Visit East Gojjam

Visit East Gojjam This page is dedicated to promote the diverse natural, historical & cultural heritages of East Gojjam

31/05/2026
28/05/2026

ዞኑ ያለውን የቱሪዝም ሀብት በተገቢው መንገድ በማልት አከባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ወ/ሮ ብርቄ ይዘንጋው
የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል ፣ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ
East Gojjam Communication

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች !! እንኳን ለ1447ኛው  ለኢድ አል-አድሀ/አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ ! በዓሉ የሰላም፥ የፍቅር፥ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች !!

እንኳን ለ1447ኛው ለኢድ አል-አድሀ/አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ !
በዓሉ የሰላም፥ የፍቅር፥ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መልካም በዓል !!!

17/05/2026

የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለአመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጠናቆ የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በስኬት አስተናግዷል።

@አሚኮ ደብረ ማርቆስ

የምስራቅ ጎጃም ዞን የወረዳዎች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር  በደብረ ወርቅ ከተማ መካሄድ ጀመረ።=============የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ከምስራቅ ጎጃም ዞን...
17/05/2026

የምስራቅ ጎጃም ዞን የወረዳዎች የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር በደብረ ወርቅ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
=============
የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ከምስራቅ ጎጃም ዞን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የወረዳዎች የእግር ኳስ ሻምፒዮና በደብረ ወርቅ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻ ውድድሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ብርቄ ይዘንጋው እንደገለጹት በዞናችን ብሎም በክልላችን በደረሰው የፀጥታ ችግር ምክንያት ባለፉት ለሁለት ዓመታት ተኩል ስፖርታዊ ውድድሮች ሳይደረጉ ቆይተዋል፤በመሆኑም አሁን ላይ በክልሉም ሆነ በዞኑ እየታየ ያለውን አንፃራዊ ሰላምን መሠረት በማድረግ ከጥር ወር ጀምሮ የተለያዮ ስፖርታዊ ውድድሮችን በማድረግ፣ በክልል ተሳታፊ በመሆን የአሸናፊ ዋንጫና ሽልማቶችን ለዞናችን ብሎም ለመምሪያችን በማምጣት መምሪያውን ከነበረበት መቀዛቀዝ እንዲወጣ አልመን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

ውድድሩ የዞናችን እግር ኳስ ፌደሬሽን እና የምስራቅ ጎጃም ባህል፣ ቱራዝምና ስፖርት መምሪያ በጋራ በመሆን ከዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር ተቀዛቅዞ ብሎም ተረስቶ የቆየውን የግር ኳስ ጨዋታ ለማነቃቃት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ወይዘሮ ብርቄ አስረድተዋል።

በውድድሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ወርቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ይበልጣል አበበ እንደገለጹት የስፖርት ዘርፉ ለሰላም ካለው ፋይዳ ባሻገር በማህበረሰቡ መካከል አንድነትን ፣ሰላምን ለመፍጠር ትልቅ ሚና አለውና ሁሉም ማህበረሰብ የስፖርት ዘርፍን ለማጠናከር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፣

የእግር ኳስ ስፖርት መዝናኛ ብቻ ሳይሆን አለማቀፋዊ ዕውቅናን የሚፈጥር ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያግዝ በመሆኑ ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትንና ዲሲፕሊን በተላበሰ መልኩ መጠናቀቅ እንደሚገባው ከንቲባው አስገንዝበዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ህበረትስራ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊናየእናርጅ እና ደብረ ወርቅ ከተማ አስተዳደር ደጋፊ አመራር አቶ ታረቀኝ ጀንበሬ በበኩላቸው ስፖርታዊ ውድድሩ ጤንነትን ወዳጅነትን ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ዲሲፕሊን በተሞላበት ሁኔታ በማጠናቀቅ ዓላማውን ማሳካት ይገባዋል ብለዋል።

Enarge communication info

12/05/2026

የጎጃሟ~~መርጡለ ማርያም
Blue nile press

 #የመልዕልተ አድባር  ቅዱስ ማርቆስ  ዓመታዊ  በዓልእንኳን ለቅዱስ  ማርቆስ  ዓመታዊ  በዓል አደረሳችሁ !
08/05/2026

#የመልዕልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ በዓል
እንኳን ለቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ !

 #እንኳን ለጀግኖች ለ85 ኛው ለጀግኖች፣ አርበኞች አባቶቻችን የድል በዓል የመታሰቢያ ቀን አደረሳቹሁ" ሚያዝያ 27።
05/05/2026

#እንኳን ለጀግኖች ለ85 ኛው ለጀግኖች፣ አርበኞች አባቶቻችን የድል በዓል የመታሰቢያ ቀን አደረሳቹሁ" ሚያዝያ 27።

3ኛው የምስራቅ ጎጃም ዞን የወንዶች የቮሊቦል ሻምፒዮና ውድድር በደ/ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው።‎************‎‎ሚያዝያ 27 /2018 ዓ/ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬ...
05/05/2026

3ኛው የምስራቅ ጎጃም ዞን የወንዶች የቮሊቦል ሻምፒዮና ውድድር በደ/ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ነው።
‎************

‎ሚያዝያ 27 /2018 ዓ/ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ): 3ኛው የምስራቅ ጎጃም ዞን የወንዶች የቮሊቦል ሻምፒዮና ውድድር በደ/ማርቆስ ከተማ የዞኑ የቮሊቦል ፌዴሬሽን ከዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመተባበር እየተካሄደ ነው።

‎በሻምፒዮን ውድድሩ ላይ የክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሓላፊ ወ/ሮ ብርቄ ይዘንጋው በዞኑም ብሎም በክልሉ በደረሰው የፀጥታ ችግር ምክንያት ባለፍት ሁለት አመታት ተኩል ስፖርታዊ ውድድሮች ተቀዛቅዘው መቆየታቸውን ጠቅሰው አሁን ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም ስፖርቱ ተመልሶ እንዲንሰራራ በዞናችን የተለያዮ ስፖርታዊ ውድድሮችን እያደረግ ነው ብለዋል።


‎በውድድሩ 7 ወረዳዎችና 1 ከተማ አስተዳደር እንደሚሳተፉ እና የውድድሩ አሸናፊዎች ዞኑን ወክለው ቀጣይ ለሚደረገው ክልላዊ ውድድር የሚሳተፉ መሆናቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ብርቄ ስፖርት ለሰላም ካለው ፋይዳ ባሻገር በማህበረሰባችን መካከል አንድነትንና ሰላምን ለመፍጠር ትልቅ ሚና ስለአለው ሁሉም ሰው ለስፖርት ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።


‎ስፖርት ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ከማጎልበት፣ ከማዝናናት እና የስፖርት አፍቃርያንን ከማነቃቃት ባለፈ ጤናን፣ ባህልንና ማህበራዊ አንድነትን በአንድ ጊዜ የሚያጠናክር ትልቅ ሳይንሳዊ ጥበብ በመሆኑ ለእድገቱ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

‎በአሁኑ ስዓት በመክፈቻ ውድድሩ ባሶሊበንና ስናን ወረዳዎች በመጫዎት ላይ ሲሆኑ ውድድሩ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 3/2018 የሚቆይ ይሆናል።

‎East Gojjam Zone Communication

ሚያዚያ በደብረ ማርቆስ የታሪክ፣የድልና የበዓላት ወር  ነው፡፡************ሚያዝያ 27/2018ዓ.ም(ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን)፡ በጎጃም በተለይም በደብረ ማርቆስ የሚያዝያ ወር አከባበር...
05/05/2026

ሚያዚያ በደብረ ማርቆስ የታሪክ፣የድልና የበዓላት ወር ነው፡፡
************
ሚያዝያ 27/2018ዓ.ም(ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን)፡ በጎጃም በተለይም በደብረ ማርቆስ የሚያዝያ ወር አከባበር ከሃይማኖታዊ ሥርዓቶች፣ ከታሪክና ከማኅበራዊ ትስስር ጋር የተቆራኘ ደመቅ ያለ ሁነት ነው፤ሚያዝያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እጅግ ከሚከበሩት ወራት አንዱ በመሆኑ፣ በታሪካዊቷ የደብረ ማርቆስ ከተማም ልዩ ድባብ አለው።

ሚያዚያ 30 የሚከበረውን የሚያዚያ ማርቆስ ክብረ በዓል አስመልክተው የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተስፋየ አእምሮ በሰጡት ማብራሪያ ሚያዚያ በደብረ ማርቆስ የታሪክ፣የድልና የበዓላት ወር ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

የሚያዝያ ማርቆስ ክብረ በዓልን በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የገለፁት መምሪያ ሃላፊው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሚያዝያን በማርቆስ በተለያዩ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉ ከሚያዝያ 27 እሰከ 30/ 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ መሆኑን የገለፁት መምሪያ ሃላፊው ክብረ በዓሉ ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ በተጨማሪ በፓናል ውይይት፣በባላዊ ፌስቲቫል፣ባላዊ እሴቶችና አልባሳትን እንዲሁም ባህላዊ ምግቦችን በማስተዋወቅ እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

እንግዶች ከሚያዝያ 27 ጀምሮ በመገኘት የበዓሉ ታዳሚ እንዲሆኑ መምሪያ ሃላፊው አቶ ተስፋየ መለዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መረጃዎችዉ የደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው

Address

Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit East Gojjam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Visit East Gojjam:

Share