የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የእናንተው ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ነው Like Share Invite ያድርጉ እናመሰግናለን
ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ፈጣሪ ይባርክ

ሸዋ የአባት ግቢ ሸዋ የእናት ማጀት‎ጥበበኛ አርበኛ የሚወለድበት ‎ያምርበታል በርኖስ ያምርበታል ኩታ‎ሸዋ በአደባባይ ወጣ ያለ ለታ።የሸዋ የጋራ ቤት ታሪካዊት ከተማ ደብረብርሃን ቡሔን በድምቀ...
18/08/2026

ሸዋ የአባት ግቢ ሸዋ የእናት ማጀት
‎ጥበበኛ አርበኛ የሚወለድበት
‎ያምርበታል በርኖስ ያምርበታል ኩታ
‎ሸዋ በአደባባይ ወጣ ያለ ለታ።

የሸዋ የጋራ ቤት ታሪካዊት ከተማ ደብረብርሃን ቡሔን በድምቀት አክብራለች።

የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 182ኛ ዓመት እና የእቴጌ ጣይቱ 186ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ በዓል በደብረ ታቦር በድምቀት ተከብሯል።  ~•~•~•~•
18/08/2026

የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 182ኛ ዓመት እና የእቴጌ ጣይቱ 186ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ በዓል በደብረ ታቦር በድምቀት ተከብሯል።

~•~•~•~•

የአማራ ፖሊስ ሰላምና ደኅንነትን በብቃት ለማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ አዛዡ አሳሰቡ፤ፖሊስ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የማስከበር፣ የወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራዎችን በጥራትና በብቃት ...
18/08/2026

የአማራ ፖሊስ ሰላምና ደኅንነትን በብቃት ለማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ አዛዡ አሳሰቡ፤

ፖሊስ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የማስከበር፣ የወንጀል መከላከልና የምርመራ ሥራዎችን በጥራትና በብቃት የመወጣት ታላቅ ኃላፊነት አለበት ሲሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ አሳስበዋል።

አዛዡ በዋና ጠቅላይ መምሪያው ሥር የሚገኙ የወንጀል መከላከል፣ የወንጀል ምርመራ፣ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያዎችን፣ እንዲሁም የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ቢሮዎችን በአካል በመገኘት ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም በየክፍሎቹ የተፈጠሩ ምቹና ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓቶችን አድንቀው፣ ፖሊስ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ከማስከበር ባለፈ ወንጀልን በመከላከልና የተፈጸሙ ወንጀሎችን በብቃት በመመርመር ታላቅ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ የተቋሙን አጠቃላይ የሪፎርም እንቅስቃሴ፣ የሕዝብ ግንኙነት ሚናና በቀጣይ የሚከናወኑ ሀገራዊ ተልዕኮዎችን መሠረት ያደረጉ ዋና ዋና ጉዳዮችንም በጉብኝታቸው ወቅት አንስተዋል።

የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የተቋሙን መልካም ገጽታ በመገንባት፣ የግዳጅ አፈጻጸምን፣ የአገልግሎት አሰጣጥንና ተቋማዊ ዕቅዶችን ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ የጎላ ሚና እየተወጣ መሆኑንም አዛዡ ገልጸዋል።

በተቋሙ ተወዳዳሪነትና የሥራ አቅም ላይ የሚያበረክቱ ሥራዎችም በተለይ በማርች ባንድና በኪነ-ጥበብ ቡድኑ በኩል እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን የማሟላት ሥራ መሠራቱንና በቀጣይ የበጀት ዓመትም አቅምን የሚያጎለብት የሙያ ሥልጠና እንደሚሰጥ አክለዋል።

በሕዝብና በፖሊስ መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥና የተቀናጀ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም አዛዡ አሳስበዋል። መረጃዎችን በጥራት፣ በፍጥነትና በተዓማኒነት ለሕዝብ ማድረስ እንዲሁም ሕዝባዊ አመኔታን አጠናክሮ ማስቀጠል የኮሙኒኬሽን ሥራው ቀዳሚ ተግባር መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅት የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ለኮሙኒኬሽን ዘርፉና ለሌሎች ጠቅላይ መምሪያዎች ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍና ትኩረት ምስጋና አቅርበዋል።

የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በበኩላቸው፤ የከፍተኛ አመራሩ የሥራ ጉብኝት ለክፍሉ አባላት ትልቅ የሞራል ጥንካሬ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋሙ ሕዝባዊ አመኔታውን አጠናክሮ ለመቀጠልና መረጃዎችን በጥራት ለሕዝብ ለማድረስ የጀመራቸውን ዘመናዊ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ አክለውም ተቋሙ ከኮሙኒኬሽን ሥራው ጎን ለጎን የወንጀል መከላከልና የሕግ ማስከበር ተግባራቱን በላቀ ቁርጠኝነት እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የወንጀል ስጋቶችን አስቀድሞ ለመግታት በሕብረተሰብ አቀፍ የፖሊስ አሠራር የታገዘ የመከላከል ሥራ መጠናከሩን ገልጸው፣ የተፈጸሙ ወንጀሎችንም በሳይንሳዊ አሠራርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሙያ ብቃትን በመጠቀም በጥራትና በፍጥነት የመመርመር አቅም እያደገ መሆኑንም አስረድተዋል።

ሕዝቡ ለፖሊስ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀረቡት ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ፤ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የማስከበርና የሕግ ማስከበር ሥራው በከፍተኛ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የደብረ ታቦር (የቡሄ)  በዓል  ዋዜማ በደብረ ብርሃን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ፤ለበዓሉ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ፣ተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት እና አማራ ባንክ የምስጋና እና የዕውቅ...
18/08/2026

የደብረ ታቦር (የቡሄ) በዓል ዋዜማ በደብረ ብርሃን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ፤

ለበዓሉ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ፣ተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት እና አማራ ባንክ የምስጋና እና የዕውቅና ሠርተፍኬት የተሰጣቸው ሲሆን፤በተመሳሳይ ተቋማት፣መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች አጋር አካላት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በመርሐ ግብሩ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣የከተማው ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ  የቡሄ  (ደብረ ታቦር) በዓል  በተለያዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከበረ፤በሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት...
18/08/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል በተለያዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከበረ፤

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሥራ መሪዎች፣የተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

18/08/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል በተለያዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች በድምቀት ተከበረ፤

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሥራ መሪዎች፣የተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል በድምቀት ተከበረበደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶቹን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ።የከተማዋ ምክትል ከን...
18/08/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል በድምቀት ተከበረ

በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶቹን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ።

የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ፤ ነሐሴ 12 ቀን ለአሁኗ ኢትዮጵያ መሰረት የጣሉ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ ብጡልና ፊታውራሪ ገበየሁ የልደት ቀን መሆኑን በማብራራት፣ ችቦ የመብራትና ሙልሙል ዳቦ የመስጠት ባህላዊ ስርዓቶች ትርጉም ላይ ተናግረው፣ ህብረተሰቡ የአባቶችን ታሪክ በመጠበቅ ኢትዮጵያዊ አንድነትን የማጠናከር ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

የከተማው ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተክለዮሃንስ ኃይለጊዮርጊስ፤ ታሪካዊ ስፍራዎች ላይ የሚከናወኑ አከባበሮች የቱሪዝም ሀብትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃጥበብ አባቡ የደብረ ታቦር በዓልን ሃይማኖታዊ ዳራ አብራርተው፣ ጅራፍ ማጮህ፣ ሙልሙል ዳቦና ሆያ ሆዬ ጨዋታዎች ኢትዮጵያዊ ሀገር በቀል እሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት መሥራች ተሼ ባላገሩ በበኩላቸው፤ የመከባበርና የመተሳሰብ እሴቶች ለትውልድ እንዲተላለፉ የሁሉንም ጥረት እንደሚሻ አስገንዝበዋል።

በመርሐ-ግብሩ የከተማው አመራሮች፣ አባት አርበኞችና እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ ተሼ ባላገሩ አስጎብኚ ድርጅትና አማራ ባንክ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!”​"ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማት...
18/08/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!”

​"ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል የደብረ ብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከከተማና ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ተወያይቷል።

​መድረኩ ሀገር በቀል ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት፣ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ እና ስጋቶችን በንቃት ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን፤ የውይይት መነሻ ጽሁፉ በከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ም/ኃላፊ በአቶ እሸቱ ፍቃዱ ቀርቧል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ​የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታጠቅ ገድለ አማኑኤል እንደተናገሩት፤ የሀገርን ሰላምና ልማት ለማወክ ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች የሚነሱ የጥፋት ሴራዎችን ከመቼውም በላይ በጋራ መመከት ያስፈልጋል።

አክለውም በክልሉ የሚታዩ የፀጥታና የኢኮኖሚ ጫናዎችን ተረድቶ የህዝብን ሰላም ለማስጠበቅ በንቃት መታገል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

​የደብረ ብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው በበኩላቸው፤ ሀገር የማፍረስ አጀንዳ ያላቸውና የውጭ ተልዕኮ የተቀበሉ ኃይሎችን አደጋ ለመቀልበስ የአመራሩ ግንባር ቀደም ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም የገጠመንን የሰላምና ፀጥታ ስጋት ለመቀልበስ የህዝብን አንድነት በማጠናከር ለሀገር ዘብ በመቆም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንሰዲፍን የልማት አርበኝነት እንዲረጋገጥ ማድረግ የወቅቱ የጋራ ትኩረታችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።

​ኃላፊው አያይዘውም፣ ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት ማረጋገጥ የሚቻለው ህዝብን ያሳተፈ አሰራር በመከተል፣ የህግ የበላይነትን በማስከበር እና አንድነትን በማጠናከር እንደሆነ ተናግረዋል።

​የስብሰባው ተሳታፊ አመራሮችም የቀረቡትን ሃሳቦች ወደ ተግባር በመቀየር፣ የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስና የተጋረጡ ስጋቶችን በጋራ ለመመከት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል።

ወጣቱ ትውልድ የጀግኖች አባቶችን ታሪክ ማከበር ብቻ ሳይሆን ሀገር የመውደድና ሉአላዊነት የማስከበር እሴቶቻቸውን በተጨባጭ መተግበር እንደሚገባው ተገለጸ​የእምዬ ምኒልክ 182ኛ ዓመት እና የእ...
18/08/2026

ወጣቱ ትውልድ የጀግኖች አባቶችን ታሪክ ማከበር ብቻ ሳይሆን ሀገር የመውደድና ሉአላዊነት የማስከበር እሴቶቻቸውን በተጨባጭ መተግበር እንደሚገባው ተገለጸ

​የእምዬ ምኒልክ 182ኛ ዓመት እና የእቴጌ ጣይቱ ብጡል 186ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ።

በደብረ ብርሃን ከተማ ጠባሴ ክፍለ ከተማ በአንጎለላ ቀበሌ "እንቁላል ኮሶ" በሚባለው ቦታ የእምዬ ምኒልክና የፊታውራሪ ገበየሁ 182ኛ ዓመት እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱ ብጡል 186ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከብሯል።

​በበዓሉ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዕለቱ ለዘመናት በታሪክ ተሸፍኖ እንዲኖር የተደረገ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን በትውልድ ቦታቸው በመገኘት ታሪካቸውን ማሰብ እና ማክበር መቻሉ ልዩ ስሜት የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።

​ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጥቁር ህዝቦች ላይ ተጭኖ የነበረውን የባርነት እና የግዞት ሰንሰለት በአድዋ ጦርነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሰበሩ ታላቅ መሪ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን፣ ሆስፒታሎችን፣ ባንኮችን፣ ፖስታ ቤቶችን፣ የባቡር መስመሮችንና ሌሎች በርካታ ዘመናዊ ተቋማትን በማስገባት የሀገር አንድነትና ሉአላዊነትን ያረጋገጡ ታላቅ መሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​በተመሳሳይ የዛሬ 186 ዓመት የተወለዱት እቴጌ ጣይቱ፣ በምክርና በጥበባቸው ለዛሬ ሴቶች አርአያና ተስፋ የሆነ ታሪክ የሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል። በተለይም በአድዋ ጦርነት ወቅት በነበራቸው ብልህ ስትራቴጂ፣ የጠላትን የመጠጥ ውሃ ምንጭ በመክበብና በማስጠማት ለድሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ እናት መሆናቸውን አስምረውበታል።

​እንዲሁም ፊታውራሪ ገበየሁ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ተሾመው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጦር ሚኒስትር በመሆን ሀገራቸውን ማገልገላቸውን ጠቅሰው፤ በጦር ሜዳ እስከ መጨረሻው ድረስ ለሀገራቸው ነፃነት ሲታገሉ ሕይወታቸውን የሰጡ ጀግና አርበኛ መሆናቸውን አስረድተዋል። በመሆኑም ወጣቱ ትውልድ የጀግኖች አባቶችን ታሪክ ማከበር ብቻ ሳይሆን፣ ከእነርሱ ሀገርን መውደድ፣ ሉአላዊነት ማስከበርና የህዝብ ፍቅርን ተምሮ በተጨባጭ መተግበር እንደሚገባው መልዕክት አስተላልፈዋል።

​"እንቁላል ኮሶ" ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የተወለዱበት ታሪካዊ ቦታ በመሆኑ፣ ይህ ስፍራ የነበረውን ታሪካዊ ትውስታ በመጠበቅ ለተመራማሪዎች፣ ለተማሪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን ይሰራል ያሉት ደግሞ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተክለዮሃንስ ኃይለጊዮርጊስ ናቸው።

​በዚህም ታሪካዊ መረጃዎችን በአግባቡ በማደራጀትና ሰነዶችን በማዘጋጀት የጎብኚዎች መረጃ ማዕከል ማቋቋም፣ የመንገድ እና የእግረኛ መስመሮችን በማሻሻል ከአካባቢው የተፈጥሮ እና ባህል ቱሪዝም ጋር ማስተራሰር፣ እንዲሁም የአካባቢውን ምርትና የእጅ ስራዎች በማስተዋወቅ ለወጣቶች የገቢ ምንጭ እና የስራ እድል መፍጠር የሚሉትን የቀጣይ ተግባራት ዘርዝረዋል።

​በተጨማሪም ወጣቶች የታሪክ ባለቤት መሆናቸውን በመገንዘብ ማንነታቸውንና የሀገር ፍቅራቸውን የሚያጎለብቱበትን አጋጣሚ መጠቀም እንዳለባቸው በመጠቆም፤ ቦታው በኢትዮጵያ የታሪክና የቱሪዝም ካርታ ላይ ጎልቶ እንዲወጣ ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ የታሪክ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

​በአንጎለላ ቀበሌ የተወለዱት አፄ ምኒልክ (ኃይለመለኮት) በህዝቡ ዘንድ ታላቅ ተወዳጅነትን ያተረፉ ንጉሥ እንደነበሩ በማስታወስ የጠባሴ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌታወይ ማሞ ንግግር አድርገዋል።

እምዬ ምኒልክ በዘመናቸው የኢትዮጵያን አንድነት ከመጠበቅ ባሻገር እንደ መኪና፣ ስልክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ባቡር፣ ዘመናዊ ትምህርት እና መንገድ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አክለውም ባርነትን በማስቀረትና በተለይም በታላቁ የአድዋ ድል የጣሊያንን ወራሪ ኃይል ድል በማድረግ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት መሆናቸውን ገልጸው፣ የእቴጌ ጣይቱንና የፊታውራሪ ገበየሁን ታሪክ በአጭሩ በመዳሰስ ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬን ጨምሮ አባት አርበኞች፣ተጋባዥ እንግዶች፣ወጣቶች፣ሴቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ታድመዋል።

የአማራ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸለመ።የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመታት  አፈፃፀም ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።...
17/08/2026

የአማራ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን 1ኛ ደረጃ በመውጣት ተሸለመ።

የብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመታት አፈፃፀም ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።

በበጀት አመቱ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ በአመቱ በፈርጅ አንድ አጠቃላይ ምዘና ከሁሉም ክልሎች የአማራ ክልል የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን በጣም ከፍተኛ (95.86) ውጤት በማምጣትና 1ኛ ደረጃ በመውጣት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) በጋራ መድረኩ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት የፓርቲውን የፖለቲካና የስነ ምግባር ጤንነት በመጠበቅ ብዙ ውጤቶች መገኘቱን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ ከማዕከል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን የፓርቲው መመሪያዎችና አሠራሮች እንዲሁም የሀገራችን የምርጫ ሕጎች እንዲከበሩ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል፡፡

የኢንስፔክሽን ግኝቶችን ለፓርቲው በማቅረብ የሚታዩ ግድፈቶችን እንዲያርም በማድረግ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ የቀረቡ አቤቱታዎችን በማጣራትና ምላሽ በመስጠት የአባላት መብት እንዲከበር መድረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ደስታ ገለጻ የኮሚሽኑን አቅም በመገንባት በርካታ ውጤቶች የተገኙ ቢሆንም ከተልዕኳችን አኳያ ብዙ መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበለዋል፡፡

የተገኙ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም አሁን የተገኘውን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም የኮሚሽኑ 3ኛው ዓመታዊ የእውቅና መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት፣ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የፌደራል ተቋማት የአደረጃጀት ጸሃፊና የኮሚሽኑ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ለዚህ ውጤት መሳካት ከክልል ጀምሮ እስከ ህብረት ያለው የኮሚሽን መዋቅር ባለቤት በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል።

"ጠንካራ ኮሚሽን ለጠንካራ ፓርቲ"

Address

Debre Birhan

Telephone

+251116812872

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share