀየሩት(ሴካፋም እንደ ሊጋችን በተለይም የሰአት ለውጥ በማድረግ ይጋራናል)....መንገደኛ ነሽ ክፉ አትናገሪ ነው ያላችሁት?...እሺ ተቀብያለሁ ለማንኛውም ሁለቱንም ጨዋታዎች ከስፍራው እየተከታተልን የምናደርስ ይሆናል።

23/11/2015

በጃንዳሜዳ የሚከበረውን የጥምቀት ክብረ በዓላት ለመታደም ነበር፡፡ የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት በመስቀል አደባባይ በ10,000 ተሳታፊዎች ዝግጅቱን አንድ ብሎ የጀመረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ዘንድሮ 40,000 ለመድረሱ እነዚሁ በሩጫው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የባህር ማዶ ሰዎች ቁጥር የራሱ ድርሻ እንዳለው ይታመናል፡፡ የውጭ ዜጎች ለጉብኝት ከሚመርጧቸው የአገሪቱ ታላቅ ዝግጅት አንዱ እንደሆነ እምነት አሳድሯል፡፡

የተለያዩ አገሮች ዜጎች ምንም ዓይነት ዕድሜ፣ ፆታና ዘር እንዲሁም ሃይማትና የቆዳ ቀለም ሳይገድባቸው በአንድ መድረክ ተሳትፈው ስሜታቸውን የሚገልጹበት፣ የሚደሰቱበትና የሚዝናኑበት ነው፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በያዝነው ኅዳር ወር መካሄዱ በራሱ ‹‹ኅዳር ሲታጠን›› በሚለው የቆየ ብሂል ዜጎች አካባቢያቸውን የሚያፀዱበት ወር ከመሆኑም ባሻገር፣ የአገሪቱ መልክዓ ምድር በአረንጓዴ ፅዕዋት ደምቆና ተውቦ የሚስተዋልበት ወቅት ሩጫውን የተለየ ያደርገዋል፡፡

የወቅቱን መልክዓ ምድራዊ ገጽታ በሚያመላክተው አረንጓዴ ቲሸርት መስቀል አደባባይና አካባቢውን የሚያደምቀው ታላቁ ሩጫ በዚህ ብቻ ሳይወሰን፣ የአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ተብሎ ተወስዷል፡፡

ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ የሚከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከወትሮው የሚለይበት ዓይነተኛ መገለጫዎች አሉት፡፡ ዋናውና የመጀመርያው ታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሩጫው ተሳትፎ ካጠናቀቁ በኋላ ከዓለም አቀፍ የሩጫ መድረክ መሰናበቱን በይፋ የሚያበስርበት ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በሁለተኛው ታላቁ ሩጫ ላይ አሸናፊ የነበሩት፣ ጥንዶቹ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያምና ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ እንዲሁም በሦስተኛው ታላቁ ሩጫ አሸናፊ የነበሩት በተመሳሳይ ጥንዶች ስለሺ ስህንና ጥሩነሽ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለና ሌሎችም የአገሪቱ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዝግጅቱ ታዳሚዎች ይሆናሉ፡፡



በጃንዳሜዳ የሚከበረውን የጥምቀት ክብረ በዓላት ለመታደም ነበር፡፡ የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት በመስቀል አደባባይ በ10,000 ተሳታፊዎች ዝግጅቱን አንድ ብሎ የጀመረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ ዘንድሮ 40,000 ለመድረሱ እነዚሁ በሩጫው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የባህር ማዶ ሰዎች ቁጥር የራሱ ድርሻ እንዳለው ይታመናል፡፡ የውጭ ዜጎች ለጉብኝት ከሚመርጧቸው የአገሪቱ ታላቅ ዝግጅት አንዱ እንደሆነ እምነት አሳድሯል፡፡

የተለያዩ አገሮች ዜጎች ምንም ዓይነት ዕድሜ፣ ፆታና ዘር እንዲሁም ሃይማትና የቆዳ ቀለም ሳይገድባቸው በአንድ መድረክ ተሳትፈው ስሜታቸውን የሚገልጹበት፣ የሚደሰቱበትና የሚዝናኑበት ነው፡፡ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በያዝነው ኅዳር ወር መካሄዱ በራሱ ‹‹ኅዳር ሲታጠን›› በሚለው የቆየ ብሂል ዜጎች አካባቢያቸውን የሚያፀዱበት ወር ከመሆኑም ባሻገር፣ የአገሪቱ መልክዓ ምድር በአረንጓዴ ፅዕዋት ደምቆና ተውቦ የሚስተዋልበት ወቅት ሩጫውን የተለየ ያደርገዋል፡፡

የወቅቱን መልክዓ ምድራዊ ገጽታ በሚያመላክተው አረንጓዴ ቲሸርት መስቀል አደባባይና አካባቢውን የሚያደምቀው ታላቁ ሩጫ በዚህ ብቻ ሳይወሰን፣ የአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ተብሎ ተወስዷል፡፡

ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ የሚከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከወትሮው የሚለይበት ዓይነተኛ መገለጫዎች አሉት፡፡ ዋናውና የመጀመርያው ታላቁ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሩጫው ተሳትፎ ካጠናቀቁ በኋላ ከዓለም አቀፍ የሩጫ መድረክ መሰናበቱን በይፋ የሚያበስርበት ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በሁለተኛው ታላቁ ሩጫ ላይ አሸናፊ የነበሩት፣ ጥንዶቹ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያምና ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ እንዲሁም በሦስተኛው ታላቁ ሩጫ አሸናፊ የነበሩት በተመሳሳይ ጥንዶች ስለሺ ስህንና ጥሩነሽ ዲባባ፣ ቀነኒሳ በቀለና ሌሎችም የአገሪቱ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዝግጅቱ ታዳሚዎች ይሆናሉ፡፡

20/11/2015

የወረዳ 5 ሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር ሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ በተካሄደው የ2007 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ምዘና ከ116ቱ ወረዳዎች ሁለተኛ ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ፡፡
የወረዳ05 አስተዳደር ሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ በተካሄደው የ2007 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ምዘና ከ116 የወረዳ ሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ፅ/ቤት ባሳዩት የስራ አፈጻጸም ሁለተኛ ደረጃን በማግኘት ከቢሮው የእውቅና የምስክር ወረቀት፣ዋንጫና ላፕቶፕ ኮፒዩተር ተበርክቶላቸዋል፡፡በመጨረሻም ያናገርናቸው የወረዳ 5 ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ፈጻሚዎች እንደገለጹት የህ ውጤት የተገኝው እያንዳንዱ ፈጻሚ ስራዎን በቅንንትና በታማኝነት በመስራታችን እንደሆነ ገልጽው ይህ ሽልማት ቀጣይ ለምናከናውናቸው ሥራዎች እንደሚያነሰሳቸው ገልጽው በቀጣይም አንደኛ ለመውጣት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

20/11/2015

የወረዳ 5 ደንብ ባስከበር አገልግሎት ጽ/ቤቱ በተለያዩ ቦታዎች የያዛቸውን የተለያዩ የሽሻ እቃዎችን በማቃጠል አስወገደየአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በተለያዩ መንገድ የያዛቸውን የሽሻ እቃዎች በማቃጠል ማሰወገዱን የወረዳው ድንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፒክተር ድሪባ ወዬቻ ገለጹ፡፡ኃላፊው ጨምረውም እንደገለፁት ሲያሰጠቅሙ የተያዙ ግለሰቦች እቃዎችን ከመውረስ በተጨማሪ በደንብ ቁጥር 54 መሰረት መቀጣታቸውን አስታውቋዋል፡፡የሽሻ እቃዎቹ በዋነኝነት የተያዙት በወረዳው ልዩ ስሙ ጉሙሩክ እና ሃይቆች በሚባሉ አካባቢዎች ላይ በሚሰሩ የፅ/ቤቱ ኦፊሰሮችና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሊያዙ እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም ኃላፊው አያይዘው ማህበረሰቡ እንደዚህ አይነቱ ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈጸም እንዲያውገዘውደና ለሚመለከተው ክፍል ጠቆማ በመስጠት እንዳለበት ገልጸው፡፡ህብረተሰቡ በአካባቢው ያለውን ወጣት በመምከርና ወላጆችም ልጆቻቸውን አዋዋል በሚገባ አውቀው ነገ ተውልድተ ረካቢ ወጣቶችን ከአልባሌ ሱሶች እንዲቆጠቡናየበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

20/11/2015

የወረዳ5 ባህልና ቱሪዝም ጽቤት የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ የቲያትር ሰልጣኞችን በሃገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ አስመረቀ

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ5 ባህልና ቱሪዝም ጽቤት ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ለ2 ወራት በክረምት የወጣቶችበጎ ፈቃድ የቲያትር ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ አማተር ሰልጣኞች በሃገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽአስመረቀ፡፡በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የእሩይ አማተር ኪነጥበብቡድን ነባር ተዋናዮችና ሰልጣኝ ተመራቂዎች የተለያዩ መልክት አዘልና አስተማሪ ተውኔቶችን ለታዳሚው በማቅረብ የፕሮግረሙ ድምቀት ሆነዋል፡፡በዚህ ፕሮግራም ከመግቢያ ሽያጭ የተገኘ ሰባት ሺ ብር (7000) አዲስ ለተቋቋመው የኩላሊት ህሙማን መርጃ ማህከል አማተር ተመራቂዎቹ አበርክተዋል፡፡በሃገር ፍቅር ቲያትር አዳራሽ የተገኙት የወረዳ05 ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳዊት ሙሴ ስለ ወጣት ተመራቂዎች እንደገለጹት ስልጠናው ወጣቶች በክረምት ወቅት አልባሌ ቦታ ከመዋል ተጠብቀው ተሰጦአቸውን የሚያዳብሩበት እና ኪነጥበብ ዋነኛ ልማት ሃይል በማድረግ ህብረተሰቡን እያዝናኑ ላማስተማር የተሻለ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው ተመራቂዎች በቀጣይ የበጋ ወቅትም የኪነጥበብ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሳሰብ በዚህ ረገድ ጽ/ቤቱ ለኪነ-ጥበብ ቡድኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ለተመራቂ አማተር ስልጣኞች የሰርተፍኬት ሽልማት አበርክተዋል፡፡

20/11/2015

አደረጃጀቱ ዘጠኙን የሊግ ስራ አስፈጻሚዎችን ሹመት አፀደቀየወረዳ 5 ወጣት ሊግ ሰበብሳቢ የነበረው ወጣት ደፋሩ ሃ/ሚካኤል እንደገለጸው የተጀመረውን ልማት ማስቀጠል የሚችሉ የተሰጡትን ተልዕኮዎችን መወጣት የሚችሉና ለወጣቶች ተጠቃሚነት የሚተጉ ከህዝብ አደረጃጀት የተውጣጡ 15 እጭዎችን አቅርቦ ለኮንፈረሱ ተሳታፊዎች ካስተዋወቀ በሆላ በተደረገ ምርጫ ልጉን የሚመሩ ዘጠኙን ስራ አስፈጻሚዎች ተመርጠዋል፡፡በመጭሻም ወጣት ደረጀ አበራ የሊጉ ሰብሳቢ አድርጎ ሹሞል፡፡በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ወጣት ሊግ 10ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ኮንፍረንስ ወቅት አደረጃጀቱ ዘጠኙን የሊግ ስራ አስፈጻሚዎችን ሹመት አፀደቀ፡፡በኮንፈረሱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙልጌታ ተካ እንደገለጹት ሊጉ ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እንደሰራ አስታውሰው በተለይ ደግሞ ሊጉ አምስተኛውን ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከሌሎች አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ትልቅ ሚና ነበረው ብለዋል፡፡

Address

Akaki Kaliti

ADISS ABABA

Telephone

+251926878484

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki Kaliti Woreda 5 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Akaki Kaliti Woreda 5 Communication:

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share