East Gojjam Zone Water And Energy Department

East Gojjam Zone Water And Energy Department (የምስራቅ ጎጃም ዞነ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ)

በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸውየአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና ...
02/09/2026

በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተጠናቀቀ።

በመድረኩ ማጠቃለያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሠላም፣ በልማት በመልካም አስተዳደር መስኮች የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች እና ከተማ አስተዳድሮች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚህም የምስራቅ ጎጃም እስተዳደር ዞን ፈተናን ወደ ድል በመየር ባደረገው ጥረት የአመቱ 3ኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ በአብክመ ውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ  ከተለያዩ  ዳሬክተሮች በተውጣጣ ቡድን ድጋፍ ተደረገለት።ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ የቢሮው ከፍተኛ ባለሙ...
30/07/2026

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ በአብክመ ውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ ከተለያዩ ዳሬክተሮች በተውጣጣ ቡድን ድጋፍ ተደረገለት።

ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ደብረማርቆስ

የቢሮው ከፍተኛ ባለሙያዎች እና ዳሬክተሮች የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፍሬው ካሤን ጨምሮ የዞን ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የዞኑን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ዝግጅትየክረምት ሥራዎች እቅድ አፈጻጸም ፣ የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በክልሉ በኤል-ኒኖ የሚከሰት የዝናብ እጥረት ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎችንና የማህበረሰብ ክፍሎች የሚወሠዱ እርምጃዎች ላይ ሰፊው ግምገማና ውይይት ተካሄደ።

የሙያተኞች ቡድን ከመምሪያው ያገኜውን ግበዓት በመያዝ የከዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና የምስራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ከሆኑት ከአቶ ተስፋየ በላይ ጋር በዘርፉ እስትራቴጅክ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

19/07/2026
17/07/2026
16/07/2026
በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሠሩ ተቋማት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረኤልያስ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ጽ/ቤት አስታወቀ።‎‎በ2018 የበጀት አመት በመንግስትና...
10/07/2026

በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የተሠሩ ተቋማት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረኤልያስ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ጽ/ቤት አስታወቀ።

‎በ2018 የበጀት አመት በመንግስትና በማህበረሠቡ ተሣትፎ 98 አነስተኛ የመጠጥ ውሃ ተቋማት እና 25 የባዮጋዝ ፕላንቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን የደብረኤልያስ ወረዳ ውሃና ኢነርጅ ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ አውራጃው ላቀ አስረድተዋል። ስራዎች የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑን ጨምሮ የዞኑ ካቤኔ አባላት፣ የወረዳው አመራር ፣የመንግስት ሰራተኞች እና በወረዳው የአበሻም ቀበሌ ነዋሪዎችተገኝተው ጎብኝተውታል።

‎ መረጃው የደብረኤልያስ ውሃና ኢነርጅ ጽ/አቤት ነው

የምስራቅ ጎጃም  ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ የ2018 በጀት አመት ጠቅላላ ስራዎችን ገመገመ። የዋና ዋና ስራወች አፈጻጸምም እንደሚከተለው ቀርቧል።በዞን አቅም የዲዛይን ስራ 4  ለመስራት ታቅ...
09/07/2026

የምስራቅ ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ የ2018 በጀት አመት ጠቅላላ ስራዎችን ገመገመ። የዋና ዋና ስራወች አፈጻጸምም እንደሚከተለው ቀርቧል።

በዞን አቅም የዲዛይን ስራ 4 ለመስራት ታቅዶ ክንውን 5 አፈጻጸም 125%
‎👉የመጠጥ ውሃ ግንባታ እቅድ 499 ክንውን 989 አፈጻጸም 198.14%
‎👉በከተማ አዲስ መስመር ዝርጋታ በኬ.ሜ እቅድ 49.77 ክንውን 44.933 አፈጻጸም 89.9%
‎አዲስበከተማ አዲስ ደንበኛ በቁጥር ከተማ እቅድ 4890 ክንውን 3030 አፈጻጸም 61.96%

‎👉የዞኑ የው ሽፋን 2018 የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን በጀት አመት መጨረሻ በዞን ደረጃ ከ48.7 % ወደ 57.08% ተጠቃሚ 1,537,457 ማድረስ ተችሏል
‎የውሃ ተቋማት ጥገና 3600 የተበላሹ የውሃ ተቋማትን ለመጠገን ታቅዶ ክንውን 4714 አፈጻጸም 130.9%
‎👉3,159,757 ኢንቨስትመንት ወጭ ለመመለስ ታቅዶ ክንውን 2,603,639.76 አፈጻጸም 82.4%
‎👉የውሃና ንጽህና ኮሚቴ ህጋዊ እውቅና መስጠት እቅድ 136 ክንውን 175 አፈጻጸም 128 %
‎👉የውሃ ህክምና 37880 የውሃ ህክምና ስራ ለመስራት ታቅዶ ክንውን 39253 አፈጻጸም 104%
‎👉1020 ባክቶሮሎጅካል ውሃ ጥራት ቀጥጥር ለማካሄድ ታቅዶ 1248 አፈጻጸም 122%
‎👉የተሸሻሉ ጭስ አልባ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎች ሥርጭት ዕቅድ 27,000 ክንውን 41,963 አፈጻጸም 155%
‎👉በቤተሰብ የባዩ ጋዝ ግንባታ ተጠቃሚ ማድረግ ዕቅድ 318 ክንውን 413 የግንባታ ስራ ተሰርቷል አፈጻጸም 126%፡፡
‎👉የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች እቅድ 522 ክንውን 804 አፈጻጸም 138%%

‎የመልካም አስተዳደር አፈታት እቅድ 17 ክንውን 11 አፈጻጸም 76.4%

‎ሀ በበጀት አመቱ የተፈቱ
‎1.ለገ ብርሃን (እናርጅ)
‎2.ርዘነብ (ደ/ኤልያስ)
‎3.ነቢ (አዋበል)
‎4.ትኖራ (ደጀን)
‎5.ራም (ጎዛምን)
‎ 6.ድጎጽዮን (ቢቡኝ
‎7.ማኑኤል (አማኑኤል )ከል ከተማ)
8.ከኮ‎ርክ (ባሶሊበን)
‎9. ውላ (ማቻክል)
‎ለ ችግራቸው በከፊል የተፈታ
1.‎ሃገረ ሰላም (ደጀን)
2.‎መጠያ (እናርጅ)
3.‎ገሰስ (እነብሴ ሳር ምድር)
‎ሐ ችግራቸው ያልተፈተ
1.‎የሰንበት (አዋባል)
‎ይል አቅርቦት ችግር ከመብራት ሃይል በመነጋር ሃይል ማቅረብ በሂደት ላይ ያለ
2.‎ወይራ (እነማይ)
‎ል አቅርቦት እና መስመር በጦርነቱ የወደመ ጀነሬተሩን ወደ ሶላር መቀየር መስመሩን መጠገን
3.‎ዲማ (እነማይ)
‎የሀይል አቅርቦት እና መስመር
‎ደነሬተሩን ወደ ሶላር መቀየር
4.‎.እነቆይ (ደባይ ጥላት ግን)
‎ኮትሮል ፓናል ቦርድ መግጠም
5.‎ጃማ (አነደድ)
‎የውሃ መስመሩን ማስተካከል

04/07/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ የህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው የስራ ኃላፊዎች አስታወቁ። በወረዳው በዱቄ ቀበሌ የተገነቡ ስድስት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችም ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

​የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብዙነህ አለሙ፣ የወረዳው የውሃና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዮት መሾቢያው እና ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች በዱቄ ቀበሌ የተገነቡትን 6 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችና በአርሶ አደሮች ቤት እየተዘጋጁ ያሉ የባዮ ጋዝ ፕሮጀክቶችን በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል።

​የአዋበል ወረዳ በአሁኑ ወቅት ለ25 የገጠር ቀበሌዎችና ለአንድ የከተማ ቀበሌ በድምሩ ለ26 ቀበሌዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት እያቀረበ ይገኛል።

​የወረዳው የውሃና ኢነርጂ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዮት መሾቢያው እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡን የተቀናጀ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት በተቀላጠፈና ፈጣን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው። ይህም ለህብረተሰቡ በቂና ዘላቂነት ያለው አቅርቦት በማረጋገጥ፣ ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመፍጠርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ታስቦ የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል።

​ኃላፊው አክለውም የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ከነበረበት 48 በመቶ ወደ 50 በመቶ ለማድረስ በበጀት ዓመቱ 31 የእጅ ውሃ ጉድጓዶች እንዲገነቡ መደረጉን ገልጸዋል። ለነዚህ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ፦ ​ከወረዳው በጀት 7 ሚሊዮን ብር፣ ​ከማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ​አንድ የእጅ ውሃ ጉድጓድ ደግሞ በቀይ መስቀል ማህበር ድጋፍ መገንባቱን አስረድተዋል። ​በዱቄ ቀበሌ የተገነባውና ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የውሃ ፕሮጀክት ብቻ ከ3 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ኃላፊው ጠቁመዋል።

​የአካባቢው ነዋሪዎችና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑት አቶ ጤናው ጓዴ እና አቶ ቢሰነብት ሙሉቀን በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ባለመኖሩ ምክንያት ረጅም ርቀት ተጉዘው ውሃ ለመቅዳት ይገደዱ እንደነበርና ይህም ጊዜና ጉልበታቸውን ያባክን እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ላይ ግን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦቱ በየአካባቢው በመዘጋጀቱ ጊዜና ጉልበታቸውን በአግባቡ ለሌላ የልማት ስራ ለማዋል እንደሚያግዛቸው በደስታ ገልጸዋል።

​የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብዙነህ አለሙ በበኩላቸው፤ የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ለማሳደግ በበጀት ዓመቱ 7 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ በተመረጡ ቀበሌዎች 31 የእጅ ጉድጓድ ውሃዎች ተገንብተው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አረጋግጠዋል።

​ መረጃው የአዋበል ወረዳ የመንበረ ኮሙዩኒኬሽን ነው

04/07/2026

Address

Debra Markos

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Water And Energy Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share