04/09/2026
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የግብር ሕግ ማስከበር ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።
ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረው የግብር ሕግ ማስከበር ሥራ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።
በሕግ ማስከበር ሥራው በተለይም የደረሰኝ አጠቃቀምና አሰጣጥ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን፣ የግብር ሕግና ደንብን ተከትለው የማይሠሩ ተቋማትና ድርጅቶች ላይም ተገቢው አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
የደረሰኝ ሕግን መጣስ፣ግብርን ለመሰወር የሚደረጉ ሕገወጥ ተግባራትና ሌሎች የግብር ሕግ ጥሰቶች በቸልታ እንደማይታዩ በማስገንዘብ፣ የቁጥጥርና የሕግ ማስከበር ሥራው በተጠናከረ መልኩ በዞኑ ወልቂጤ ከተማ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ይህ ጥብቅ የሕግ ማስከበር አቅጣጫ ሁሉም ግብር ከፋይ ሕጋዊ ግዴታውን በወቅቱና በትክክል እንዲወጣ፣ ፍትሐዊ የግብር ሥርዓት እንዲጠናከር እና የገቢ መሰረቱ እንዲሰፋ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል
በተጨማሪም በነሐሴ ወር የታቀደውን የገቢ ግብ በሙሉ ለማሳካት፣ የገቢ አሰባሰብን ለማሳደግና የገቢ ክፍተትን ለማስቀረት የደረሰኝ ቁጥጥር፣ የግብር ሕግ ማስከበርና የግብር ከፋይ ክትትል ሥራዎች በቅንጅትና በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።
በክልሉ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በግብር ህግ ማስከበር ላይ የተጀመረው ተግባር በሁሉም የገቢ መዋቅሮች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ቀጣይም በተጠናከረ መልኩ እንደሚሠራበት ተገልጿል።
👇👇👇👇👇
👉የፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61562204634443
👉የቲክቶክ ገፅ
https://www.tiktok.com/.ethiopia4?_t=ZM-8ynTRPSsANR&_r=1
👉የዩቲዩብ ገፅ (https://youtube.com/?si=ELneJRp2Lj7xJ8GK
👉ኢንስታገራም
https://www.instagram.com/centralethiopiarevenue?igsh=cmY4a2g5dnAxcmQ3
👉በሬዲዮ ፕሮግራም በDebub Fm100.9 ሬዲዮ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ8:40_9:00 ይከታተሉን
👉 ይደውሉ
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!