Saylem Woreda Communications

Saylem Woreda Communications saylem woreda communication

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

ካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው።በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የተከ...
02/09/2026

ካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የተከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸም የሚገመገም ሲሆን፣ የአመራር ሥራ አፈጻጸምም የሚመዘንበት መሆኑ ተገልጿል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ የሥራ አፈጻጸምን በግልጽ ሁኔታ በመመርመር ጥንካሬዎችን ማጠናከር፣ ድክመቶችን ማረምና በቀጣይ የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።

በመድረኩ ላይ የካፋ ዞን የፐብሊክና የሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ አቶ ነፃነት ብርሃኑ፣ የሳይለም ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አየለ፣ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ሽፈራው እንዲሁም ሌሎች የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በተለያዩ የማሀበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን!👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100079727967214
ቴሌግራም፡-
https://t.me/saylemworedagovernment

02/09/2026
ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር ሂደታቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ እንዲያጠናቅቁ ተገለጸ።የሳይለም ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር ሂደታቸውን እስከ ነሐሴ 30...
01/09/2026

ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር ሂደታቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ እንዲያጠናቅቁ ተገለጸ።

የሳይለም ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች የግብር ሂደታቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስቧል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታርኩ ተካ እንደገለጹት፣ ግብር ከፋዮች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የግብር ሂደታቸውን ማጠናቀቅ አለባቸው።

ከነሐሴ 30 ቀን በኋላ ሂደቱን ሳያጠናቅቁ የሚቆዩ ግብር ከፋዮች በየቀኑ ሊጨመር ለሚችለው ወለድና በሲስተሙ ላይ ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂ እንደሚሆኑ ኃላፊው ገልጸዋል።

በመሆኑም ግብር ከፋዮች ነሐሴ 30 ቀን የመጨረሻ የጊዜ ገደብ መሆኑን በመገንዘብ የግብር ሂደታቸውን በወቅቱ እንዲያጠናቅቁ መልዕክታቸውን አስተላልፏል ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በተለያዩ የማሀበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን!👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100079727967214
ቴሌግራም፡-
https://t.me/saylemworedagovernment

በ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እኩል ነጥብ ያመጡት መንትዮች በአማራ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል 15.56 በመቶዎቹ  የዩኒቨርስቲ መግቢያ ማለፊያ ...
30/08/2026

በ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና እኩል ነጥብ ያመጡት መንትዮች

በአማራ ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል 15.56 በመቶዎቹ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል።

በዚህ አጠቃላይ ውጤት ውስጥ በአማራ ክልል የባህር ዳር ከተማ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሆኑት መንትዮቹ በዕምነት መልካሙ እና ዮርዳኖስ መልካሙ ያመጡት ድንቅ ውጤት ልዩ ትኩረት የሳበ ሆኗል።

መንትዮቹ በዕምነት እና ዮርዳኖስ በዕድሜና በደም ዝምድና ብቻ ሳይሆን በትምህርት ገበታቸውም ያላቸውን ትጉህነት በማሳየት ሁለቱም ከ600 ፣ 413 ውጤት በማምጣት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናውን ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
EBC #

30/08/2026
ሀገራዊ ምክክሩ ለትውልድ ዘላቂ ትምህርት የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ጉባዔ ነው ሀገራዊ ምክክሩ የሕዝቡን የምክክር ባህል የሚያንፅ እና ለትውልድ ዘላቂ ትምህርት የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ጉባዔ መሆኑን የ...
30/08/2026

ሀገራዊ ምክክሩ ለትውልድ ዘላቂ ትምህርት የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ጉባዔ ነው

ሀገራዊ ምክክሩ የሕዝቡን የምክክር ባህል የሚያንፅ እና ለትውልድ ዘላቂ ትምህርት የሚያስጨብጥ ታሪካዊ ጉባዔ መሆኑን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አሕመድ ሁሴን ገለጹ።

የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ከውጤቱም በላይ አስተማሪ የሆነና ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀገራዊ ምክክሩ በተመካካሪነት ያገለገሉት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አሕመድ ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የምክክር ጉባዔው የተለያየ አቋም ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበትና ልዩ ልዩ ሀሳቦች የተንጸባረቁበት ነው።

ምክክሩ ለረጅም ዓመታት እየተንከባለሉ በመምጣት ወደ አለመግባባትና ግጭት ሲመሩ በቆዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት የተመከረባቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

በምክክሩ ሂደት ተመካካሪዎች አቋማቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውንና ሥጋቶቻቸውን በነፃነት የገለጹበት ጉባዔ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

ምክክሩ ከ400 በላይ የውሳኔ ሀሳቦችን በማቅረብ መጠናቀቁን አንስተው፤ ተመካካሪዎች በአብዛኛው አጀንዳ ላይ ከስምምነት የደረሱበትና በጥቂት አጀንዳዎች ላይ የአማራጭ ሀሳቦች የቀረቡበት መሆኑን አስረድተዋል።

ተመካካሪዎች ለሀገርና ለትውልድ በማሰብ የቆዩ አቋሞቻቸውን ለውጠው ወደ መግባባት የመጡበት ውጤታማ ጉባዔ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዘመናችን ያልተግባባንባቸው ጉዳዮች ተለይተው መውጣታቸው ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ተግባር ለመጪው ትውልድ ልዩነት ተፈጥሮአዊ የሆነና መፍትሔውም ምክክር መሆኑን የሚያስገነዝብ ታሪካዊ ጉባዔ ነው ብለዋል።

ከምክክሩ የተገኙ ሀሳቦች በፖሊሲና ሕግ ግብዓትነት የሚካተቱ መሆናቸውን አመልክተው፤ ለተግባራዊነታቸው በትኩረት መስራት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትም በምክክር ሂደቱ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በቀጣይም የበኩሉን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ከግጭትና የኃይል አማራጭ ከመምረጥ ይልቅ ተቀራርቦ መምከር የበለጠ ጥረት፣ ትዕግስትና ብስለት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል።

ግጭት ከአስተሳሰብ ስለሚመነጭ ይህን አስተሳሰብ መቀየር የሚቻለው በምክክር ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።

የኃይል አማራጭ የተከተሉ አካላትም መፍትሔ የሚገኘው በምክክር እንደሆነ በመገንዘብ በውይይት ችግሮቻቸውን መፍታት እንዳለባቸው መክረዋል።

ሕብረተሰቡን ከድህነት ለማላቀቅ፣ በሰላም ተንቀሳቅሶ መስራት፣ መነገድና ምርቱን በገበያ መሸጥ እንዲችል ምክክርና ድርድርን መምረጥ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹነሐሴ 24/2018 ዓ.ም  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራል...
30/08/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም የገለፁ ሲሆን ኖርዌይም የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋር ነች ብለዋል::

በዚህ የሐዘን ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከኖርዌይ ሕዝብ ጎን እንደሚቆም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ቼልሲ ብራይተንን 4–3 በማሸነፍ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ።ሳይለም ወረዳ ኮሙኒኬሽን — ነሐሴ 24፣ 2018 ዓ.ም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ብራይተንን 4–...
30/08/2026

ቼልሲ ብራይተንን 4–3 በማሸነፍ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ።

ሳይለም ወረዳ ኮሙኒኬሽን — ነሐሴ 24፣ 2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ብራይተንን 4–3 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ድል አስመዝግቧል።

በስታምፎርድ ብሪጅ ብራይተንን ያስተናገደው ቼልሲ፣ በተደረገው ተመጣጣኝና አስደሳች ጨዋታ በአጠቃላይ ሰባት ጎሎች የተቆጠሩበትን ጨዋታ በድል አጠናቋል።

ለቼልሲ ሮሜኦ ላቪያ፣ ፔድሮ ኔቶ፣ ጆአኦ ፔድሮ እና ኮል ፓልመር ጎሎችን አስቆጥረዋል።

በብራይተን በኩል ደግሞ ማሊክ ያልኮዬ እና ፓስካል ግሮስ ጎል ሲያስቆጥሩ፣ ተጨማሪው ጎል በራስ መረብ ላይ የተቆጠረ ነበር።

በዚህ ውጤት ቼልሲ በሊጉ የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ድል ሲያስመዘግብ፣ ብራይተን ደግሞ ነጥብ ሳይወስድ ጨዋታውን አጠናቋል።

በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ሰንደርላንድ ፉልሃምን 1–0 ሲያሸንፍ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ 1–1 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል።

Address

Kafa Zone Saylem Woreda
Bonga

Telephone

+251910095551

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Saylem Woreda Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share