Debre Birhan city Communication Affairs Office

Debre Birhan city Communication Affairs Office ይህ ገጽ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው

በደብረ ብርሃን  ከተማ  ሰክሰስ  ፕላስ ከሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ  ጋር በመተባበር የ5 ሚሊዮን ብር ዊልቸር ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ፤በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃ...
05/09/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ ሰክሰስ ፕላስ ከሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ጋር በመተባበር የ5 ሚሊዮን ብር ዊልቸር ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ አደረገ፤

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደተናገሩት፣በከተማው አካል ጉዳተኞች በማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተሰራው ሥራ ውጤታማ ነው ብለዋል።

​በተለይም አካል ጉዳተኞች ሰርተው ራሳቸውን እንዲችሉና እንዲለውጡ መስሪያና መሸጫ ቦታ በማመቻቸት፣የመኖሪያ ቤት በመስጠት፣ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በማቅረብ እንዲሁም በቅርበት ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በኩል ብዙዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል።

​በዕለቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የክልሉ ሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ጋር በመተባበር የተደረገው ድጋፍ
የመንቀሳቀስ ችግር ያለባቸውን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በመጠቆም ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ለአካል ጉዳተኞች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍንጭ ሰጥተዋል።

የሰክሰስፕላስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍሬውሁን መንገሻ በበኩላቸው፣ድርጅቱ ባላፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫዎች ለአካል ጉዳተኞች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታወቀዋል።

​ድርጅቱ በዋናነት በዊልቸር ድጋፍ፣በገቢ ማስገኛ፣በትምህርት ዕድልና ስፖንሰርሺፕ በመስጠት ከመንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ዛሬም በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች 5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት 100 ዊልቸር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

በአካል ጉዳተኞች ዘርፍ የሚታዩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም እና ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የአካል ጉዳተኞች ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ጥላሁን አስታውሰው፣አሁን ግን መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ተሳትፏቸውን የሚያረጋግጡ ስራዎች
እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

​የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች ዋጋቸው ውድ በመሆኑ በራሳቸው ገዝተው ለመጠቀም ለማይችሉ ወገኖች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፌዴሬሽኑ፣ከሰርከስ ፕላስ እና ከአማራ ክልል ሴቶችና ማህበረሰብ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የአማራ ክልል ሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ አክለው እንደገለጹት፣አካል ጉዳተኞች በማህበረሰቡ ዘንድ ባለው የተዛባ አመለካከት፣ የተደራሽነት እጥረት፣ የባለሙያና የተቋማት አሰራር ድክመቶች ምክንያት ለአካላዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠው እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የኢኮኖሚና የህክምና አገልግሎት እጥረ፣የመሰረተ ልማትና የተደራሽነት ችግር፣የትምህርትና የመረጃ ተደራሽነት እጥረት፣የህጎችና ስማምነቶች አፈፃጸም ክፍተት መኖሩን ጠቁመው፣በተለይም የእንቅስቃሴ ጉዳት ያለባቸው በርካታ ዜጎች በሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ እጥረት ከቤት መውጣት አቅቷቸው በጨለማ ውስጥ ለመኖር መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአካል ጉዳተኞችን ችግር የሚቀርፉ የፖሊሲ ሀሳቦች ከማመንጨት ባለፈ፣ የተደነገጉ አለም አቀፍ ስምምነቶች በክልሉ ተፈፃሚ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ተቋማዊ አሰራርን በማጠናከር፣ልዩ አገልግሎቶችን በማስፋፋት፣አካል ጉዳተኞችን በማብቃት ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል።

ሰክሰስ ፕላስ ለ100 ወገኖች የዊልቸር ድጋፍ በማድረጉ፣የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከማንም በላይ አካል ጉዳተኞችን ተጠጠቃሚ በማድረጉ ምስጋና አቅርበው፣የዕለቱ ዕድለኞችም የተሰጣቸውን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተለያየ ምክንያት የመንቀሳቀስ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን በመግለጽ፣ከዚህ በኋላ የተሰጣቸውን ዊልቸር ተጠቅመው እንደሚንቀሳቀሱ አመልክተዋል።

05/09/2026
በኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን "በበጎነት" በሚል መሪ ሀሳብ ለሀበሻ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።በኢትዮ ቴሌኮም የማዕ...
05/09/2026

በኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን "በበጎነት" በሚል መሪ ሀሳብ ለሀበሻ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን የኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ አንተነህ ፋንታሁነኝ እንደተናገሩት፣ "በቀጣይ አዲስ ዲጅታልና ከዚያም ባሻገር" በሚል የ3 ዓመት ስትራቴጅ ቀርፆ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

እንደ ሀገር የቴሌ ኮሙንኬሽን ዘርፉን በማዘመን የደንበኞች ኑሮ ቀላል ከማድረግ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ባላቸው ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ጠንካራ ሥራ እየሰራ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ማህበራዊ ዘርፎችን በመደገፍና በማዘመን፣ በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ማለትም በአርንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት፣ የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው የነገ ተሰፋዎች የፅህፈት መሣሪያዎችን በመደገፍ እና በሌሎችም ዘርፎች እየተሳተፈ ነው፤ ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለግብርና እና ለአካባቢ ጥበቃ 492 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጎ እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አንተነህ፤ የጳጉሜ ቀናትን "በበጎነት "ስያሜ አድርገ ላለፉት በርካታ ዓመታት እየሰራን እንገኛለ ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ብቻ 75 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጎ በሁሉም መዳረሻዎቹ በ50 ቦታዎች ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አውስተዋል።

ስለተደረገው ድጋፍ የድርጅቱ አመራሮችና አባቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአሁኑ ሰዓት የመርጃ ልማት ድርጅቱ 300 ለሚሆኑ በቋሚነት፣ 1ሺ 500 በተመላላሽ፣ ለ 150 ቤት ለቤት በድምሩ ለ1ሺ 950 አርጋውያንንና ምስኪኖች ዘርፈ ብዙ ድጋፍና እንክብካቤ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የሪጅኑ ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመርጃ ልማት ድርጀቱ አመራሮችና አርጋውያን ተገኝተዋል።

ሰሜን ሸዋ ኮሙኒኬሽን

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግ...
05/09/2026

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤

​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በባህርዳር ከተማ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

​በልምድ ልዉዉጥ መድረኩ የተገኙት የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ እንደገለጹት፤ የአማራ ክልል የሀገራችን የቱሪዝም የስበት ማዕከልና ከራሱ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ትልቅ ሀብት ያለው ክልል ነው።

በባሕር ዳር ከተማ ተዘዋውረን የተመለከትናቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ጸጋዎች ለሀገራችን የወደፊት የቱሪዝም እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የባህርዳር በለዉጥ ላይ ነች የከተማዋ የለዉጥ ጉዞም የብልጽግና ጉዟችን ዋነኛ ማሳያ ምልክት ነዉ ብለዋል።

​ሃላፊዉ ክልሉ ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ አሁን ትኩረቱን ልማት ላይ ማድረጉን በቆይታቸው መታዘባቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በጋራ እንደሚሠሩ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ በበኩላቸው፤ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ሚዲያው ዋነኛ መሳሪያ ነዉ። ከሀረሪ ክልል ጋር የነበረውን የቆየ መልካም ግንኙነት እና የተግባራት አፈጻጸም ልምድ በመካፈልና በማዳበር፣ ለክልላችን እንዲሁም ለሀገር ገጽታ ግንባታ የሚጠቅሙ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። የልምድ ልውውጡም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና የነበሩ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ በበኩላቸው፤ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ ከምናሳካባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ዲጂታል ኮሙኒኬሽን መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህ የሚመጥን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አሁናዊ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፤ የልምድ ልውውጡ በቀጣይ በጋራ ለሚከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች ጠንካራ መሠረት የጣለ ነውም ብለዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የትምህርት ቤቶች የገጽታ ማሻሻል ተግባራትየደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎች ምቹ ለማድረግ...
04/09/2026

በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ የትምህርት ቤቶች የገጽታ ማሻሻል ተግባራት

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማከናወኑን አስታወቀ።

በትምህርት ቤቶች የተከናወኑ የማሻሻያ ሥራዎች ከህንፃና የመሰረተ ልማት ግንባታ በዘለለ የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በደብረ ብርሃን ከተማ የጠባሴ መድኃኔዓለም አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ታደሰ በላቸው ተናግረዋል።

የፊት አውራሪ ገበየሁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ማሙየ ደምሴ በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ 5 የአይሲቲ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ይህም የበለጠ ዘመናዊና ጥራት ያለው የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

​የትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለማሻሻል የተከናወኑት ተግባራት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በተደረገ ቅንጅትና በማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ዉጤታማ መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ ብዙነህ ገልጸዋል።

በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎች ጥገናና ዕድሳት፣ የወንበር አቅርቦት እንዲሁም የጥቁር ሰሌዳ የማዘጋጀት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

​ለቅድመ -መደበኛ ትምህርት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ ደረጃቸውን የጠበቁ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 13 ማድረስ መቻሉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በተገኘ የ75 ኮምፒውተሮች ድጋፍ 4 ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቀ የኮምፒውተር አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

​በከተማው የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ቁጥር 132 ማድረስ መቻሉን አስረድተዋል።

አሚኮ

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ያስተላለፉት መልእክት፦የሕብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አም...
04/09/2026

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ያስተላለፉት መልእክት፦

የሕብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አምራች ሕብረተሰብ መገንባት ነው።

ኢትዮጵያን ላለፉት 100 ዓመታት ያገለገለውን፣ ታሪካዊ ወረት እና ዘመናዊ አቅምን ያጣመረውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ ተመልክተናል።

የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው። ተቋሙም በወረርሽኝ ልየታ፣ በበሽታ ክትትልና ምላሽ፣ በላብራቶሪ፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን እና በጤና ስጋት ዝግጁነት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በጥንካሬ እየደገፈ ይገኛል።

በክልሎች የድንገተኛ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋሙና የሪፈራል ላብራቶሪዎችን ማስፋፋቱ የሀገሪቱን የጤና ዝግጁነት አቅም እያጠናከረ ያለ ወሳኝ ተግባር ነው።

በቀጣይም የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም የጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል በመሆን ዓለም አቀፍ ሚናውን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት እያደረገ ነው።

የትላንትን ታሪክ ጠብቆ፣ ዛሬን በዘመናዊነት ዋጅቶ፣ ወደ ነገ የሚገሰግስ እንደዚህ ያለ ተቋምን መደገፍና ማጠናከር ለነገ የማንለው ተግባር ነው። ኢንስቲትዩቱ የሀገርን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ አቅም በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የመገጭ ግድብ ጎበኙ።ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማ...
04/09/2026

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የመገጭ ግድብ ጎበኙ።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት ለአካባቢው አርሶ አደሮች ከፍተኛ የኾነ ለመስኖ ልማት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ከመስኖ ልማት ባለፈም የጎንደር ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግርን በዘላቂነት እንደሚፈታ ተስፋ የተጣለበት ትልቅ ፕሮጄክት ነው።

ለዓመታት ሲጓተት የነበረው እና የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ የኖረው መገጭ ግድብ አሁን ላይ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል። ፕሮጄክቱ 94 በመቶ አፈጻጸም ላይ መድረሱም ተገልጿል።

ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚኾን ይጠበቃል። አሁን ላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይዟል።

አሚኮ

ወንጀልን በጋራ በመከላከል አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፤ በደብረ ብርሃን፤ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም (ደብመኮ):...
04/09/2026

ወንጀልን በጋራ በመከላከል አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፤

በደብረ ብርሃን፤ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም (ደብመኮ):-የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ዙሪያ በአገልግሎት ዘርፍ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ ከተሳተፉት መካከል ለዘላቂ ሰላም መጽናት ሕዝብና መንግሥት በጋራ መሥራት እንዳለበት፣በፀጥታ መዋቅሩ ስም የሚነግዱና ሕዝብ የሚያንገላቱትን የፀጥታ አካላት ሥርዓት ማስያዝ እንደሚያሻ፣በጫትና በሺሻ ሥራ ላይ ለተሰማሩ አማራጭ የሥራ መስክ ሊፈለግላቸው እንደሚገባ አንስተዋል።

የሕዝብን ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጡና በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን ተከታትሎ ለፀጥታ አካላት መረጃ መስጠት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር ሳይሆን የሁሉም ሰው ኃላፊነት እንደሆነም አመልክተዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ወንጀልን በጋራ በመከላከል አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ መሳፍንት ተስፋው እንደተናገሩት፣አሁን ያለው የከተማው ሰላም የበርካታ የፀጥታ መዋቅር አባላት የሕይወት፣የአካል እና የንብረት ዋጋ የተከፈለበት ድምር ውጤት ቢሆንም፣በሂደቱ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ የጎለ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በመስዋዕትነት የመጣውን የከተማው ሰላም በማጽናት ልማቱን ለማስቀጠል የከተማው ሕዝብ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለወንጀል መንስዔ የሚሆኑ መጤና ከማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ያፈነገጡ ድርጊቶች በመከላከል በኩል ነዋሪው ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ መሥራቱን መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ፖሊስ ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅቶ በወሰደው ስምሪት በርካታ በእገታና በዘረፋ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት በህግ ጥላ ስር አውሎ ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የደብረ ብርሃን ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ገብረመስቀል ቦጋለ አስታውቀዋል።

ወደፊትም ሕዝብና የፀጥታ አካላት ተባብረው ከሰሩ ወንጀል በቀላሉ በመቆጣጠር የኅብረተሰቡን ደህንነት በአስተማማኝ በማስጠበቅ ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንችላለን ብለዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በማጠቃለያው እንዲነሱት፣ደብረ ብርሃን ተፈናቃዮችን ጨምሮ ከ4 መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ የሚኖርበት ከተማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለልማት መፋጠን፣ለባህል ብዝሃነት መዳበር ፋይዳው ከፍተኛ ቢሆንም፣በዚያው ልክ ለወንጀል መበራከት መንስዔ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል።

ይህን መልካም ዕድል አጣጥሞና በነቃ የሕዝብ ተሳትፎ የከተማው ሰላም ማረጋገጥ ለአፍታም ችላ የማይባል አንገብጋቢ ቀዳሚ ሥራ እንደሆነ አብራርተዋል።

ለከተማው አስተማማኝ ሰላም መረጋገጥ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች የተሰማሩ የንግዱ ማኅበረሰብ ፀጉረ ልውጦችን ተከታትሎ መረጃ በመስጠትና ተናቦ በመሥራት በኩል በማንም የማይተካ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው በማሳሰብ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ለቀጣይ ሥራቸው መሻሻል በግብዓትነት የሚጠቅሙ መሆናቸውን ጠቁመው፣በመንግሥት በኩል የድርሻውን ወስዶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ቸሻየር ኢትዮጵያ ከሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ለአካል ጉዳተኞች እና ለልጆቻቸው ከ545 ሺህ በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፤የቸሻየር ኢትዮጵያ ፕ...
04/09/2026

ቸሻየር ኢትዮጵያ ከሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ለአካል ጉዳተኞች እና ለልጆቻቸው ከ545 ሺህ በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ፤

የቸሻየር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ኦፊሰር አቶ መሐመድ ደምሰው እንደገለጹት፣በደብረ ብርሃን ከተማ በዘላቂ ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ለታቀፉ ተጠቃሚዎች 545 ሺህ 400 ብር ግምት ያለው የዊልቸር እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

በዕለቱ 184 ሺህ ብር ወጪ የሆነበት 220 ደርዘን ደብተርና 1 ሺህ 100 እስክርቢቶ ለ220 ልጆች የተሰጠ ሲሆን፣365 ሺህ ብር ወጪ የሆነበት 9 ዊልቸር ለተጠቃሚዎች መሰራጨቱን አቶ መሐመድ አክለው ገልጸዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ሴቶች ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ በቀለ ገብረመድህን በበኩላቸው፣በከተማው ውስጥ የሚኖሩ አካል ጉዳተኞች በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

መምሪያቸው እስከታችኛው የአስተዳደር እርከን ባለው መዋቅር በራሱ ከሚያከናውነው በተጨማሪ ከአጋር ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከጊዜያዊ የድጋፍ አገልግሎት በተጨማሪ በዘላቂነት እንዲቋቋሙና ሕይወታቸውን እንዲመሩ ሰፊ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣የዛሬው ድጋፍም የሥራቸው አንድ አካል እንደሆነ አመልክተዋል።

የመምሪያው የማኅበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያና መከታተያ ቡድን መሪ አቶ ለማ ደምሴ አክለው እንደገለጹት፣የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያደገ እንዲሄድ በየጉዳት ዓይነቱ ተደራጅተው እንዲቀሳቀሱ በማድረግና ከልማት ድርጅቶች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለይም ከቸሻየር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 161 አካል ጉዳተኞች በዘላቂ ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ታቅፈው ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

ዛሬም በፕሮጀክቱ የታቀፉ ቤተሰቦች 220 ልጆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ደርዘን ደብተር፣5 እስክርቢቶ እንዲሁም የመንቀሳቀሻ ችግር ላለባቸው ወገኖች ዊልቸር ድጋፍ መደረጉን አመልክተዋል።

ከድጋፍ ርክክቡ በኋላ ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት፣በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው፣ችግራቸውን በትክክል የሚያቃልል እንደሆነ መስክረዋል።ወደፊትም ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረው በመጠየቅ ድርጅቱን አመስግነዋል።

Address

Amhara
Debre Birhan
251

Telephone

2516813085

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Birhan city Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Debre Birhan city Communication Affairs Office:

Shortcuts

Share