የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን Debre Birhan City Admin CFRS

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን Debre Birhan City Admin CFRS

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን Debre Birhan City Admin CFRS ይህ ገፅ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ሲሆን ስለ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ የምንተነትንበት፣ ገለፃ የምናደርግበት፣ እርስዎም ሐሳብና አስተያየት በመስጠት የሚሳተፉበት ገፅ ነው፡፡

ይህ ገፅ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ቡድን ሲሆን ስለ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚተነተንበት፣ ገለፃ የምናደርግበት፣ እርስዎም የሚወያዩበትና የሚሳተፉበት ገፅ ነው፡፡

27/08/2026
10/08/2026
.....................የቀጠለ...................የዞንና ከተማ አስተዳደር የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪዎች በአፈፃፀሙና በእቅዱ ላይ በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎ...
24/07/2026

.....................የቀጠለ...................
የዞንና ከተማ አስተዳደር የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪዎች በአፈፃፀሙና በእቅዱ ላይ በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በመድረኩ ከሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ጋር ተያይዘው ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት አቶ አህመድ አደምና አቶ ሞላ ትዛዙ በሰጡት አቅጣጫ፣ በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ድክመቶችን በማረም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የምዝገባ ስራው በቀበሌ ደረጃ የሚካሄድ በመሆኑ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ባለሙያዎችን፣ የአስተባባሪና ቴክኒክ ኮሚቴዎችን፣ እንዲሁም አሳዋቂዎችን እና የክብር መዝገብ ሹሞችን የመፈጸም አቅም ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል። በመጨረሻም ህገወጥ አሰራሮችን በመከላከል፣ ትክክለኛ መረጃዎችን በመያዝ እና የህዝብ ተሳትፎን በማጎልበት የዞኑን ተልእኮ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁሉም የምዝገባ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀርቧል።

ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከዞን እና ሪጅዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር የ2018በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ20...
24/07/2026

የአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከዞን እና ሪጅዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር የ2018በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በzoom meeting አካሄደ፡፡
+++++++
(ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ደብረ ብርሃን)
የአብክመ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዋለ ቅዱስ በክልሉ ስር በሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና በሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ የተከናወኑ የምዝገባና ሌሎች ስራዎችን በስፋት የዳሰሰ ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።
በውይይቱ በzoom meeting መድረክ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ አበረታች ስኬቶችና የተከናወኑ መልካም ስራዎች በጥልቀት ተገምግመዋል። በዚህም መሰረት በተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ፣ በሰው ኃይል ስምሪት፣ በህብረተሰብ ግንዛቤ ፈጠራ፣ በጤና ተቋማት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስፋፋት፣ ክበባትና አድማጭ ቡድኖችን በማደራጀት እንዲሁም በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ መልካም አፈጻጸሞች መመዝገባቸው ተገልጿል። ይሁን እንጂ በአንዳንድ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የታዩ የአደረጃጀትና የክትትል መላላቶች፣ የወቅታዊ ምዝገባ ምጣኔ አነስተኛ መሆን፣ የምዝገባ መቆራረጥ፣ እንዲሁም በጋብቻ እና ፍቺ የምዝገባ ሽፋን ላይ የታዩ ዝቅተኛ አፈጻጸሞች ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ ክፍተቶች መሆናቸው ተለይቷል። በተጨማሪም የቀጥታ ምዝገባ በጀመሩባቸው አካባቢዎች የታብሌቶች የጥራት ደረጃ ውስንነት እና የኢንተርኔት መስመሮች መቆራረጥ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ተመላክቷል።
የ2019 በጀት ዓመት አሻጋሪ የልማት እቅድ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በጋራ መግባባት ጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጧል። በእቅዱ መሰረት በክልሉ ይከሰታል ተብሎ ከሚታሰበው ኩነቶች አንጻር በምዝገባ ስሌት መሰረት በመመዝገብ 100% የምስክር ወረቀት ለመስጠት ግብ ተጥሏል። የቀጥታ ምዝገባ ስርዓትን ማስፋፋትም በሁሉም ቀበሌዎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል። ለፈጻሚዎች የሚሰጡ ስልጠናዎችን ማጠናከር፣ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስፋፋት፣ የጤና ተቋማት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሰፋ ማድረግ እና ሁሉንም ተግባራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተደራሽ ማድረግ በዕቅዱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው።
........ይ......ቀ......ጥ............ላ......ል.

ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

22/07/2026

የሲቪልና ቤተሰብ የምዝገባ ቦታ
ሁለት ዓይነት የሲቪልና ቤተሰብ የምዝገባ ቦታዎች አሉ፡፡
እነዚህም
1. ኩነቶችን በተከሰቱበት ቦታ መመዝገብ (Registration by Place of Occurrence)
የሰዉ ልጆች በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜያዊነትም ይሁን ለዘለቂታዉ ለመኖር በመደበኛነት ይኖሩበት ከነበረዉ ቦታቸዉ ለቀዉ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ ኩነቶች ደግሞ አንድ ሰው ወደ ህይወት የሚገባበትና በህይወት ዘመኑ ውስጥ የሚያልፍባቸው ተፈጥሮአዊና ማህበረሰባዊ ክስተቶች በመሆናቸዉ ሰዎች በያሉበት ቦታ ሁሉ ይከሰታሉ፡፡ እነዚህን በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተፈጠሩ ኩነቶችን ለመመዝገብ ሰዎቹ ወደ መደበኛ መኖሪያ ቦታቸዉ መመለስ ሳይኖርባቸዉ ኩነቱ በተፈጠረበት አካባቢ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት የመመዝገብ ሂደት ኩነቶች በተፈጠሩበት ቦታ ምዝገባ (Registration by place of occurrence) ይባላል፡፡ ኩነቶችን በተከሰቱበት ቦታ ከሚመዘግቡ አገሮች ዉስጥ ህንድን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
2. በመደበኛ መኖሪያ ቦታ መመዝገብ (Registration by Place of Residence)
ይህ አመዘጋገብ ኩነቶች የትም ቦታ ይከሰቱ ወይም ይፈጠሩ ምዝገባዉ የሚካሄደዉ የኩነቱ ባለቤቶች (ኩነቱ የተከሰተላቸዉ ግለሰቦች) በመደበኛነት በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ የሲቪልና ቤተሰብን ምዝገባ ስርዓት ለመዘርጋት በወጣዉ ህግ አዋጅ ቁጥር 1370/2017 መሰረት የኩነቶች ምዝገባ ሚካሄደዉ የኩነቱ ባለቤቶች በመደበኛነት በሚኖሩበት ቦታ እና በተለየ ሁኔታ አንዳንድ ኩነቶች ከመደበኛ መኖሪያ ቦታ ዉጭ እንደሆነ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ይህ ማለት አንድ የትዉልድ ቦታዉ ጋምቤላ ከተማ የሆነ እና በመደበኛነት እየሰራ የሚኖርበት ቦታ ደግሞ ባህርዳር ከተማ የሆነ ሰው ልደቱን አስመዝገቦ የልደት የምስክር ወረቀት ማዉጣት ቢፈልግ ወደ ትዉልድ ቦታዉ ጋምቤላ መሄድ ሳይጠበቅበት ባህር ዳር በሚኖርበት ቀበሌ በሚገኝ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ጽ/ቤት የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ በመሄድ የልደት ምስክር ወረቀት ማዉጣት ይችላል፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

22/07/2026

ወላጆቻቸው የማይታወቁ ህጻናትን በፍርድ ቤት በተሰጠ የተንከባካቢነት/የአሳዳሪነት ማስረጃ አስመዝግቦ የምስክር ወረቀት መውሰድን በተመለከተ
************************************************
በፍርድ ቤት በተሰጠ የተንከባካቢነት ወይም የአሳዳሪነት ማስረጃ የተሰጠ ቢሆንም ወላጆቻቸው የማይታወቁ በመሆኑ የልደት የምስክር ወረቀት ለመስጠት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን አዋጅ 1370/2017 አንቀፅ 25 የህፃኑ ወላጆች የሌሉ እንደሆነ የህፃኑ አሳዳሪ ወይም ህፃኑን በመንከባከብ ላይ ያለ ሰው ልደቱን የማስመዝገብ ግዴታ አለበት በሚለው አንቀፅ መሰረት የፍርድ ቤት ውሳኔው ላይ በተቀመጠው የስም ቅደም ተከተል መሰረት ልደቱ ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት እንዲወስድ ይደረጋል፡፡ ልደት በተከሰተ በ90 ቀናትና ሌሎች ኩነቶች በተከሰቱ በ30 ቀናት ውስጥ በአቅራቢያ በሚገኝ የምዝገባ ጽ/ቤት በመሄድ በወቅቱ ያስመዝግቡ

22/07/2026

ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ማስመዝገብ ግዴታ መሆኑን ያውቃሉ?
= = = = = = = = =
ልደት ከተከሰተ እስከ 90 ቀናት/ ጋብቻ፣ ፍቺና ጉድፈቻ በተከሰቱ እስከ 30 ቀናት ውስጥ፣ ሞት በ50 ቀናት ውስጥ፤ በቀበሌ የክብር መዝገብ ሹም(ሥራ አስኪያጅ)ጽ/ቤት ያስመዝግቡ!!
* #በልደት ምዝገባ ወቅት መሟላት የሚገባቸው * #ቅድመ ሁኔታዎችና * #ደጋፊ ማስረጃዎች
 ቅድመ ሁኔታዎች፡-
1. የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት ወይም እናት አንዳቸው የልጃቸውን ልደትን ማስመዝገብ ይችላሉ(በአዋጅ ቁጥር 1370/2017 መሰረት የልደቱ አስመዝጋቢ ከወላጆቹ አንደ በሆነ ጊዜ በህግ አግባብ ለማስመዝገብ የሚያበቁ ማስረጃዎችን ማቅረብ አለበት፤)፡፡
2.አስመዝጋቢው ወላጅ ያልሆነ እንደሆነ ሞግዚት ወይም አሳዳሪ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ የአስመዝጋቢው ሰው ሙለ ስም፣ ከተመዝጋቢው ጋር ያለውን ዝምድና፣ ፆታ፣ የትውልድ ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት፣ የትውልድ ቦታ፣ መደበኛ መኖሪያ ቦታና ፊርማ ሊኖረው ይገባል፤
3. ከወላጆቹ አንዱ በህይወት የሌለ እንደሆነ በህይወት ያለው ወላጅ የሟች ወላጅን ህጋዊ የሞት ማስረጃ ሲያቀርብ ልደቱ ይመዘገባል፡፡
4. ችሎታ የሌላቸው ሰዎች በተንከባካቢዎቻቸው ወይም በአሳዳሪዎቻቸው አማካይነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
5. ልደት የሚመዘገበው በህይወት ለተወለደ ወይም በሕይወት ተወልዶ ወዲያውኑ ለሞተ ሲሆን ሞቶ የተወለደ ከሆነ ግን አይመዘገብም፡፡
6. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ምዝገባ አገልግሎት ፈላጊ ልደቱን ራሱ ማስመዝገብ አለበት፡፡
7. 18 ዓመት ሳይሞላቸው ልጅ የወለዱ ወላጆች የልጃቸውን ልደት ለማስመዝገብ ሲቀርቡ ከሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ ካለው ዝቅተኛ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ማንነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
8. ልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደ መሆን አለበት፡፡
9. ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ተመዝጋቢ ወላጆቹን በሚመለከት ቦታ ላይ መረጃውን ካስሞላ በኋላ የወላጅ ፊርማ ቦታ ላይ ሰረዝ (-) ምልክት በማድረግ ይታለፋል፡፡
 ደጋፊ ማስረጃዎች፤-
1. ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡
2. የህጻኑ አሳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የአሳዳሪነት ወይም የተንከባካቢነት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጥሎ የተገኘ ህፃንን ለማስመዝገብ የሚመጣ ፖሊስ ወይም አግባብ ያለው የመንግስት አካል ማንነቱን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
4. የልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ራዕያችን ሁሉም ኩነቶች ተመዝበው የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት ነው!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

22/07/2026

ለሁሉም ኩነት አስመዝጋቢዎች በሙሉ
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስራ ከልደት ጀምሮ እስከ ሞት ያሉ ኩነቶች የሚመዘገቡበት በመሆኑ በተለይ ለደህንነት ስራዎች ከምዝገባው የሚገኙ መረጃዎች ፋይዳቸው የጎላ ነው።
የምዝገባ ስራው በባህሪው ክትትልና ድጋፍ የሚፈልግ በመሆኑ ከከተማ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ታችኛው አደረጃጀት ያለው መዋቅር ለስራው ስኬት ጠንከር ያለ ድጋፍ እያደረገ የሚሰራ ይሆናል።
የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት ኩነቶች ሲከሰቱ ማስመዝገብ ከህዝቡ የሚጠበቅ ግዴታ ነውና ማስመዝገቡ ደግሞ ለህብረተሰቡ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባለፈ ለአገር እድገትም የሚጠቅም መሆኑን በመገንዘብ፤ ወሳኝ ኩነቶች ሲከሰቱ በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡
ያንብቡ!
መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ!
ራዕያችን ሁሉም ኩነቶች ተመዝበው የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት ነው!
ኩነትን በወቅቱ በማስመዝገብ ኃላፊነትዎን ይወጡ
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን

በ2018 በጀት ዓመት በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት 17,369 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን አስታወቀ ። ሰኔ 17/2018ዓ.ም...
25/06/2026

በ2018 በጀት ዓመት በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት 17,369 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን አስታወቀ ።
ሰኔ 17/2018ዓ.ም
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ አካሂዷል። በበጀት ዓመቱም 17,369 ዜጎችን የሲቪል ምዝገባ በመመዝገብ የዕድሜ ልክ የምስክር ወረቀት ባለቤት ማድረጉን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ገልፀዋል ።
የሰቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማቀድ፣ የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ዜጎች ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በፍትሕ አስተዳደር ቀልጣፋና ውጤታማ አሠራር እንዲኖር ለማስቻል የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የምዝገባ አፈፃፀሙ በበጀት አመቱ ለመመዝገብ ከታቀደው አኳያ ከፍተኛ ቢሆንም በአንዳንድ ክፍለ ከተሞች የታየው የወቅታዊ ምዝገባ አፈፃፀም ዝቅተኛ ሆኖ በመገኘቱ በቀጣይ ከተማ አስተዳደሩ በልዩነት ገምግሞ አስፈላጊውን ማስተካከያ እንደሚያደርግና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት ነጥብ መሆኑን ተናግረዋል ።
በምዝገባ አፈፃፀም በቅንጅታዊ ስራዎች ፣ በቴክኖሎጂ አመዘጋገብና በሌሎችም በዩኒሴፍ ድጋፍ በአጠቃላይ ለ648 ሚመለከታቸው የንድፈ ሃሳብና ተግባር ስልጠና መሰጠቱን ተገልፀዋል።
የተመዘገቡ ስኬቶችና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት በበጀት ዓመቱ ውስጥ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ኩነቶችን በትክክል በመመዝገብ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል የታየ ሲሆን፣ የተቀናጀ አሰራርን በመዘርጋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል። ይህም ከተማዋ ወደ ዘመናዊ የዲጂታል አሰራር ለምታደርገው ሽግግር ትልቅ እምርታ መሆኑ ተገልጿል። ከጤና ተቋማት፣ ከእድር አመራሮችና ከማህበረሰብ አንቀሳቃሾች ጋር የተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር ለዕቅዱ መሳካት በዋናነት የተጠቀሰ ጥንካሬ ነው።
በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለ103,042 ህብረተሰብ ግንዛቤ መፈጠሩን ያስታወቁት አቶ ሰለሞን ከተማ አስተዳደሩ ከፋና ሬድዮ ጣቢያ ጋር ውል በመግባት የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ መልዕክቶች ለከተማው ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን መሰራቱን ገልፀው ለቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
የአገልግሎት አሰጣጡ ከብልሹ አሰራር በፀዳ መንገድ እንዲሳለጥ ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ስራዎች በመከናወናቸው በበጀት ዓመቱ ለውጦች መታየታቸውን ጠቁመው በአዲሱ በጀት ዓመትም ክትትሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ቡድን መሪው አክለውም በበጀት ዓመት በሁሉም ኩነቶች የተጀመሩት ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን ገልፀው ከንቲባው ቃል በገቡት መሰረት የቀበሌ መዝጋቢ ባለሙያ ቅጥር እና ቁሳቁሶችን በማሟላት ሌሎች ለኦንላይን ምዝገባ የሚያግዙ በጀት በመመደብ ስራው እንዲፋጠን ያሳሳቡ ሲሆን ተሳታፊዎች በበኩላቸው የኦንላይን ምዝገባ ስራቸውን እንዲፋጠን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይ በጀት ዓመት ምዝገባውን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ያሉትን የአሰራር ክፍተቶች ለማረም የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

19/06/2026

ኩነቶችን በወቅቱ በማስመዝገብ ሃላፊነትዎን ይወጡ።

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን Debre Birhan City Admin CFRS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share