05/09/2026
የዘንድሮው የ2018 ዓ/ም #የጷጉሜ ወር 5 ቀናቶች በተለያዩ ዝግጅቶችና ሁነቶች ይከባራሉ።
ነሀሴ 30/018(ዳንግላ ኮሚኒኬሽን)
የዘንድሮው የ2018 ዓ/ም የጷጉሜ ወር 5 ቀናቶች በተለያዩ ዝግጅቶችና ሁነቶች እንደሚከበሩ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር የዳንግላ ወረዳ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
- ነሀሴ 30/018(ዳንግላ ኮሚኒኬሽን)
የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ አቶ አለበል አባት እንደገለፁት የ2018 ዓመተ ምህረት የመጨረሻ ጳጉሜ ወር የብልጽግና መንግስት ያከናወናቸውን ፍሬያማ ስራዎችና ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች በተለያዩ ዝግጅቶች የምናስተውቅበት ነው ብለዋል።
መንግስት በሁሉም ዘርፍ ያስመዘገባቸውን በተለይም በስንዴ ምርት፣ በግብርና በሜካናይዜሽን፣ በአረጓዴ አሻራ እና በተለያዪ የመንግስት ኢኒሸቲቭ የልማት ስራዎችን ለማህበረሰቡ የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል።
በተለይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የመንግስት ሰራተኞችና አመራሩ ጋር በመሆን ጷጉሜ 01/13/018 ዓ/ም የምርታ ቀን፣ ጷጉሜ 02 የማንሰራራት ቀን፣ ጳጉሜ 03 የፅናት ቀን፣ ጳጉሜ 04 የህብር ቀን፣ ጷጉሜ 05 የነገ ቀን ተብለው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳና ሰዓት በተለያዩ ዝግጅቶችና በፓናል ውይይት እንዲሁም ሁነቶች እንደሚከበሩ አቶ አለበል አስታውቀዋል።
በመጨረሻም መጪው የጳጉሜ ወር አምስት ቀናት ለመላው የዳንግላ ወረዳ ማህበረሰብ ጳጉሜን በአንድነት፣ በፍቅር በህትማማችነትና በወንድማማችነት እንዲያሳለፉ ምኞታቸውን ገልፀዋል።