National Veterinary Institute

National Veterinary Institute NVI stands on firm foundation with its experience of at least 5 decades and optimal capacity to prod

የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኢንስቲትዩቱን ጎበኙታህሳስ 27፣ 2018 ዓ.ም ፤ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ...
07/01/2026

የኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ
ታህሳስ 27፣ 2018 ዓ.ም ፤ የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ባደረጉት የመስክ ምልከታ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ፣ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ኮሬ እና የኮሚቴዉ አባላት ተገኝተዋል።

አላማዉም ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ከማሳካት አንጻር ከክትባት እና መድሃኒት ምርት አኳያ አሁን ያለበትን የአፈፃፀም ደረጃ በመገምገም የተገኙ ጠንካራና ደካማ ጎን እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ግብረ መልስ በመስጠት የተቋሙ አገልግሎት ፈጣን ፣ቀልጣፋ ለማድረግ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ገልጸዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ ስለ ክትባትና መድኃኒት አመራረት ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫና የፖሊሲ ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮቸን እንዲሁም፣ ስለተቋሙ አጠቃላይ እንቅስቃሴና ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ ለቋሚ ኮሚቴዉ አብራርተዋል፡፡ ተቋሙ በቀጣይ አሁን እየሰራ ካለበት ቴክኖሎጂ ወደ ተሻለ ለማሸጋገርና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል መልካም የአመራረት ዘዴን መስፈርት የሚያሟላ ዘመናዊ የእንሰሳት ክትባት ማምረቻ ላብራቶሪ እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ የማምረቻ ማሽኖችን ለመተካት የአዋጪነት ጥናት ለማከናወን በሂደት ላይ መሆኑን ገልፀዉ ኢንስቲትዩቱ ከሚያገኘው ትርፍና የውጭ ምንዛሪ ባሻገር ለእንስሳት ሀብት ልማት ዘረፉ የሚያበረክተዉ አስተዋጾ በእጅጉ የጎላና ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ አመራረቱንና የምርቶቹን ግብይት ለማሳለጥና በፖሊሲ ሊደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የግብይትና ሽያጭ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ታደሰ ከክትባት እና መድሃኒት ግብይት ጋር በተያያዘ ያለዉን ነባራዊ ሁኔታ አቅርበዋል።

ቋሚ ኮሚቴዉ ከሰራተኛዉ ጋር በምርት ስራዎች፣ በሰዉ ሃብት አስተዳደር እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት አካሂዶ አመራሩና ሰራተኛዉ የኢንስቲትዩቱን ራዕይ ለማሳካት በቅርበት ለችግሮች መፍትሄ በማስቀመጥ የኢንስቲትዩቱን ትርፋማነት ሊያስቀጥል እንደሚገባ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በአደይአበባ ታምሩ

Chinese delegation visits the National Veterinary Institute (NVI) on 16 Dec, 2025 for discussion on collaboration for po...
22/12/2025

Chinese delegation visits the National Veterinary Institute (NVI) on 16 Dec, 2025 for discussion on collaboration for potential tech transfer on biotechnological products development & manufacturing. The visit is sideline event of collaborative initiative of the China-Africa forum on Science & Technology for African Animal Resources Management organized by mission of PRC, AU-IBAR & AU-PANVAC.

29/11/2025
ኢንስቲትዩቱ ለአፍሪካ የአስቸኳይ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የደስታ በሽታ ክትባት / Rinderpest (RP) Vaccine አምርቶ አስረከበ----------------------------------...
18/11/2025

ኢንስቲትዩቱ ለአፍሪካ የአስቸኳይ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የደስታ በሽታ ክትባት / Rinderpest (RP) Vaccine አምርቶ አስረከበ
-----------------------------------------------------------------
የአለም የእንሰሳት ጤና ድርጅት /WOAH ለአፍሪካ አህጉር የአስቸኳይ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የደስታ በሽታ ክትባት / Rinderpest (RP) Vaccine በፓን አፍሪካ የእንሰሳት ክትባት ቁጥጥር ማዕከል (AU-PANVAC) በሚገኘው ማከማቻ ለማስቀመጥ በወጣው አለም አቀፍ ጨረታ የብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በመመረጡና ክትባቱን አምርቶ እንዲያቀርብ በጊዜያዊነት እንዲያመርት ስምምነት መደረጉ ይታወቃል፡፡
በሽታው ከአለም የጠፋ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀውን የማምረት ስራ በዉሉ መሰረት አከናውኖ ኢንስቲትዩቱ ክትባቱን ለ AU-PANVAC አስረክቧል፡፡ በርክክቡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ እና የAU-PANVAC ተ/ዳይሬክተር ዶ/ር ቻርለስ ቦጆ በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
የጊዜያዊ ማምረት ፈቃድ በመስጠቱ ሂደት፣ የአለም የእንስሳት ጤና ድርጅት /WOAH ባለሙያዎች ቡድን፣ በአለም አቀፍ መመዘኛዎች መሰረት የኢንስቲትዩቱን የማምረቻ ላብራቶሪ ከመልካም አመራረት ትግበራ፣ ከባዮሴፍቲ እና ከባዮሴኩሪቲ እንዲሁም ከባለሙያ ብቃት አንጻር ፍተሻ በማድረግ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ የተፈቀደ በመሆኑ የኢንስቲትዩቱን ጥንካሬ የሚያሳይ እንደሆነና ወቅታዊ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴዎችን (cCGMP) ከዚህ በበለጠ በመተግበር አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ማሳደግ እንደሚገባ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል፡፡

The Institute has produced and delivered the Rinderpest (RP) vaccine, which serves as an emergency reserve Vaccine for Africa
----------------------------------------------------------------------
The World Organization for Animal Health (WOAH) selected the National Veterinary Institute through an international tender to produce and temporarily supply the Rinderpest vaccine for emergency stockpiling at the Pan-African Veterinary Vaccine Control Centre (AU-PANVAC).
Given the global eradication of the disease, the production process requires utmost caution. Based on the agreement, the Institute successfully manufactured and delivered the vaccine to AU-PANVAC. This collaboration was formalized during a meeting between Dr. Takele Abayneh, Director General of the Institute, and Dr. Charles Bogo, Acting Director of AU-PANVAC.
As part of the temporary production approval process, a team of WOAH experts conducted an evaluation of the Institute’s production laboratory. The assessment was based on international standards, including good management practices, biosafety and biosecurity measures, and professional competence. The Institute was found to be qualified and granted permission, demonstrating its strength and capacity.
Dr. Takele Abayneh emphasized that this achievement reflects the Institute’s capability and its commitment to implementing contemporary global manufacturing standards (cCGMP), thereby enhancing its international competitiveness.

14/11/2025

Did you know?
National Veterinary Institute supports Ethiopia’s livestock industry by producing vaccines that protect millions of animals each year?It’s innovation with impact, safeguarding livelihoods and advancing agricultural resilience.

የሀዘን መግለጫ  ..................ከ 1964 – 1965 እ.አ.አ በብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩት የተከበሩ ዶ/ር አሰፋ ወ/ጊዮርጊስ ህልፈ...
14/11/2025

የሀዘን መግለጫ
..................
ከ 1964 – 1965 እ.አ.አ በብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስኪያጅ በነበሩት የተከበሩ ዶ/ር አሰፋ ወ/ጊዮርጊስ ህልፈት ኢንስቲትዩቱ የተሰማዉን ሃዘን ይገልጻል ::
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ለኚህ አንጋፋ የእንስሳት ህክምና ባለሞያ ለዘርፉ ላበረከቱት አስተዋፆ የህይወት ዘመን እውቅና እንዳበረከተላቸው የሚታወስ ነው።
ለመላው ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል !
ነብስ ይማር!

10/11/2025
10/11/2025
የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በብሔራዊ ጥቅምና በሃገሪቱ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ቁመና ላይ ስልጠናና ውይይት አካሄዱ የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ...
30/10/2025

የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በብሔራዊ ጥቅምና በሃገሪቱ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ቁመና ላይ ስልጠናና ውይይት አካሄዱ

የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች በብሔራዊ ጥቅምና በሃገሪቱ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና ላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስልጠና ተሰጠ፡፡ የውይይቱን መድረክ የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ ሲሆኑ፤ የጥናት ሰነዱን ያቀረቡት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (ኢኢሆ) አቶ ናትናኤል ብርሃነ በኢኢሆ ስር የሚገኙ ተቀጥላ ተቋማት የቢዝነስ ተቋማት በመሆናቸው ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፆ እያበረከቱ መሆናቸውን በመግለፅ የመወያያ አጀንዳውን የብሄራዊ ጥቅምና ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና ሃገራዊ አጀንዳ እንደሆነ እና ማንኛውም ዜጋ ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በዚህ ስልጠና የሚነሱ ጉዳዮች እንደ ዜጋ ሁሉም ሰው ሊያውቀው እንደሚገባ እና እንደ መንግስት ሰራተኛም የሚጠበቅብንን ሚና ለመለየት እንደሚያስችል በመግለጽ፣ ብሔራዊ ጥቅምና የውጭ ፖሊሲ፤ የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ሁኔታ እና ያሉብን ፈተናዎች፤ ሀገሪቷ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የመንግስት ተቋማት እና ሰራተኞች ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ያላቸዉ ሚና፤ በሃገር ምንነትና ትርጉም በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሰፊ ስልጠና ሰጥተዋል።

ሀገራችን ያላትን መልክአምድራዊ አቀማመጥ፣ የተፈጥሮ ፀጋና ሃብት ተጠቃሚ እንዳትሆን፤ የባህር በር አልባ በማድርግ የጂኦግራፊ እስረኛ እንድትሆንና ብሔራዊ ጥቅሟን እንዳታስከብር በባዳና ባንዳ ሃይሎች የተለያዩ ተጽእኖዎች ሲደረጉባት የቆየ መሆኑን በመገንዘብ፣ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶቿን በአግባቡ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ ዜጎቿ ድህነትን በማሸነፍ በአለምአቀፍ ደረጃ ተሰሚነት እንዲኖራት ለማስቻል ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ እንደ ሃገር በአንድ አቋም ለጋራ ተጠቃሚነት የብሔራዊ አጀንዳ ይዘን በጋራ ስንቆም፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማረጋገጥ እንደምንችልና እንደ ተቋምም ለጋራ ተቋማዊ ራዕይና ተልዕኮ መሳካትና ትርፋማነትን ለማስቀጠል የአንድነት ዕሴትን መገንባትና ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሰራተኞችም ከመድረግ በተደረገዉ ገለጻ መሰረት እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ተቋም የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳቦችን እና ጥያቄዎችን አንስተዉ ዉይይት ተደርጎበት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ጥቅምት/ 2018

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በታማኝ ግብር ከፋይነት የሀገር ዓቀፍ የብር/ Silver ደረጃ ተሸላሚ ሆነከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግብር ከፋዮች የዕዉቅና እና...
10/10/2025

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በታማኝ ግብር ከፋይነት የሀገር ዓቀፍ የብር/ Silver ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

ከ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግብር ከፋዮች የዕዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን ፤ በ2017 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ታማኝ ግብር ከፋዮች በ7ኛዉ ዙር ሀገር አቀፍ የዕዉቅና እና የሽልማት ሥነ- ሥርዓት የኢፌድሪ ጠ/ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በ7ኛው ዙር ሀገራዊ ዕዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ላይ 22 የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተለያየ ደረጃ (የፕላቲኒየም/platinum፣ የወርቅ/Gold እና የብር/ Silver) ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የብር/ Silver ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታከለ አባይነህ በገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ለምስጋና በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ ሽልማቱን የተቀበሉ ሲሆን ከሰባቱ ዙር የምስጋና ፕሮግራም ኢንስቲትዩቱ ሲሸለም የመጀመሪያዉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱን ለዚህ እውቅና ያበቃው የተቋሙ ስራ አመረር ቦርድ፣ ማናጅመንትና የመላው ሰራተኞች የተቀናጀ ድምር ውጤት በመሆኑ፣ ዋና ዳይሬክተሩ የላቀ ምስጋናቸውን በማቅረብ፣ ኢንስቲትዩቱ የሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ልማት አጋርነቱን ለማስቀጠል ተግቶ እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡

ከእንስሳት ጤንነት እስከ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት!!!
መስከረም/2018

እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር  ይሁንላችሁ!               መልካም አዲስ ዓመት!
10/09/2025

እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር ይሁንላችሁ!

መልካም አዲስ ዓመት!

Address

Debre Zeit
DEBREZEIT19

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when National Veterinary Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to National Veterinary Institute:

Share