30/08/2026
ለሀገር በቀል የምግብ ዋስትና እና ለከተሞች ልማት የሚሆን አቅም የ'ሌማት ትሩፋት' እና የከተማ ግብርና!
ምግብን በራስ አቅም መሸፈንና የገበያ እጥረትን በዘላቂነት መቅረፍ የብልጽግናችን መሠረት ነው፤በሀገራችን የተጀመረው የ'ሌማት ትሩፋት' መርሐ-ግብር በዋናነት ወተት፣ እንቁላል፣ዓሳ ሥጋ እና ማር ከቅንጦትነት ወጥተው በትርፍነት ለእያንዳንዱ አባወራ እንዲደርሱ የማስቻል ትልቅ ራእይ አንግቦ እየሰራ ይገኛል።
ነዋሪዎች የራሳቸውን የምግብ ፍጆታ በራሳቸው እንዲሸፍኑ፣ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ፣ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀ የምግብ ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣የገበያ አቅርቦት እጥረትን የሚሞሉ ሞዴል አምራቾችና ተቋማት እንዲፈጠሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮም ነባር ስራዎችን በማስቀጠልና አዳዲስ አምራቾችን ወደ ስራ በማስገባት የመርሐ-ግብሩን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በግንባር ቀደምትነት እየሰራ ይገኛል።