East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህ ገጽ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገጽ ነው

05/09/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፍትሕ ሙዚየም በይፋ ተመርቆ ለጉብኝት ክፍት በሆነበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ 👇

"የአማራ ክልል የፍትሕ ሙዚየም ተቀዳሚ አላማዎች ታሪክን ጠብቆ ለማቆየት፣ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለቀጣይ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎች መነሻ ሆኖ ማገልገል ነው"

"ሙዚዬሙ ታሪክን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዓላማ ያደረገ ነው" የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደውበአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዘመናዊ መንገድ የተደራጀው  የፍት...
04/09/2026

"ሙዚዬሙ ታሪክን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዓላማ ያደረገ ነው" የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው

በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዘመናዊ መንገድ የተደራጀው የፍትሕ ሙዚየም የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት ተመርቆ ክፍት ኾኗል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የፍትሕ ሙዚዬሙ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የፍትሕ እና የዳኝነት ሥርዓቶችን የሚያስረዱ ሰነዶችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን ሰንዶ የያዘ ነው።

የፍትሕ ሙዚዬሙ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኑ የዘመናዊ ሥርዓት ድረስ በባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች መሠረት ተደርገው ሲሰጡ የኖሩት የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓት አጠቃላይ ሂደት በሚያሳይ መልኩ በዲጂታል ሥርዓት እና በሀርድ ኮፒ የተደራጀ መኾኑንም ገልጸዋል።

ከሌላ ቦታ የማይገኙ መረጃዎች ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ በሙዚዬሙ ተሠባሥበው ለሕዝብ ዕይታ ክፍት እንዲኾኑ መደረጋቸውንም ጠቁመዋል።

የሙዚየሙ ዓላማ በፍትሕ ዙሪያ ለሚደረጉ የሕግ ማሻሻያዎች፣ የአሠራር ሥርዓቶች ለጥናት እና ምርምር ግብዓት እንዲኾን ነው ብለዋል። ለተማሪዎች እና ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ስትራቴጅ ለመንደፍ እንደሚያገለግልም አንስተዋል።

የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት ታሪክን ጠብቆ በማቆየት ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዓላማ ያደረገ ስለመኾኑም አመላክተዋል። በየጊዜው የነበረው የፍትሕ ሥርዓት አንዱ የታሪካችን አካል በመኾኑ በሚገባ ጠብቆ ለማቆየት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ ዓየነ (ዶ.ር) ሙዚዬሙ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ታሪክ ውስጥ የነበረውን የሕግ እና የፍትሕ ሂደትን በአንድ ቦታ ማሳየት የሚችል ነው ብለዋል።

ሙዚዬሙ በዩኒቨርሲቲው ለሚማሩ የሕግ ተማሪዎች መረጃዎችን በሚፈልጉት መንገድ ለማግኘት ዋነኛ ግብዓት እንደሚኾንም ገልጸዋል።

"መሪዎች ተቋም ይገነባሉ ተቋማት ደግሞ ሀገር ይገነባሉ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያደራጀው ሙዚዬምም ለዚህ ማሳያ ኾኖ አግኝቸዋለሁ" ብለዋል። ለዚህም ለተቋሙ መሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።

በሙዚዬሙ ውስጥ ቀደምት የዳኝነት እና የፍትሕ አካላት ማቋቋሚያ ሕጎች፣ በተለያየ ወቅት የተወሰኑ ውሳኔዎች፣ ከፍትሕ ተቋማት ጋር የተያያዙ የተለያዩ ታሪካዊ መረጃዎች፣ ፎቶዎች እና አልባሳት ተደራጅተው እና ተሰንደው ይገኛሉ።
ነሀሴ 29/2018 ዓ/ም
የዘገበው አሚኮ ነው

04/09/2026

#አንኳር
"ሙዚዬሙ ታሪክን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ዓላማ ያደረገ ነው።"
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው

#ፍትሕ #ሰላም #ባሕርዳር #ኢትዮጵያ

04/09/2026
04/09/2026

#አንኳር

"የሙዚየሙ ዓላማ በፍትሕ ዙሪያ ለሚደረጉ የሕግ ማሻሻያዎች፣ የአሠራር ሥርዓቶች፣ ለጥናት እና ምርምር ግብዓት እንዲኾን ነው።"

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው

#አሚኮ

04/09/2026
"በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተደራጀው የፍትሕ ሙዚዬም የሕዝቡ የማንነቱ መገለጫ ኾኖ የሚያገለግል ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ጠቅላ...
04/09/2026

"በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተደራጀው የፍትሕ ሙዚዬም የሕዝቡ የማንነቱ መገለጫ ኾኖ የሚያገለግል ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያደራጀውን የፍትሕ ሙዚዬምን መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የኢኖቪሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሙዚዬሙ በሀገራችን እና በክልላችን የፍትሕ እና የፍርድ ሥርዓት አሥተዳደር ከተጀመረበት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን በግልጽ በሚያሳይ መልኩ የተደራጀ ነው ብለዋል።

ሙዚየሙ በሀገራችን የፍትሕ አሥተዳደር እና የፍርድ ቤቶች አሠራር ጋር በተያያዘ ለጥናት እና ምርምር መሠረት የሚኾን ስለመኾኑም ነው የተናገሩት።

ለቀጣዩ ትውልድም መነሻ መኾን የሚችል ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

የክልሉ ሕዝብ "በፍርድ ካጣኋት በቅሎዬ ያለ ፍርድ የሄደችው ጭብጦዬ ትቆረቁረኛለች" በሚል ብሂል የሚያምን እና ለሕግ እና ለፍትሕ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥ መኾኑን ተናግረዋል።

በዚህም በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተደራጀው ሙዚዬም ማኅበረሰቡ ለሕግ እና ለፍትሕ ያለውን የማንነቱ መገለጫ ኾኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል።

ሙዚዬሙን ለገነቡት፣ ላደራጁት እና መረጃዎችን ላሠባሠቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መሪዎች እና ባለሙያዎች ምሥጋና ይገባል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
ነሀሴ 29/2018 ዓ/ም
የዘገበው አሚኮ ነው።

Address

Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to East Gojjam Zone high court/የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት:

Shortcuts

Share