07/08/2026
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!"
በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ አስተዳደር በረዕቡ ገበያ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች በስጦታ ቤት ሰርቶ ለማስረከብ በረዕቡ ገበያ ከተማ 01 እና 02 ቀበሌዎች ውስጥ የቤት የግንባታ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ይህ የበጎነት ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የስናን ወረዳ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሽደብር በለጠ ተናግረዋል።
ሃላፊዋ በበጎ ተግባራት ላይ መሳተፍ የህሊና እርካታን የሚያጎናፅፍ ከመሆኑም በላይ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ አቅመ ደካሞችን ካለባቸው የመጠለያ እጦት ችግር መታደግ ነው ብለዋል።
ከተማችን ውስጥ በሚገኙ በሁለቱም ቀበሌዎች ላይ ለአቅመ ደካሞች በበጎ ፈቃደኞች በሚደረግ ድጋፍ አማካኝነት ቤት በመገንባት ለመስጠት እስከ አሁን ድረስ በእያንዳንቸው ቀበሌ 10 ክፍል ቤት የተገነባ ሲሆን በሁለቱ ቀበሌዎች በድምሩ 20 ክፍል ቤት መገንባቱን ገልፅው የግንባታ ስራው በሁለቱም ቀበሌዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀው ለዚህ በጎ ተግባር ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅበት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።
በበጎ ተግባሩ ላይ የወረዳ አመራሮች፣በጎ ፈቃደኞች፣የመንግስት ሰራተኞች፣ የቀበሌ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
መረጃው የስናን ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።