06/09/2026
በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።
ደባርቅ፡ ጳጉሜን 01/2018 ዓ.ም(ሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን)
በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።
በወረዳው ከአሁን በፊትም በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬም በወረዳው በምስራቁ ቀጠና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የሚሆኑ ተጨማሪ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የደባርቅ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ሲጓዙበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል። የነበሩበትን የጥፋት መንገድ በመተው ወደ ኅብረተሰቡ እና ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ መወሰናቸውንም አስታውቀዋል።
ደባርቅ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን