25/08/2026
የሰላም ሚኒስቴር ከቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ደም ለገሱ
ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም ቡታጅራ
የሰላም ሚኒስቴር ከቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር “በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በክረምት ወራት ውስጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
እየተካሄደ በሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም የደም ልገሳ ያደረጉ ሲሆን፤ ባለፉት ቀናትም በማህበራዊ ድጋፍ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በአከባቢ ፅዳት፣ የትራፊክ ደንብ ማስከበር ስራዎች ላይ በበጎ ስራዎች መሳተፋቸውን በመግለፅ የከተማው ነዋሪዎችም ላደረጉት ቀና ትብብር ከሰላምና ሚኒስቴር የመጡ አካላት ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን ጀማል በከተማዋ ባለፉት ግዚያትም ድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አካላት ሰጪዎች, ዩኒቨርስቲዎች ሌሎችም ከተማ አስተዳደሩ ተቀብሎ ወጣቶችን በማስተባበር ሰፊ ሰራ መሰራቱን በመጠቆም ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ግዚያት እንደዚ ድጋፍ ሰጪ አካላት ተቋማት ድርጅቶች በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
በጎነት ለአብሮነት!!