Amhara Region North Shoa Zone Road, Transport and Logistics Department

Amhara Region North Shoa Zone Road, Transport and Logistics Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Region North Shoa Zone Road, Transport and Logistics Department, Government Organization, North Shewa Debre Birhan, Debre Birhan.

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የሐምሌ ወር አፈጻጸምን ገመገመ።ደብረ ብርሃን፦ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ...
11/08/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የሐምሌ ወር አፈጻጸምን ገመገመ።

ደብረ ብርሃን፦ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ተቋማት ጋር በመሆን የሐምሌ ወር አፈጻጸሙን በዙም ሚቲንግ ገምግሟል።

መምሪያው በ90 ቀናት ውስጥ ለማከናወን ያቀዳቸውን መደበኛ ተግባራትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች የሐምሌ ወር አፈጻጸምን ገምግሟል።

በግምገማው የሐምሌ ወር ዋና ዋና ተግባራት በዝርዝር ቀርበው፣ የተገኙ ጥንካሬዎችና የታዩ እጥረቶች በመለየት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በግምገማው ወቅት በቀጣይ በትራንስፖርት ዘርፍ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ማጠናከር፣ መደበኛ ቁጥጥርን በማጠናከር ሕገወጥነትን መከላከል፣ ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።

የመናኸሪያ ስምሪትንና አገልግሎት አሰጣጥን እንዲሁም መሠረተ ልማትን ማሻሻልና ማዘመን፣ የድንገተኛ ተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎትን ማጠናከር እና ሁሉአቀፍ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ከመንገድ ዘርፍ አንጻርም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ከወዲሁ መጀመር፣ በሁሉም ዘርፍ ሕዝቡን ባለቤትና ተሳታፊ በማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠበቅ ያለ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

መድረኩን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ የመሩ ሲሆን፣ በመድረኩ የዞን ማኔጅመንት አባላት፣ የወረዳና ከተማ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የወረዳና ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።

የመንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አፈ...
30/07/2026

የመንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።

የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ከመምሪያው የማኔጅመንት አባላትና ጠቅላላ ሠራተኞች ጋር ገምግሟል።

​በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፎች የተከናወኑ አበይት ተግባራትን አስመልክቶ ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል።

ተሳታፊዎችም በውጤቶቹ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

​በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተመለከተው የተመዘገቡ ውጤቶች አብዛኞቹ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ አበይት ተግባራት በተሻለ ደረጃ መከናወናቸው ተገልጿል።

በሂደቱ የታዩ ጥንካሬዎች የተገመገሙ ሲሆን፣ የታዩ እጥረቶች ደግሞ በዝርዝር ተለይተዋል።

የታዩ እጥረቶችን በመቅረፍ በቀጣዩ የበጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ ተካተው ሊፈጸሙ የሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

​በመጨረሻም የመድረኩ መሪ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ በበጀት ዓመቱ ለተመዘገቡት በጎ ውጤቶች የሠራተኞቹን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

በቀጣይም የተለዩ እጥረቶችን በማረም የተሻለ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም በቁርጠኝነት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።(ሰሸመኮ)

በሰ/ሸዋ ዞን በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የማህበረሰቡን ህይወትና ልማት የሚታደገው  የታች ዘራም ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ...
26/07/2026

በሰ/ሸዋ ዞን በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የማህበረሰቡን ህይወትና ልማት የሚታደገው የታች ዘራም ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የታች ዘራም ቀበሌ የድልድይ ግንባታ ጥያቄ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ በ4 ሜትር ከፍታ፣ በ6 ሜትር ስፋት፣ በ32 ሜትር ጠቅላላ ርዝመትና 11ሜትር የውስጥ ርዝመት ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል።

የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ሀይሉ፣ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደመቀ ማሙሻ፣ምከትል አስተዳዳሪና የፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሸት የሺጥላና ሌሎች የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ግንባታው ተጎብኝቷል።

የድልድይ ግንባታው ፍጥነትና ጥራቱን ጠብቆ ለረጅም ዘመን ለመኪና፣ለሰውና ለእንስሳት መሸጋገሪያ እንዲያገለግል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የማህበረሰቡን ጥያቄ የመመለሰና ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ተሞክሮ በተግባር የታየበት ሆኗል።

ወረዳው ከሰላም ስራው ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን በማስቀጠል ለተሞክሮ የሚበቁ በርካታ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ድንቅ ታሪኮችን እያስመዘገበ ይገኛል።

"አዲሱ የተሽከርካሪ ታርጋ ህጋዊ አሰራርንና ደህንነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ ነው" ዶ/ር ጋሻው አወቀ(ዶ/ር)​******,​የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ በሀገር...
24/07/2026

"አዲሱ የተሽከርካሪ ታርጋ ህጋዊ አሰራርንና ደህንነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ ነው" ዶ/ር ጋሻው አወቀ(ዶ/ር)
​******,
​የአማራ ክልል መንገድ፣ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ቢሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን አዲስ የተሽከርካሪዎች ታርጋ ቅየራ አሰራር አስመልክቶ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማስፈጸሚያ መሠረታዊ አቅጣጫዎች ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።

​በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ጋሻው አወቀ እንደገለጹት፤ አዲሱ የታርጋ ቅየራ የምዝገባ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን የመንገድ ደኅንነትን፣ የትራንስፖርት ስምሪትን እና ቁጥጥርን ውጤታማ ለማድረግ የተቃኘ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡

​አዲሱ ሰሌዳ የሀሰተኛ ታርጋ ዝውውርን የሚያስቀር እና ወንጀልን ለመከላከልና ለመመርመር የሚያስችሉ የደህንነት መለያዎች ያሉት መሆኑን የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል። አክለውም አሰራሩ የትራፊክ አስተዳደርን፣ የመንገድ ላይ ቁጥጥርን እና የመረጃ አሰባሰብ ስርዓትን ግልጽና ዘመናዊ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

​በክልሉ ከ135 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚገኙ የጠቆሙት ዶ/ር ጋሻው፤ አሰራሩ ውጤታማ ይሆን ዘንድ አሽከርካሪዎች አዲሱን ታርጋ ከመውሰዳቸው በፊት አሮጌውን እንዲመልሱ አሳስበዋል። የታርጋ ስርጭቱ ግልጽና ህጋዊ አሰራርን የተከተለ እንዲሆን ለተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰራ ገልጸው፣ ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ተግባር ላይ በማዋል ሀላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

​በፌዴራል ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኘውን ይህን ሥልጠና በተመለከተ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አማካሪ አቶ አሰፋ አዲስ በበኩላቸው፤ መርሃ ግብሩ አገራዊ ቅርጽና ብሔራዊ ትርክት ያለው አዲስ የታርጋ ስርዓትን በክልሉ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው የኮድ አሰራር በየክልሉ የተከፋፈለና ለቴክኖሎጂ አሰራር ያልተመቸ እንደነበር ያብራሩት አማካሪው፤ አዲሱ አሰራር በመላ ሀገሪቱ ወጥና ተመሳሳይ ሰሌዳ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

​ከሰልጣኞች መካከል የቢሮው የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ወ/ሮ አሚነት ጀማል እንደገለጹት፤ ወጥ የሆነ የሰሌዳ አሰራር መዘርጋቱ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ያስቀራል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እና የተገልጋዩን ወጪና እንግልት ለመቀነስ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።

የመንገድ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አቅርቦትን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ የቀወት ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፅ/ቤት የትራንስፖርት አቅርቦቱን ለማሳደግ  ...
24/07/2026

የመንገድ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አቅርቦትን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የቀወት ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፅ/ቤት የትራንስፖርት አቅርቦቱን ለማሳደግ ቀበሌን ከወረዳ እና ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ የጠጠር መንገዶች እና የህዝ መናኸሪያ በጥገና እና በአዲስ ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አስታወቀ ።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደጀን ምትኬ እንደገለጹት የማህበረሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ አግባባዊ ምላሽ ለመስጠት ያስችል ዘንድ የመንገድ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፋን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው በበጀት አመቱ የተሻለ የስራ እንቅስቃሴ ማሳየት መቻላቸውን አስረድተዋል ።

ኃላፊው በመግለጫ ሀሳባቸው እንደተመላከተው ቀበሌን ከቀበሌ እንዲሁም ቀበሌን ከወረዳ በትራንስፖርት ለማገናኘት በተደረገው ጥረት በመንግስት የካፒታል በጀትና በህብረተሰብ ተሳትፎ 6.5 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድና በአባያ አጥርቀበሌ የሚገኘው ደረጃ 3 የህዝብ አገልግሎት መስጫ መናኸሪያ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ታውቋል።

ወረዳው የተለያዩ የግብርና ምርቶች የሚመረቱበት እና ወሳኝ የተፈጥሮ ሀብቶች የሚገኝበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ከተወሰኑ ቀበሌዎች በስተቀር በትራንስፖርት ተጠቃሚ ሳይሆኑ በመቆየታቸው ማህበረሰቡ ለእንግልት ተዳርጓል ያሉት ሀላፊው ይህንን ችግር ለማቃለል 5ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ወጭ በማድረግ ከወረዳው ወደ መንግስትና ወዠድ ቀበሌ እንዲሁም አያበር ቀበሌን የሚያገናኘውን 6.5 ኪ.ሜ መንገድ ጥገና እና አዲስ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ የአባያጥር መናኸሪያም በደረጃ3 አስፈላጊውን ጥገና ተደርጎ ወደስራ ገብቷል ሲሉ አብራርተዋል ።

አቶ ደጀን በማጠቃለያ ንግግራቸው ለዚህ ተግባር በሀሳብ በጉልበት እና በቁሳቁስ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ተጀምረው የተቋረጡ መንገዶችንና በአዲስ የሚገነቡ መንገዶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ ስለሆነ ማህበረሰቡ አጋዥ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል ።

የሰሜን ሸዋ ዞን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ስራዎችን በማቀናጀት ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ።​ደብረ ብርሃን፦ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ...
17/07/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ስራዎችን በማቀናጀት ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ።

​ደብረ ብርሃን፦ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የተከናወነው መዋቅራዊ ውሕደት፦

የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን እና የመንገድ ልማት ሥራዎችን ይበልጥ ለማቀናጀትና የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ማስቻሉን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ ገለጹ።

ኃላፊው በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችንና ያጋጠሙ ፈተናዎችን አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

​በበጀት ዓመቱ ከ1 ሺህ 7 መቶ 75 በላይ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን በዘመናዊ መንገድ በማሰማራት፣ ከ48 ሚሊዮን በላይ የህዝብ እና ከ55 ሚሊዮን በላይ የከተማ ታክሲ ተጠቃሚዎችን በድግግሞሽ ማጓጓዝ ተችሏል ብለዋል።

ከ15 በላይ መናኸሪያዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢ-ትኬት (e-ticketing) አገልግሎት እንዲጀምሩ የተደረገ ሲሆን፣ የቦሎ፣ የአሽከርካሪዎች ፈተና እና የባለቤትነት ዝውውር አገልግሎቶች በሲስተም ተደግፈው ተከናውነዋል ነው ያሉት ኃላፊው።

በትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎች ህግ ጥሰው በተገኙ 25 ሺህ 3 መቶ 17 ተሽከርካሪዎች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት የተጣለ ሲሆን፣ 1መቶ 25 ተሽከርካሪዎች ላይ የእገዳ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

9 መቶ 32 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ በሰው ኃይል፣ 4 መቶ 18 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር በማሽን የተጠገነ ሲሆን፣ 72 ኪሎ ሜትር አዲስ መንገድ ፣ 1 የኮንክሪት እና 3 የእግረኛ ተንጠልጠያ ድልድዮች ግንባታቸው መጠናቀቁን ኃላፊው ገልጸዋል።

ለመንገድ ግንባታና ጥገና ከ3 መቶ 57 ሚሊዮን ብር በላይ የሕዝብና የመንግሥት በጀት ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፣ መምሪያው ከአገልግሎቶች ከ1 መቶ 41 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

​በዓለም አቀፍ ግጭቶች ምክንያት የተከሰተው የነዳጅ እጥረት በማሽነሪዎች እና በትራንስፖርት ስምሪት ላይ ተጽዕኖ የፈጠረ ቢሆንም በልዩ ኮሚቴ አማካኝነት ሥራዎች እንዳይቆሙ ተደርጓል ብለዋል።

የጸጥታ ሁኔታ፡ በአካባቢው የነበረው የጸጥታ ችግር በስራዎች ላይ እንቅፋት ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሁኔታዎች ወደ ቀድሞ ይዟቸው እየተመለሱ ይገኛሉ ነው ያሉት ኃላፊው።

የሰሌዳ ህትመት እጥረትን ለመቅረፍ ከጎረቤት ዞኖች ሰሌዳዎችን በማምጣት ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ጥረት መደረጉ ተመላክቷል።

መምሪያው ከማህበራትና ባለድርሻ አካላት ጋር የትራንስፖርት ሥምሪትና ቅንጅታዊ አሠራርን ገመገመ።ደብረ ብርሃን፣ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርት...
13/07/2026

መምሪያው ከማህበራትና ባለድርሻ አካላት ጋር የትራንስፖርት ሥምሪትና ቅንጅታዊ አሠራርን ገመገመ።

ደብረ ብርሃን፣ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መምሪያ የትራንስፖርት ሥምሪትና ቅንጅታዊ አሠራርን ከትራንስፖርት ማህበራትና ባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።

የትራንስፖርት ሥምሪት፣ ቁጥጥርና ቅንጅታዊ ሥራዎች በዝርዝር ቀርበው በጥንካሬና በእጥረት ግምገማ ተደርጎባቸዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ቅንጅታዊ ሥራዎች በመጠናከራቸው መሻሻሎች መታየታቸው በጥሩ ጎን ተገምግሞ በተለይ በቀጣይ በየደረጃው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ማጠናከር፣ ከትርፍና ታሪፍ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ማረም፣ ቅንጅታዊ አሠራሮችን የበለጠ ማጠናከር፣ የትራንስፖርት ሥምሪቱን በጥብቅ ዲሲፕሊን መከታተል፣ በህገወጦች ላይ የተጠናከረ ክትትል በማድረግ አስተማሪ ርምጃ መውሠድና በሁሉም ሥራዎች ህዝቡ አጋዥና ተሣታፊ እንዲሆን ማድረግ በትኩረት ተይዘው መሠራት እንደሚገባቸው የመምሪያው ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ በሰጡት የአሰራር አቅጣጫ አስመርውባቸዋል።

በውይይቱ ላይ የህዝብ ትራንስፖርት ማህበራት ቦርድ አመራሮች፣ የኦፕሬሽን ሠራተኞች፣ የደብረ ብርሃን መናኸሪያ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

በ4ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር  የተሰራዉ አዲሱ መነሀሪያ ለአገልግሎት ክፍት ሆነበአብክመ ሰሜን ሸዋ  ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከ4ነጥብ ...
03/07/2026

በ4ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር የተሰራዉ አዲሱ መነሀሪያ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከ4ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደረረጎበት የተሰራዉ አዲሱ መነሀሪያ ስራ ጀምሯል።

ከመንግስት በጀት 3ሚሊዮን 402ሺ 6መቶ ብር ከፃድቃኔ ማርያም ገዳም 840ሺብር በድምሩ 4ሚሊዮን 242ሺ 6መቶ ብር ወጪ በማድረግ የተሰራ ሲሆን ከነባሩ መነሀሪያ በተሻለ መልኩ ብዙ መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ የወረዳዉ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ሸዋይርጋ ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊዉ ገለፃ አዲሱ መነሀሪያ ከ3ሺ ካሬ መሬት በላይ ስፋት ያለዉ እና የመነሀሪያ እስታንዳርድን መሰረት ተደርጎ የተሰራ ነዉ ብለዋል።

በሰ/ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ፅ/ቤት ዘመናዊ የመንገደኞች የጉዞ ትኬት ኢ-ትኬቲንግ አገልግሎት ማስጀመሪያና የመናኸሪያ አጠቃላይ ጥገና ምርቃ ፕሮግራ...
27/06/2026

በሰ/ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ፅ/ቤት ዘመናዊ የመንገደኞች የጉዞ ትኬት ኢ-ትኬቲንግ አገልግሎት ማስጀመሪያና የመናኸሪያ አጠቃላይ ጥገና ምርቃ ፕሮግራም ተካሄደ ።

የወረዳው መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ፅ/ቤት በፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት ለተሳፋሪዎች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና ከእንግልትና ላልተፈለገ ወጪ እንዳይዳረጉ የሚያደርግ ዘመናዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ የኢ-ቲኬቲንግ አሰራር አሰጀምረናል ብለው እስከ ዛሬ በመናኸሪያው ውስጥ የነበረውን የተለመደ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመቀየር ህብረተሰቡን ካሰበበት ባሰበው ስአት እንዲደርስ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ብለዋል ።

‎በፕሮግራሙ ላይም የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽዋመነ ሀይሌ : የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የ104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር ም/አዛዥና የትጥቅና ሎጀስቲክ ኃላፊ ኮ/ል ሲሳይ በሻህ ታድመውበታል ።

በጎልባና ቃፈሮ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ጫጫ፦ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አጠወመኮ)በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በጎልባና ቃፈሮ ቀበሌ የገጠር...
22/06/2026

በጎልባና ቃፈሮ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ጫጫ፦ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (አጠወመኮ)

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ ወረዳ በጎልባና ቃፈሮ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የገጠር ኮሪደር ልማቱ ከመሰረተ ልማት ባለፈ ዘመናዊ አኗኗርን ለማረጋገጥ የሚያስችል በተለይም የአርሶ አደሩን ኑሮ በተሻሻለ መንገድ በጤና ፣በግብርና እና በውሃ አስተሳስሮ ለማሳደግ እንደሚጠቅም ተገልጿል።

የመንገድ ስራው በተሻለ ጥራትና ፈጥነት እየተሰራ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ስራዎችን የወረዳው አስተባባሪ ኮምቴ እና የሚመለከታቸው አካላት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ስራ እየተደረገበት ይገኛል።

Address

North Shewa Debre Birhan
Debre Birhan
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region North Shoa Zone Road, Transport and Logistics Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share