Hiwot Assegid

Hiwot Assegid "Head of Revenues Bureau, SWEPR | Dedicated Leader | Driving Regional Growth & Economic Integrity''

🇪🇹 ብልጽግና፡ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌትነት!ኢትዮጵያ ከነበረችበት የፖለቲካ ስብራት ወጥታ፣ የሁላችንም የምትሆንበት አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል!ብልጽግና ፓርቲ የትላንቱን የፖለቲካ አግላይነት በመ...
03/05/2026

🇪🇹 ብልጽግና፡ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌትነት!

ኢትዮጵያ ከነበረችበት የፖለቲካ ስብራት ወጥታ፣ የሁላችንም የምትሆንበት አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል!

ብልጽግና ፓርቲ የትላንቱን የፖለቲካ አግላይነት በመስበር፣ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ተምሳሌት ለማድረግ የሚተጋ የታሪክ ቀያሪ ኃይል ነው። እኛ የምንመራው በቃላት ሳይሆን በተግባር በሚታይ እኩልነትና አንድነት ነው።

🔹 ከጥግ ተመልካችነት ወደ ውሳኔ ሰጪነት!

ከለውጡ በፊት የነበረው "እህት" እና "አጋር" የሚል የከፋፋይነት ታርጋ አብቅቶለታል። ብልጽግና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት ያቀፈ አገራዊ ውህድ ፓርቲ በመመስረት፣ እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ጉዳይ ላይ እኩል የመወሰንና የመምራት መብቱን አረጋግጧል። ዛሬ ማንም የበይ ተመልካች አይደለም፤ ሁላችንም የሀገራችን ባለቤቶች ነን!

🔹 የሰፋ የፖለቲካ ምህዳርና ተፎካካሪነት

🌾ከተቃዋሚነት ወደ ተፎካካሪነት፦ በስደትና በበረሃ የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች በሰላም ገብተው የራሳቸውን አማራጭ ፖሊሲ ይዘው እንዲፎካከሩ ምህዳሩን አስፍቷል።

🌾ገለልተኛ ተቋማት፦ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሀብትና በሎጂስቲክስ ተደራጅቶ በነጻነት እንዲሰራ በማድረግ፣ ብልጽግናም እንደማንኛውም ተፎካካሪ ፓርቲ ለህግ ተገዢ በመሆን ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አርአያነቱን አሳይቷል።

🔹 የኢትዮጵያ ህዳሴና የአፍሪካ ኩራት

ብልጽግና ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ የሚሠራ፣ አፍሪካዊ ተምሳሌትነትን ያለው ፓርቲ ነው።

🌾ከተረጂነት ወደ ሰጪነት፦ ሀገራችን ማንም የማያንበረክካት፣ በራሷ የምትቆም ኩሩ ሀገር እንድትሆን ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ፓርቲ ብልጽግና ነዉ።

🌾ጽኑ መሰረት፦ ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ በተዘረጋ ወጥና ዘመናዊ አሰራር፣ የሀገረ መንግስት ግንባታችንን እያጠናከረ ይገኛል።

🤝 ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት፦ የአንድነታችን ሚስጥር!

የእኛ ጥንካሬ ልዩነታችን ሳይሆን ውበታችን በሆነው ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ላይ የተገነባ ነው። ጥላቻን በፍቅር፣ መከፋፈልን በውህደት በማሸነፍ ለነገዋ ኢትዮጵያ ጽኑ መሰረት አስቀምጧል።

"ያልተገባ ስም መስጠት ሳይሆን፣ አማራጭ ሀሳብ ይዞ መቅረብ የሰለጠነ ፖለቲካ መገለጫ ነው!"

🗳️ ምርጫዎ ብልጽግና ይሁን!

✨ ምልክታችን፦ የስንዴ ነዶ 🌾

01/05/2026
01/05/2026
23/02/2026
23/02/2026
23/02/2026

Address

Bonga
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hiwot Assegid posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share