የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ

17/08/2026

የ11 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ የደፈረው ተከሳሽ ወጣት አወቀ ሙሉሰው አንዳርጌ በ14ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሰሹ የፈጸመውን የአስገድዶ መድፈር( በህጻናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብ ስጋ ድፍረት በደል) ወንጀል የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት የምርመራ መዝገቡን አጣርቶ የላከ ሲሆን የወረዳው አቃቢ ህግም መዝገቡን በመመርመር በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 627/1/ ላይ የተደነገገውን የወንጀል ድንጋጌ ተላልፎ የተገኘ በመሆኑ በአስገድዶ መድፈር (በህጻናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል) ወንጀል ክስ መስርቷል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነሀሴ 11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ያለውን የ14ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

የህግ የበላይነትንና ሰባዊ መብትን በማክበር እና ወንጀልን በጋራ በመከላከል ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ።‎*******‎ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም የምስራቅ ጎጃ...
07/08/2026

የህግ የበላይነትንና ሰባዊ መብትን በማክበር እና ወንጀልን በጋራ በመከላከል ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ።
‎*******
‎ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ።

‎የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ሃላፊ አቶ አበበ አወቀ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንዳሉት የህግ የበላይነትንና ሰባዊ መብትን በማክበር እና ወንጀልን በጋራ በመከላከል በዞኑ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎በዕለቱም የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

‎በውይይት መድረኩ ላይም የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ሓላፊ አቶ አበበ አወቀን ጨምሮ የዞን አቃቢ ህጎችና ባለሙያዎች፣ የወረዳ ፍትህ ሓፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።


28/07/2026

በ2018 በጀት ዓመት በፍትሐብሄር ጉዳዮች ፍትህ አስተዳደር በርካታ ተግባራት የተፈጸሙ እና መልካም አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
በፍትሐብሄር ጉዳዮች በቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ መልስና ሰበር መልስ ክርክሮች የመዛግብት የማጥራት ቅልጥፍናን 97.5% ለማድረስ በዕቅድ ተይዞ ብር 25 ቢሊየን 014 ሚሊየን 264 ሽህ 920.10 የያዙ 9 ሽህ 784 መዛግብት ቀርበው፣ 24 ቢሊየን 983 ሚሊየን 377 ሽህ 330.20 ብር የያዙ 9 ሽህ 651 መዛግብት ውሳኔ በመስጠት የማጥራት ምጣኔዉን በመዝገብ 98.64% መፈጸም ተችሏል፡፡
የቀጥታ ክስና መልስ ተከራክሮ የማሸነፍ አቅም 90.5% ለማድረስ ታቅዶ፤ ብር 26 ቢሊየን 478 ሚሊየን 200 ሽህ 584 ብር በያዙ 7 ሽህ 389 መዛግብት ላይ ክርክር ተደርጎ ብር 4 ቢሊየን 665 ሚሊየን 092 ሽህ 422 ብር የያዙ 3 ሽህ 254 መዛግብት በአሸናፊነት፤ብር 197 ሚሊየን 169 ሽህ 144 ብር የያዙ 381 መዛግብት በተሸናፊነት ተወስነዋል፡፡ አፈጻጸሙ በገንዘብ 96%፣ በመዝገብ 90% ነው፡፡
በሴቶች፣ በህጻናት፣ በወጣቶች፣ በአረጋውያንና በአካል ጉዳተኞች በፍትሐብሄር የቀጥታ ክስና መልስ ተከራክሮ የማሸነፍ አቅምን 90.5% ለመፈፀም በእቅድ ተይዞ ብር 592 ሚሊየን 991 ሽህ 277 ብር የያዙ 1 ሽህ 406 መዛግብት ቀርበዉ ብር 185 ሚሊየን 347 ሽህ 864 ብር የያዙ 598 መዛግብት በማሸነፍ፣ብር 20 ሚሊየን 239 ሽህ 150 የያዙ 35 መዛግብት በመሸነፍ ውሳኔ አግኝተዋል፡፡ አፈጻጸሙ በመዝገብ 94.47%፣ በገንዘብ 90.16% ነው፡፡
ለመንግስት ተቋማት ህግ ምክር አገልግሎትን 100% ለማከናወን በእቅድ ተይዞ 2 ቢሊየን 026 ሚሊየን 947 ሽህ 657 ብር የያዙ 4 ሽህ 208 ጉዳዮች ቀርበው ሁሉም በመከናወናቸዉ አፈፃፀሙ 100% ነው፡፡
የዉል ረቂቅ የመመርመር እና ረቂቅ ውልን የማዘጋጀት ስራዎችን 100% ለማከናወን በእቅድ ተይዞ 240 ቢሊየን 995 ሚሊየን 623 ሽህ 483 ብር የያዙ 8 ሽህ 454 ጉዳዮች የውል ረቂቅ መመርመር እና 444 ሚሊየን 370 ሽህ 628 ብር የያዙ 345 ጉዳዮች የውል ሰነድ ዝግጅት ቀርበዉ ሁሉም በመሰራታቸው አፈጻጸሙ 100% ነው፡፡
ጉዳዮችን በድርድር የመፍታት ምጣኔን 14% ለማድረስ ታቅዶ፣ብር 50 ቢሊየን 674 ሚሊየን 164 ሽህ 264 ብር የያዙ 16 ሽህ 099 መዛግብት ውስጥ ብር 2 ቢሊየን 211 ሚሊየን 241 ሽህ 567 ብር የያዙ 3,390 መዛግብት በድርድር ተቋጭቷል፡፡ አፈጻጸም በመዝገብ 21% በገንዘብ 4% ነው፡፡
የተወሰደን የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለማስመለስ የአፈጻጸም ክስ ከቀረበባቸው ጉዳዮች ውስጥ የማስፈጸም አቅምን 97% ለማድረስ በእቅድ ተይዞ በ4 ሽህ 043 መዛግብት ብር 1 ቢሊየን 680 ሚሊየን 314 ሽህ 533.70 የያዙ ጉዳዮች ተፈላጊ እዳ የነበረ ሲሆን ከ3 ሽህ 254 መዛግብት ብር 1 ቢሊየን 275 ሚሊየን 297 ሽህ 256.53 ገቢ ተደርጓል፡፡ ብር 12 ሚሊየን 683 ሽህ 761.62 የያዙ 61 መዛግብት ንብረት በመጥፋት የተዘጉ በመሆኑ አፈጻጸሙ በመዝገብ 98.16%፣ በገንዘብ 99.02% ለማድረስ ተችሏል፡፡
መንግስት በተከሰሳባቸው ጉዳዮች ብር 23 ቢሊየን 030 ሚሊየን 365 284 ሽህ ከያዙ 4 ሽህ 648 መዛግብት ውስጥ ብር 4 ቢሊየን 235 ሚሊየን 284 ሽህ 723 በያዙ 4 ሽህ 308 መዛግብት በማሸነፍ የመንግሰትን ንብረት ከምዝበራ ማዳን ተችሏል፡፡ ሌሎች የዞሩ፣ ክስ የተነሳ ወዘተ ናቸው፡፡
የአቤቱታ አቀባበል ውሳኔ አሰጣጥ እና የአቤቱታ ተፈጻሚነት ምጣኔን 98.5% ለማድረስ ታቅዶ፣ በፍትሐብሄር 6 ሽህ 290 ቀርቦ 6 ሽህ 246 ውሳኔ ያገኙ በመሆኑ አፈፃፀሙ 99.3% ነው፡፡
በይቅርታ ቦርድ እንዲታዩ 1,643 የይቅርታ ጉዳዮች ቀርበው 1,224 ለመስተዳድር ም/ቤት እንዲቀርብ በማድረግ በይቅርታ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡ ከ515 የፌዴራል ታራሚዎች 314 በይቅርታ ተፈተዋል፡፡
394,678 ሰነዶችን በጥራትና በፍጥነት በመመዝገብና በማረጋገጥ፣ 669,864 የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተናገድ 1,395,367,796.94 ብር ለመንግስት ገቢ ማድረግ ተችሏል፡፡
14 የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ቀርበው ተመዝግበዋል፡፡ ሁሉም በጥራትና በፍጥነት ስለተመዘገቡ አፈጻጸሙ 100% ነዉ፡፡
በክልሉ ተመዝግበው ከሚገኙ 482 ሲቪክ ማህበራት ውስጥ 457 ድጋፍና ክትትል ማድረግ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙም 94.81% ነው፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ክልል አቀፍ ም/ቤት የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም ክልል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ቦርድ ተቋቁሟል፡፡
የጥብቅና ፈቃድ ማሳደስ ከነበረባቸው 1,134 ውስጥ 1,060 ያሳደሱ ሲሆን ሌሎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ማሳደስ አልቻሉም ፤ በአዲስ ፈቃድ ያወጡ 71 ናቸው፡፡
የተመዘገቡትን ጠበቆች ድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራን 80% ለማድረስ ታቅዶ ከ1,134 ጠበቆች ውስጥ ለ1,028 የክትትል እና ድጋፍ የተደረገ በመሆኑ አፈፃፀሙ 90.65% ነው፡፡
አዲስ በወጡት ሁሉም ህጎች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ 100% ለመስራት ታቅዶ በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅ እና የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር፣ የማረሚያ ቤት ኮሚሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ እንዲሁም ስለ አስተዳደር ፍትህ እና ተያያዥ ጉዳዮች በአማራ ሚዲያ ኮሮፖሬሽንም በመቅረብም በቢሮው የበላይ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ለወንድ 879፣ ለሴት 127፣ ድምር 1,006 ለሚሆኑ ለማህብረሰብ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡
የሚወጡ መመሪያዎችን በዘላቂነት የመመርመር እና የመመዝገብ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችል 1 የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ ተዘጋጅቷል፡፡
በአስተዳደር ተቋማት የሚወጡ መመሪያዎችን ህጋዊነት በመመርመር ከተለያዩ ተቋማት የቀረቡ 141 መመሪያዎች ሁሉም ህጋዊነታቸዉ ተረጋግጦ የመመዝገብ ስራ ተሰርቷል፡፡ የተመዘገቡት ዌብሳይት ላይ ተጭነዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት አተገባበር ክልላዊ ሪፖርት ማዘጋጀት1 በዕቅድ ተይዞ 1 ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡
በሰው መነገድ ሰዎችን ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከልና ምላሽ መስጠትን 80% ለማድረስ ታቅዶ፤
የ2017 የፍልሰት ክልላዊ ጥምረት ቡድኖችን ሪፖርት በማደራጀት እና የ2018 ዓ/ም የክልሉን የትብብር ጥምረት እቅድ የማዘጋጀት፣
በየደረጃዉ ለሚመለከታቸዉ የፍልሰት ምክር ቤት፣ የትብብር ጥምረትና የስራ ቡድን አባል ተቋማት ማስገምገም እና ሰነዱን አደራጅቶ ለሚመለከታቸዉ አካላት የማድረስ ተግበባራት ተከናውኗል፡፡
የፍልሰት ማስተባበሪያ ምክር ቤት ማቋቋሚያና የትብብር ጥምረት የአሰራርና አደረጃጀት መወሰኛ ደንብ እንዲጸድቅ ክትትል እና ድጋፍ ተደርጓል፤
አዲስ በተፈጠረው የብሔራዊ የትብብር ጥምረት የቡድኖች አደረጃጀት አግባብ የክልሉን፣ የዞንና የሚትሮፖሊታንት ከተሞች የትብብር ጥምረት አደረጃጀቶችን የማደራጀት ስራተጀምሯል፡፡
ከአጋር ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ጋር በመተባበር በሰው የመነገድ እና በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ወንጀል ዙሪያ የሕግ ማብራሪያ፣ የክልላዊ ጥምረቱ የአሰራር አደረጃጀት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፤
የአስተዳደር ፍትሕን የማስተዋወቅ እና የማስረፅ ተግባራትን በተመለከተ
አዲስ በወጡት ሁሉም ህጎች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ 100% ለመስራት ታቅዶ በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅ እና የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር፣ የማረሚያ ቤት ኮሚሽንን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ወንድ 879፣ ሴት 127፣ ድምር 1,006 ለሚሆኑ አካላት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በአማራ ሚዲያ ኮሮፖሬሽን በመቅረብም በቢሮው የበላይ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ለማህብረሰቡ ስለ አስተዳደር ፍትህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡ አፈፃፀም 100% ነው፡፡
የሚወጡ መመሪያዎችን በዘላቂነት የመመርመር እና የመመዝገብ ተግባራትን ለመፈጸም የሚያስችል 1 የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ ተዘጋጅቷል፡፡
በአስተዳደር ተቋማት የሚወጡ መመሪያዎችን ህጋዊነት በመመርመር ምዝገባ ማካሄድ እና ዌብሳይት ላይ መጫንን 100%ለማድረስ ታቅዶ መመሪያዎች ለመመዝገብ የሚያስችል የባህር መዝገብ በማዘጋጀት ከተለያዩ ተቋማት የቀረቡ 141 መመሪያዎች ሁሉም ህጋዊነታቸዉ ተረጋግጦ የመመዝገብ ስራ ሰርተናል፡፡ የተመዘገቡትን ወደ ዌብሳይት ተጭነዋል፡፡

የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች

ተቋማዊ አደረጃጀትንና አሰራርን የሚያጠናክሩትንና የተጀመሩትን ህጎች እና አሰራሮች ፈጥኖ ማጠናቀቅ፤
ከተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎችን መስራት፤
መዛግብት ላይ የሚታዩ የውሳኔም ሆነ የክርክር ጥራት ማነስ ችግርን ማስተካከል፤
መዛግብት በድርድር የመቋጨት ምጣኔን ማሳደግ፤
ጠበቆች የፍትህ ስርአቱ አጋዥ እንድሆኑ የተጠናከረ የጠበቆች ማህበር አመራር ማደራጀትና ክትትል ማድረግ፤
መሶብ አንድ ማእከል ላይ መሰጠት ያለባቸዉን ተግባራት ለይተን ማስገባትና የገቡትንም ባግባቡ መከታተል፤
ሙያዊ ነጻነትን በመጠበቅ ተጠያቂነትን ማጠናከር፤
የአስተዳደር ፍትህን ዉጤታማነት እና ኮንስትራክሽን ዉል አስተዳደርን ክትትል ማድረግ፤
የመፈጸምና ማስፈጸም አቅምን ማሳደግ የሚችል የአቅም ግንባታ ስራወችን መስራት፤
በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር ጉዳዮች የሴቶችን፣ የህጻናትን፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያንን የፍትህ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የትኩረት መስክ በማድረግ አፈጻጸማችንን ማሳደግ ይኖርብናል፡፡
ልዩ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳች ላይ የተጠናከረ ልዩ አሰራር መከተል፣
የአቤቱታ አቀራረብ የውሳኔ አሰጣጥና የአፈፃፀሙን ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ የሚደረግበትን የአሰራር ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ፤
ለሙስናና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ የሆኑ የመንግሥት ተቋማትን በጥናት ለይቶ የድጋፍ፣ ክትትልና የቁጥጥር ሥራ መሥራት፤
የታችኛዉን መዋቅር አፈጻጸም ሊያሳድግ የሚያስችል ድጋፍና ክትትልን አጠናክሮ ማስቀጠል፤
የመረጃ አደራረስና ልውውጥ ቅልጥፍናና ጥራት ጉዳይ፤ እጅግ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ90 በላይ የህግ ማሻሻያዎች ተሰርተዋል።             አያሌው አባተ (ዶ/ር)********ሀምሌ 6/2018 ዓ.ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ):የአማራ ክልል...
13/07/2026

በበጀት ዓመቱ ከ90 በላይ የህግ ማሻሻያዎች ተሰርተዋል።
አያሌው አባተ (ዶ/ር)
********
ሀምሌ 6/2018 ዓ.ም (ምስራቅ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ):የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ በ 2018 በጀት ዓመት በቢሮው በተከናወኑ ተግባራትና በበጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከምስራቅ ጎጃም ዞንና በወረዳ ከሚገኙ አቃቢ ህጎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) እንደገለጹት የመድረኩ ዓላማ በበጀት ዓመቱ በፍትህ ቢሮው ታች ድረስ ባለው አደረጃጀት የተፈጸሙ ተግባራት ውይይት አድርጎ የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ብለዋል።

በተያዘው 2018 በጀት ዓመት የክልል ፍትህ ቢሮው በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የተናገሩት ምክትል ቢሮ ሀላፊው በበጀት ዓመቱ ከ90 በላይ የህግ ማሻሻያዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ህገ መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ማክበርና ማስከበር፣የወጡ ህጎችን ማስፈጸምና ተፈጻሚነታቸውን ማረጋገጥ፣ የክልሉን መንግስት የማማከርና የመንግስት እና ህዝብ መብትና ጥቅም ማስከበር የፍትህ ቢሮው ዋና ዋና ሀላፊነቶች አሉበት ያሉት አያሌው አባተ (ዶ/ር) ይህንን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣትና ልማትን ለማሳለጥ የሚያስችል እቅድ ታቅዶ ማከናወን መቻሉን አስገንዝበዋል።

በበጀት ዓመቱ የጥቅማጥም ጥያቄዎችን ጨምሮ 4 መመሪያዎችን በማዘጋጀት ማጽደቃቸውን ያወሱት ምክትል ቢሮ ሀላፊው ፣በኦዲት ዙሪያ 'አርአያነት ያለው ተቋም እንዲሆን እና ምቹ የስራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ በርካታ ስራዎች እንደተከናወኑ አስረድተዋል።

በወንጀል የተወሰን ውሳኔ በወቅቱ መፈጸም፣ በፍትሃብሄር ደረጃ የአፈጳጸም ክስ እንዲሁም ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በየትም ቦታ ነጻ ሁነው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ትኩረት የሚሹ መሆኑን ምክትል ቢሮ ሀላፊው አመላክተዋል።

ከህዝብ ጋር ካልሰራን ለውጥ ልናስመዘግብ አንችልም ያሉት አያሌው አባተ( ዶ/ር)ህዝቡ ያለበትን ችግር በቅርበት በመረዳትና መሰረታዊ ጥያቄዎቹን መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የምስራቅ ጎጃሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ አወቀ በበኩላቸው በክልሉ የተጠቀሱና በዞኑም የሚተገበሩ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተግባራትን በቅንጅትና በትብብር በመስራት የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚኘት ለማረጋገጥ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበውን ሪፖርት በፍትህ ቢሮ ምን ተሰራ የሚለውን እንድናውቅ አስችሎናል ብለው የሚወጡትን አዋጆች፣ መመሪያዎች መሬት እንዲነኩ ከማድረግአኳያ ክልሉ እንዴት ያይዋል?፣የባለሙያውን ጥቅማ ጥቅም ከማስከበር አኳያ ምን ላይ ነው ያለ? እና ሌሎችም ጥያቄዎችን አንስተዋል።

የባለሙያውን ክህሎት ለመገንባት ተከታታይነት ያለው ስልጠና መሰጠት እንደሚገባው ተሳታፊዎቹ ጨምረው አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ዘሪያ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ምላሽ በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫዎች ተመላክተዋል።

09/07/2026
የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም በማኔጀመንት ተገመገመ። ባህርዳር ፣ሐምሌ 1/2018 ዓም(ፍትሕ ቢሮ ) በበጀት ዓመቱ ቢሮው ዕቅድ  የተቀመጡ ግቦችን መሰረት ያደረጉ ዝርዝር ተግባራት የ...
09/07/2026

የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም በማኔጀመንት ተገመገመ።

ባህርዳር ፣ሐምሌ 1/2018 ዓም(ፍትሕ ቢሮ ) በበጀት ዓመቱ ቢሮው ዕቅድ የተቀመጡ ግቦችን መሰረት ያደረጉ ዝርዝር ተግባራት የተፈጸሙበትን እና የተደረሰበትን አፈጻጸም ከማኔጅመንት አባላት ጋር በዝርዝረ ገምግሟል።
በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው በበጀት ዓመቱ ቢሮው የተመራበት ዕቅድ ከወረዳ ጀምሮ ያለውን አፈጻጸም የተመለከተ ነው።

ቢሮው የመፈጸም አቅሙን ከማጠናከር አኳያ ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ፣በድስፕሊን በመምራት፣ተጠያቂነትን ስርዓት በማጠናከር፣ የተለያዬ ስልጠናዎች ለዐቃቢ-ሕግ እና የአስተዳደር ሰራተኛው እንዲያገኝ በማደረጉ፣ የሰው ኃይል ስምሪት መፈጸምና መመደብ መቻሉ እና ስራን እየገመገሙ መምራት መቻል ለውጤት እንዳበቁ ተገልጿል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለከተማ አስተዳደር ለክፍለ ከተማና ለቀበሌ አመራሮች  በሙስና ወንጀሎችና በመልካም አስተዳደር ችግሮ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ:::::::::::::::::::...
25/06/2026

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለከተማ አስተዳደር ለክፍለ ከተማና ለቀበሌ አመራሮች በሙስና ወንጀሎችና በመልካም አስተዳደር ችግሮ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ::
:::::::::::::::::::::
ሠኔ 17/2018 የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ፅ/ቤት በጋራ በአዘጋጁት መድረክ ከደብረማርቆስ ከተማ ለሁሉም የቀበሌ አመራርና ለሁሉም የክፍለ ከተማ አመራር በሙስና ወንጀሎችና በመልካምአስተዳደር ችግሮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል
በስልጠናዉም የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ኋላፊ አቶ አበበ አወቀ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተሾመ ዋለ የፍትህ መምሪያ የፀረ ሙስና የስራ ሂደት አስተባባሪና ባለሙያዎች ተገቢዉን ስልጠና በመስጠት ከታዳሚዎች የተነሳላቸዉን ጥያቄና ማብራሪያ ምላሽ በመስጠት ስልጠናዉ ተጠናቋል::

በመንግስት ተቋማት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።==================ሰኔ 16/2018 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ እና በጎዛም...
24/06/2026

በመንግስት ተቋማት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
==================
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ እና በጎዛምን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመንግስት ተቋማት የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን አስመልክቶ ለጎዛምን ወረዳ የመንግስት ተቋማት የስራ ቡድን መሪዋች ስልጠና ተሰጠ።
በመድረኩ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ አወቀ፣የጎዛምን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘላለም መንግስቴ ፣ የዞኑ ፍትህ መምሪያ የስራ ሂደት አስተባባሪዎችና የጎዛምን ወረዳ የተቋማት የስራ ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።
በስልጠናው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ አበበ አወቀ የሙስና ወንጀል ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሶስተኛ ሰው ለማስገኘት ታስቦ በመንግስት፣ በመንግስት የልማት ድርጅት እና በህዝባዊ ድርጅቶች ላይ የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን በመግለፅ በመንግስት እና ህዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
አቶ አበበ አያይዘውም የሙስና ወንጀልን ለመከላከልና ተፈፅሞም ሲገኝ አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ ረገድ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የጎዛምን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው ሙስናን ከመታገልና ከመግታት አንፃር በርካታ አካላት ድርሻ ያላቸው ቢሆንም ሙስናን የመታገል ሂደቱ መጀመር ያለበት ከራስ በመሆኑ የእኔ ድርሻ ምንድን ነው? ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ እና ልንቆጥብ ይገባል ብለዋል።
በሙስና ወንጀሎች ዙሪያ የተዘጋጀውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ለተሳታፊዋች ያቀረቡት የዞኑ ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ጉዳይ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ያለለት ሙኔ ወንጀሉ ከፍተኛ ችግር እየሆነ የመጣ ከመሆኑም በላይ የወንጀሉ አፈፃፀም እየረቀቀና ውስስብ እየሆነ መምጣቱ ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶችን ፈታኝ እያደረጋቸው ይገኛል ብለዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተለያዩ ጥያቄዋችን አንስተው የፍትህ ተቋማት የሙስና ወንጀለኞች ላይ በሚፈለገው ደረጃ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ እና ይህን መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

24/03/2026

በዞናችን በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈፃፀም በመንግሥት ጉዳዮች ላይ በተደረገ ድርድርና ክርክር ብር 9,633,630.41 ለመንግስት ገቢ ማድረግ ተችሏል። ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ገቢው በእጥፍ እንደጨመረ ያሳያል ። ለዚህ ለውጥ መመዝገብ ቁልፉ ነጥብ በየደረጃው ያሉ ዐቃብያነ ህጎች እና አመራሩ ተቀናጅተው መንቀሳቀሳቸው በመሆኑ በርቱ ሊባሉ ይገባል !!

Address

East Gojjam Zone
Debra Markos

Telephone

+251587711308

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category