East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debra Markos
  • East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

East Gojjam Zone Agriculture  Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ግብርና ከማምረት በላይ ነው!! Agriculture Is Beyond Production

ከ18ሺ ሄ/ር በላይ ማሳ በተለያዩ የመኸር ሰብሎች በዘር መሸፈኑን በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።‎‎የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ጌቴ አንደገለፁ...
21/08/2026

ከ18ሺ ሄ/ር በላይ ማሳ በተለያዩ የመኸር ሰብሎች በዘር መሸፈኑን በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።

‎የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ጌቴ አንደገለፁት በ2018/219 የምርት ዘመን 18ሺ 88 ሄ/ር ማሳ በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስከ አሁን 18ሺ 42.5 ሄ/ር ማሳ በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

‎የምርት ዘመኑን በዘር የመሸፈን እቅድ ለማሳካትና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እስከ አሁን ድረስ 34ሺ 97 ኩንታል ያህል ሰው ሰራሽ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል ።

‎በተጨማሪም 410ሺ 720 ሜትር ኪብ የሚሆን ተፈጥሮዊ የአፈር ማደበሪያ በማዘጋጀት ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ ኮምፖስት ወደ አርሶ አደሮች ማሳ አንዲበተን ተደረጓል።

‎ እንደ ወረዳ የሚጠበቀውን የምርት መጠን ለማግኘት የባለሙያ ምክረ ሀሳብን መሰረት ያደረገና ወቅታዊ የሆነ የአረም ስራ ፣ ተባይ የመከላከል ፣ ማዳበሪያ የመጨመርና የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ የመሰብሰብ ተግበር መከናወን አንዳለበት አሳስበዋል።

‎ የግብርና ባለሙያዎችም በቀበሌዎች በመንቀሳቀስ መያዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑንና ለሰብል ምርታማነት መሻሻል ትኩርት ሰጠው እየሰሩ እንደሆነ ተገልጿል።

‎ሀላፊው ጨምረው አንደተናገሩት " ከተረጅነት ወደ ምርታማነት" የሚለውን በራስ አቅም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

‎በመሆኑም በምርት ዘመኑ 1ሚሊዮን 111ሺ 511 ኩንታል ያህል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ዘላለም ገልፀዋል።

Woreda Communication

 #በምስራቅ ጎጃም ዞን #በተለያዩ ወረዳዎች  #ለ2019 በጀት ዓመት የቡናና ፍራፍሬ የችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የኘላስቲክ፣ ዘር የማፍሰስና መሠረተ ግንድ የማዘጋጅት ስራ ከፊ...
21/08/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በተለያዩ ወረዳዎች
#ለ2019 በጀት ዓመት የቡናና ፍራፍሬ የችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የኘላስቲክ፣ ዘር የማፍሰስና መሠረተ ግንድ የማዘጋጅት ስራ ከፊል ገፅታ በምስል።

 #በምስራቅ ጎጃም ዞን #በደጀን ወረዳ  #የትኖራ ቀበሌ #በክላስተር እየለማ ያለ የጤፍ ሰብል አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።
21/08/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በደጀን ወረዳ
#የትኖራ ቀበሌ
#በክላስተር እየለማ ያለ የጤፍ ሰብል አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የጢቅ ቀበሌ በ2018/19  የመኸር ምርጥ ዘመን በክላስተር የአሰራር ዘዴ እየለማ የሚገኝ የጤፍ ሰብል ቡቃያ
20/08/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የጢቅ ቀበሌ በ2018/19 የመኸር ምርጥ ዘመን በክላስተር የአሰራር ዘዴ እየለማ የሚገኝ የጤፍ ሰብል ቡቃያ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች በኩታ ገጠም አሰራር እየለማ የሚገኝ የሰብል ቡቃያ @ስናን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት
19/08/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በተለያዩ ቀበሌዎች በኩታ ገጠም አሰራር እየለማ የሚገኝ የሰብል ቡቃያ

@ስናን ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

 #ዘላቂ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ!!****************************የምስራቅ ጎጃም ዞን የማየቻክል ወረዳ አስተዳድር ከእርዳታ ጥገኝነት በመውጣት...
18/08/2026

#ዘላቂ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ!!
****************************
የምስራቅ ጎጃም ዞን የማየቻክል ወረዳ አስተዳድር ከእርዳታ ጥገኝነት በመውጣት የምግብ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ለማረጋገጥ የተጀመረው “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” ኢንሼቲቭ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅት እየተሰራ ነው።
የምግብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው አርሶ አደሩ ለገበያ የሚተርፍ ምርት በብቃት ማምረት፣ በገበያ ላይ በቂ ምርት ሲኖርና ሸማቹ ምግብን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ሲችል ሲሆንከዚህ በፊት እንደ ወረዳ ሳይለሙ የቆዩ መሬቶችንም ወደ ልማት በማስገባት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ሲሆን፣ የሚገኘው ምርት ለተፈናቃኞች፣ ለችግር ተጋላጭ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ይሆናል

 #በምስራቅ ጎጃም ዞን  #በባሶ ሊበን ወረዳ  #በልምጭም እና የዱግ ቀበሌዎች  #የሰፋፊ ክላስተር  የአሰራር ዘዴ የተዘራ  #የስንዴ ሰብል ቡቃያ አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።~~~~~~
18/08/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በባሶ ሊበን ወረዳ
#በልምጭም እና የዱግ ቀበሌዎች
#የሰፋፊ ክላስተር የአሰራር ዘዴ የተዘራ
#የስንዴ ሰብል ቡቃያ አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።
~~~~~~

 #በምስራቅ ጎጃም ዞን #በሸበል በረንታ ወረዳ #በሰፋፊ የኩታ ገጠም /ክላስተር/ አሰራር  #የጤፍ ሰብል ቡቃያ አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።
13/08/2026

#በምስራቅ ጎጃም ዞን
#በሸበል በረንታ ወረዳ
#በሰፋፊ የኩታ ገጠም /ክላስተር/ አሰራር
#የጤፍ ሰብል ቡቃያ አሁናዊ ከፊል ገፅታ በምስል።

በጎዛምን ወረዳ ግ/ፅ/ቤት ወይንማ ገራሞ ቀበሌ ኖራን 1/4ኛ ከዘር ጋር   መጠቀም @ጎዛምን ወረዳ ግ/ፅ/ቤት
13/08/2026

በጎዛምን ወረዳ ግ/ፅ/ቤት ወይንማ ገራሞ ቀበሌ ኖራን 1/4ኛ ከዘር ጋር መጠቀም

@ጎዛምን ወረዳ ግ/ፅ/ቤት

 #እ.ኤ.አ ከኦገስት 11 እስከ 20/2026 ነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ ትንበያ/////////// #በኦገስት የሁለተኛው አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መ...
11/08/2026

#እ.ኤ.አ ከኦገስት 11 እስከ 20/2026 ነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ ትንበያ
///////////
#በኦገስት የሁለተኛው አስር ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ይበልጥ እየተስፋፉና እየተጠናከሩ ይሄዳሉ፡፡
#ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛው፣ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው አህዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ።
#ስለሆነም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ በተለይም በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ #በተጨማሪም፣ በሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
#በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
#በሚቀጥሉት አስር ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከመካከለኛ እስከ ከባድ (ከ11-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
#በተጨማሪም በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በመካከለኛው፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

ምንጭ፡-
የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲቱት

Address

0587717275
Debra Markos
01

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to East Gojjam Zone Agriculture Department/የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ:

Shortcuts

Share