21/04/2023
Aschalew Adane ትህትናን የተላበሰ፣ ሀቀኛ፣ ሰው አክባሪ፣ ለስራ ትጉህ፣ ግልፅና ብልሹ አሰራሮችን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ፣ አመራርነትን በሙያዊ እና ፖለቲካዊ ብቃት እንጂ በጎጠኝነት የማያምን ቆራጥ አመራር መሆኑን ሁሉም የሚያምንበት ሃቅ ነው፡፡ በመሆኑም ፓርቲው በሰጠው ሹመት የከተማውን ሁለንተናዊ የመልማት ጥያቄዎች በተሻለ ደረጃ ምላሽ ያገኙ ዘንድ ጉልህ ሚና ሊወጡ የሚችሉ አመራር እንደመረጠ አምናለሁ፡፡ ቀጣይም በተሻለ ደረጃ አገሩንና ህዝቡን እንደሚያገለግል እምነቴ ከፍ ያለ ነው።
ምክንያቱም አስቻለው አዳነ
ከላይ እንደገለጽኩት ታታሪ፣ ታማኝ፣ ሃቀኛ፣ ስለእውነት የሚታገል፣ ሌብነትን አምርሮ የሚጠየፍ፣ ለሁሉም ሰው እኩል የሚታገል፣ አስተዋይ መሪ እና በየጊዜው አቅሙ እያደገ የመጣ በተለያዩ የስራ ሃላፊነት የሰራ በፍጥነት በስራ ታታሪነትና ታማኝነቱ እያደገ የመጣ የቁርጥ ቀን ልጅ ነውና።
መልካም የስራ ዘመን
ዜና ሹመት !
በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ ሹመት ሰጠ።
በዚህም መሠረት፦
አቶ አስቻለው አዳነ ሰሎሞን ከሚያዚያ 12/2015 ዓ.ም ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
አቶ አስቻለው አዳነ ሰሎሞን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በሳይኮሎጂ የትምህርት ዘርፍ ያጠናቀቁ ሲሆን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።
መረጃው በብልጽግና ፓርቲ የደብረማርቆስ ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ነው