Fendika City Revenue

Fendika City Revenue The purpose of this page is to make awereness for the pelople about tax education.

05/09/2022
05/09/2022

ለሁሉም የደረጃ "ለ"ግብር ከፋዮች በሙሉ
ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም የተጀመረው የግብር/ታክስ መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ 5ቀን ብቻ የቀረ በመሆኑ ውድ የደረጃ"ለ"ግብር ከፋዮቻችን በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመክፈል መሞከር ለአስፈላጊ መጉላላት እንዲሁም ቅጣትና ወለድ ስለሚዳርግ እስከ ጳጉሜ 5/2014 ድረስ አሳውቃችሁ በመክፈል ራሳችሁን ከቅጣት እና ወለድ እንድታድኑ በጥብቅ እናሳስባለን።
"ግብራችን ለህልውናችን ለልማታችን"
የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት

26/08/2022

በእያንዳንዷ ደቂቃ ገቢ በመሰብሰብ ህልውናችንን ዳግም እናረጋግጥ
የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት
ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም
ወራሪው የትግሬ ኃይል ዳግም የከፈተው ጦርነት በዋናነት አማራ ክልል ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ይታወቃል። ጦርነት በየሰከንዱ የሚበላው ፋይናንስ የሀገርን ዕድገት የሚጎትትና የሚያዳክም መሆኑ ይታወቃል።
የህዝባችንን ህልውናና ክብር ለማስጠበቅና ወራሪው የትግራይ ኃይል ዳግም የአማራ ህዝብና መሬት የማያይበትን ሁኔታ ለመፍጠር የጸጥታ ኃይላችንን ማጠናከር ተገቢ ነው።
ስለሆነም የማሸነፊያችን ዋነኛ መንገድ አንድነታችንና የፋይናንስ አቅማችንን በማጠናከር የጸጥታ ኃይላችንን የትጥቅና ስንቅ አቅርቦት አስተማማኝ ማድረግ ነው።
ህይወቱን ሰጥቶ እኛ ቀና ብለን እንድንሄድ ግንባር ላይ ተሠልፎ የሚዋደቅ ወገናችን እያለ ግብር እና ታክስ ለመክፈል ጊዜ ስጡኝ የሚል፣ ግብር እና ታክስ የሚሠውር ግብር ከፋይ እንደሌለ ካለፈው ተምረናል።
ስለሆነም በዚህ ወቅት እያንዳንዷን ደቂቃ ገቢ ከመሰብሰብ ችላ የሚል የገቢ ተቋም ባለሙያና የመንግስት የፖለቲካ አመራርና ሊኖር ስለማይችል ሁላችንም በንቃትና በትኩረት ለሠላማችን እንሰለፍ።
"ግብራችን ለሠላማችን ለልማታችን!"

የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶችማንኛውም ታክስ ከፋይ እራሱ አስልቶ ያቀረበውን የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ የታክስ ሚኒስቴሩ ሲፈቅድለት ሊያሻሽል እንደሚችል በአዋጅ ተደንግጓል፡፡የራስ...
19/08/2022

የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች
ማንኛውም ታክስ ከፋይ እራሱ አስልቶ ያቀረበውን የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ የታክስ ሚኒስቴሩ ሲፈቅድለት ሊያሻሽል እንደሚችል በአዋጅ ተደንግጓል፡፡
የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለማሻሻል በታክስ ከፋዩ ማመልከቻ ሲቀርብ ማሻሻያው ስለሚፈቀድበት ሁኔታ ግልጽ አሰራረር ማስቀመጥ በማስፈለጉ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 29 በተሠጠው ስልጣን መሰረት መመሪያ አውጥቷል፡፡
መመሪያው ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበውን የራስ ታክስ ስሌት እንዲሻሻል ስልሚፈቀድበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ሲሆን መመሪያ ቁጥር 144/2011 በመባል ይታወቃል፡፡
በዚህ መመሪያ መሰረት የታክስ ስሌት የሚሻሻልባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
ታክስ ከፋዩ ራሱ ያዘጋጀው የታክስ ስሌት እንዲሻሻል ሲያመለክት በሚከተሉት ምክንያቶች ሚኒስቴሩ ሊያሻሽልለት ይችላል፡፡
1. የድምር ስህተት ሲኖር፤
2. የአጻጻፍ ስህተት ሲኖር፤
3. ከሒሳብ መደብ አመራረጥ (chart of account) ጋር የተያያዘ ስህተት ሲኖር፤
4. የጆርናል ምዝገባ ስህተት ሲኖር፤
5. ሒሳብ ወደ ሌጀር ሲተላለፍ የተከሰተ ስህተት ሲያጋጥም፤
6. ከሒሳብ ማስተካከያ (adjusting entry) ጋር የተያያዘ ስህተት ሲያጋጥም፤
7. በሒሳብ መዝገብ ላይ ሳይመዘገብ የተዘለለ የገቢና ወጭ ሰነድ ሲኖር፤
8. የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ሀብት ቆጠራ አያያዝ ስህተት ሲኖር፤
9. የሒሳብ አያያዝ ዘዴ ስህተት ሲያጋጥም፤
10. በታክስ ህጎች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ቦርዱ የውጭ ኦዲተሮችን የኦዲት ሪፖርት ሲመረመር ባገኘው ግኝት መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ ሲያጋጠም፤
11. ሶስተኛ ወገን በሚሰጠው ማረጋገጫ ወይም በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ መሰረት በሂሳብ መዝገቡ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ሲያስፈልግ፤
12. በታክስ ሕግ ያልተፈቀደ ወጭ በተቀናሽነት በመያዙ ምክንያት የተፈጠረ ስህተት ሲኖር
13. የግልና የንግድ ሒሳቦች በመቀላቀላቸው የተፈጠረ ስህተት ሲያጋጥም፤
14. በታክስ ማስታወቂያ ቅጽ ላይ የአመዘጋገብ ወይም የአገላለጽ ስህተት ሲያጋጥም፤
15. በታክስ ወይም በተለይ በኤክሳይዝ ታክስ ሒሳብ አያያዝ ላይ የማምረቻና አስተዳደራዊ ወጪዎች ተፋልሰውና ባልተገባ ቦታ ላይ ተመዝግበው ሲገኙ የታክስ ስሌት ሊሻሻል ይችላል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች የተለየ እና በሚከፈለው የታክስ መጠን ላይ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል አሳማኝ ምክንያት ሲያጋጥም ስራ አስኪያጁ የራስ ታክስ ስሌት ማሻሻያ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌግራም፦ ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን አርብ ማታ ከ3፡00 ጀምሮ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራም፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣ፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎት፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!

ይነበብ!!!
19/08/2022

ይነበብ!!!

19/08/2022

የታክስ ሕግ ተገዥነት
የታክስ ሕግ ተገዥነት ማለት መንግስታት የታክስ ገቢን ለመሰብሰብ ያወጡትን የታክስ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን እና መርሆዎችን በፈቃደኝነት በማክበር የግብር እና ቀረጥ ግዴታዎችን በተገቢው ጊዜ እና መንገድ መወጣት ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ የታክስ አስተዳዳር ከግብር ከፋዮቹ የሚጠብቀው መሠረታዊ ግዴታዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም፡-
1. በግብር ከፋይነት መመዝገብ፣
2. ግብርን በወቅቱ እና በትክክል ማሳወቅ፣
3. በትክክል ሪፖርት ማድረግ ወይም ትክክለኛ ደጋፊ ማስረጃዎች ማቅረብ እና
4. ግብርን መክፈል ናቸው፡፡
1. በግብር ከፋይነት መመዝገብ፡- እያንዳንዱ በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኝ እና በግብር ከፋይነት መመዝገብ የሚጠበቅበት ግለሰብ እና ተቋም በሙሉ በራሱ ተነሳሽነት ወደ ታክስ መረቡ መምጣት እና በግብር ከፋይነት መመዝገብ ይገባዋል፡፡ መመዝገብ ለሚመለከተው የታክስ ዓይነት ሁሉ መመዝገብን ይጨምራል፡፡ ለአንዱ የታክስ ዓይነት ተመዝግቦ ለሌላው አለመመዝገብ የህግ ተገዥ አያሰኝም፡፡
በእኛ አገርም ያለው የግብር ከፋዮች ምዝገባ ሥርዓት የጣት አሻራ መስጠትን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማውጣትን እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የሂሳብ መዝገብ መያዝን የሚያካትት በመሆኑ እያንዳንዱ ግብር ከፋይ እነዚህን ሥርዓቶች አሟልቶ በግብር ከፋይነት መመዝገብ ይጠበቅበታል፡፡
2. ታክስ ማስታወቅ፡- በሌላ በኩል ከአንድ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ ግብር ከፋይ የሚጠበቀው ሌላኛው ግዴታ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና ባስቀመጠው ግብርን የማሳወቂያ መንገድ ተጠቅሞ ለግብር ሰብሳቢው ተቋም መክፈል የሚገባውን የታክስ መጠን ማሳወቅ ነው፡፡ ይህም ማለት ከነበረው የሽያጭ መጠን እና በህግ የተፈቀዱ ተቀናሽ ወጪዎች አንጻር እንዲሁም በህግ በተቀመጡ የታክስ ቀመሮች አንጻር ለገቢ ሰብሳቢው መክፈል የሚገባው የታክስ መጠን በራሱ አስልቶ ግብር ሰብሳቢው ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና ባዘጋጀው መንገድ ማሳወቅ ነው፡፡ ገቢዎች ሚኒስቴር እንደ ታክሶቹ ዓይነት የማሳወቂያ የጊዜ ሰሌዳ ያስቀመጠ ሲሆን በተቀመጠው አግባብ ማሳወቅ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ለየታክስ/ግብር አይነቱ የተለያየ ማስታወቂያ ቅጾች የተዘጋጁ በመሆኑ ቅጾቹን በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮም ተቋሙ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ግብራቸውን የሚያሳውቁበት ስርዓርአትንም ዘርግቷል፡፡
3. ሪፖርት ማድረግ፡- የሚጠበቅበትን የግብር መጠን ያሳወቀ ግብር ከፋይ ያሳወቀው የታክስ መጠን ትክክለኛ ስለመሆኑ በደጋፊነት ሊያስረዱለት የሚችሉ የተለያዩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ሪፖርቶች በዋናነት የገቢ መግለጫ /income statement/፣ የሂሳብ መዝገብ /balance sheet/፣ የገንዘብ ፍሰት /cash flow/ እና የመሳሰሉትን ያካትታሉ፡፡
4. ታክስ መክፈል፡- በአራተኛ ደረጃ ከአንድ ግብር ከፋይ የሚጠበቀው ግዴታ በራሱ ፈቃድ መክፈል ይገባኛል በማለት አምኖ ያሳወቀውን እንዲሁም በተለያዩ ሪፖርቶች ያረጋገጠውን የታክስ መጠን በግብር ሰብሳቢው ተቋም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መክፈል ነው፡፡ ይህም ማለት አመታዊ የሆኑትን በየዓመቱ በተቀመጠው ጊዜ፣ ወርሃዊ እና ሌሎቹንም በተቀመጠላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት መክፈል ነው፡፡
በአጠቃላይ፤ የታክስ ህግ ተገዥነት ማለት እነዚህን እና ሌሎች ከታክስ ጋር የተገናኙ ግዴታዎችን በራስ ተነሳሽነት መወጣት ማለት ሲሆን ከገቢዎች ሚኒስቴር አንጻር የህግ ተገዥነት ማለት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲያስፈጽም የተሰጡትን የጉምሩክ እና የታክስ ህጐችን

19/08/2022

ለ300 የፌዴራል ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸው እውቅና ተሰጣቸው

የገቢዎች ሚኒስቴር “ግብር ለሀገሬ” በሚል መሪ ቃል 3ኛ ዙር የፌዴራል ግብር ከፋዮች የዕውቅና ስነስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የታክስ አምባሳደሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር አቶ ላቀ አያሌው በዕውቅና ስነስርዓቱ ላይ “ግብር መክፈል የሀገር ፍቅር መገለጫ የሚሆነው በፍቅርና በንፅህና ሲከፈል” ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ግብርን በአግባቡና በተገቢው መንገድ መክፈል ትንሹ አገራዊ መስዋዕትነት፣ የዜግነት ክብር መገለጫና ለትውልድ አሻራ ማስቀመጫ የባለቤትነት ዕድል እንጂ የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ መቅጫና መቅረጫ ህግ አለመሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ግብራቸውን በታማኝነት የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ በግብር ስወራ የተሰማሩ፣ የሚጠበቅባቸውን ቀረጥና ታክስ ላለመክፈል ያገኙትን አጋጣሚ የሚጠቀሙ መኖራቸው የጠቆሙት አቶ ላቀ ህገ-ወጦችን ለማስተካከል የሁሉም ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌብነት ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ የሚደርሱትን ጥቆማዎች ተቀብሎ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ ብለዋል፡፡
የኢኮኖሚው መጫወቻ ሜዳ በማስተካከል ግብር ከፋዮች እኩል እንዲወዳደሩ ለማስቻል መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ከማዘመን ባሻገር ለአሰራር ልዕቀት ልዩ ትኩረት በመስጠት የአገልጋይ ስብዕናን በመላበስ የአገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋይ ተኮር፣ ተደራሽና ቀልጣፋ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሆነና በቀጣይም እንደሚሰራ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ተናግረዋል፡፡እናም ግብር መክፈል ትንሹ ሐገራዊ ኃላፊነት መሆኑን አምነን ግብር ለመሠወር የሚጥሩ ግብር ከፋዮችን ለሕግ በማጋለጥ የዜግነት ግዴታችን እንወጣ!!
"ግብራችን ለህልውናችን ለልማታችን"

19/08/2022

ኤክሳይዝ ታክስ የተመለከቱ ጥያቄዎችና ምላሾቻቸው
*****
ጥያቄ 1፡- በአዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቴምብር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተደንግጓል፡፡ ሁሉም የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ቴምብር ይመለከታቸዋል?
ምላሽ፡- ቴምብር በተመለከተ መመሪያ የማውጣት ስልጣን የተሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር በመሆኑ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡
ጥያቄ 2፡- የማምረቻ እና የመሸጫ ቦታ በሚለያይበት ጊዜ ምርቱን ለማጓዝ የወጣው የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ኤክሳይዝ ታክስ በሚሰላበት ወቅት ይካተታል ወይ?
ምላሽ፡- በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ምርት የትም ይሸጥ የትም የማስከፈያ ዋጋ የሚሰላው የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ ላይ በመመስረት ነው፡፡ ለምሳሌ ደብረብርሃን የተመረተ ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ምርት አዲስ አበባ ላይ ሲሸጥ የወጣው የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች ኤክሳይዝ ታክስ ሲሰላ አይካተቱም፡፡ ነገር ግን ሻጩ ለገዢው የሚሰጠው ደረሰኝ አንድ ስለሆነ የኤክሳይዝ ታክስ ለማስላት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች እንዲሁም ቫት ጨምሮ ጠቅላላ ዋጋውን ያስቀምጣል፡፡
ጥያቄ 3፡- ምርት ለመምረት የሚውል ግብዓት ተገዝቶ የተቀመጠ ከሆነና ኤክሳይዝ ታክስ የተከፈለበት ከሆነ ኤክሳይዝ ታክስ ተመላሽ ይደረጋል ወይ?
ምላሽ፡- ምርት ከተመረተ በኋላ ሊመለስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተገዝቶ መጋዘን ላይ ለተቀመጠ ዕቃ የኤክሳይዝ ታክስ ተመላሽ አይፈቀድም፡፡
ጥያቄ 4፡- ዊዝሆልዲንግ ኤክሳይዝ ታክስን ይመለከታል ወይ?
ምላሽ፡- አዎ፡፡ ትርፍ ከሌለ ስለሚመለስ እና የመጨረሻ ታክስ ስላልሆነ፡፡
ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info ይከታተሉ


The Ministry of Revenues is the body responsible for collecting revenue from domestic taxes.

Address

Fendika Square
Dangila
45Y7

Telephone

+251918618153

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fendika City Revenue posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Fendika City Revenue:

Share