Ethiopian Air Defence 1970.1983

Ethiopian Air Defence 1970.1983 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Air Defence 1970.1983, Government Organization, Debre Zeit, Debre Zeyit.
(6)

የአየር መከላክያ አባል መ/አ ሰብስቤ ምትኩ ጳግሜ 1 ቀን 2016 አም  ከዚህ አለም  በሞት መለየቱን ስንሰማ በጣም አዝነናል የወንድማችንን ነብስ በገነት ያሳርፍልን እያልን ለቤተሰቦቹ  መጽ...
13/09/2024

የአየር መከላክያ አባል መ/አ ሰብስቤ ምትኩ ጳግሜ 1 ቀን 2016 አም ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ስንሰማ በጣም አዝነናል የወንድማችንን ነብስ በገነት ያሳርፍልን እያልን ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እነመኗለን

10/09/2024
05/10/2023

የ42ኛ የወደብ ብርጌድ” ወይም "የ42ኛ አየር መቃወሚያ መድፍ ሬጅመንት" እና "የ4ኛ ሚሳይል ሬጅመንት" አጭር ታሪክ
።።።።።።።////።።።።።

ሰላም ወንድሜ ሻለቃ ተሾመ ተሊላ::
ምናልባትም ላታውቀኝ ትችላለህ።
ታደለ ካሣ (ሻለቃ) እባላለሁ።
የአየር መከላከያና የሐረር ጦር አካዳሚ 21ኛ ኮርስ ፣ የሙያ አጋርህና የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ነኝ::

ውድ ወንድሜ ሻለቃ ተሾመ:- አገራችን ኢትዮጵያን ከጠላት ለመጠበቅ የአንተና የእኔ ትውልድ የሆነው የቀድሞው የአየር መከላከያ ሠራዊታችንን ድንቅ ታሪክ ለትውልድ ለማስተላለፍ ያደረግኽውን ጥረትና የፃፍከውን በእጅጉ አደንቃለሁ:: አመሰግናለሁም።

አሁን እኔም የእንተን የወንድሜን ፈለግ በመከተል የማውቀውን ዕውነተኛ ታሪካችንን ለማስተላለፍ ስለነበርኩበት የአየር መከላከያ ክፍል እፅፋለሁ።

እኛ የአንድ ዘመን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሐይል የነበርን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ታሪካችን ተመሳሳይና ተቀራራቢ ነው።

ከዛሬ 46 ዓመት በፊት ማለትም ከ1970 ዓ.ም መስከረም ወር ጀምሮ ፣ የእናንተ የአየር መከላከያ ፔቹራ ሚሳይል ሠራዊት አሰብ ፣ ሳሊና ጨው ማምረቻና አሰብ ሰቂር አካባቢ ሠፍሮ በነበረበት ወቅት ፣ የእኛም የ42ኛ አየር መቃወሚያ የወደብ ብርጌድ ሶስት የ100ሚ.ሜ ተዋጊ ባትሪዎችና ሶስት የ57 ሚ.ሜ ተዋጊ ባትሪዎቻችን ፣ ከብርጌድና ከሻለቃ ጠቅላይ ሠፈሮቻቸው ጋር ከእናንተ ጎረቤት በመስፈር ፣ የአገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንበር በመጠበቅ ላይ ነበርን::

የ42ኛ የወደብ ብርጌድን ያቋቋሙት በአብዛኛው የሐረር ጦር አካዳሚ 21ኛ ኮርስ ዕጩ መኮንኖች ፣ ከማዕከላዊ ዕዝ ከመጡ ነባር መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ጋር ሲሆን ፣ በተለያዩ ቦታዎች ተመልምለው የሠለጠኑና የተማሩ ወጣት ወታደሮችና የበታች ሹማምንቶችም ቀደም ብለው አሰብ አካባቢ ሠፍረው ነበር።

በተለይም በመስከረም ወር 1970 ዓ.ም መጀመርያ ላይ አገራችን በነበረችበት አንገብጋቢ የሶማሊያ ወረራ ምክንያት እኛ የ21ኛ ኮርስ አባላት ፣ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ ዕዝ ግቢ ውስጥ ተሰባስበን ወደ አሰብ ቀጠና ለመሰማራት በመዘጋጀት ላይ ሳለን ፣ ብዛት ያላቸው ሲቪል የለበሱ ወጣቶች በአውቶብስ መጥተው ከተራገፉ በኋላ ከእኛ ጋር ተቀላቅለው ነበር።

በዚያን ጊዜ እኛም በጣም ወጣት የነበርነው የ21ኛ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችም ተዘጋጅቶ ለወታደሮቹ በአስቸኳይ እንዲከፋፈል የመጣውን አረንዴ ፋቲክ የወታደር ዩኒፎርም ወዲያውኑ ለተሰበሰቡት ወጣቶች ካደልናቸው በኋላ በግማሽ ቀን ውስጥ ከክላሺንክቭ መሳርያ ጋር በማስተዋወቅ ለአሰብ የአውቶብስ ጉዞ አዘጋጀናቸው።

በመቀጠልም በአንድ ነባር የበታች ሹም መሪነት ቁጥራቸው በጣም ብዙና ፍፁም ማሠልጠኛ ያልገቡትን ወታደሮች በብዙ አውቶብስ ጭነን ፣ አብረን እንደተዓምር ሊቆጠር በሚችል አደገኛ ጉዞ በማድረግ አሰብ ከደረስን በኋላ 30ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ የተሠራበት አውላላ ሜዳ ላይ ለጥቂት ቀናት ሠፈርን።

ከዚያም በ42ኛ የወደብ ብርጌድ ስር በመታቀፍ በየውስጥ ክፍሎች ተበታተንን።
የ42ኛ የወደብ ብርጌድ አዛዣችን ደሳለኝ ሙሴ (ብ/ጄነራል) ሲሆኑ የብርጌዱ ችፍ ኦፍ ስታፋችን መስፍን ተስፋ ማርያም (ኮለኔል) ናቸው።
አብረውን ይሠሩ የነበሩ ብዙ ሩሲያዊያን ኤክስፐርቶችና አባት ጦር ሾፌሮችም ነበሩን::

ከአዲስ አበባ ያመጣናቸውን ወታደሮች በአጭር ቀናት ውስጥ በተለይም በአዲሱ በ100ሚ.ሜ መድፍ ላይ በመሰልጠን በ18ኛው ተዋጊ ሻለቃ ስር ቦታ እንዲይዙ ተደረገ::

በዚህም መሠረት ፣ 1ኛ ባትሪ አሰብ ስቂር አካባቢ ፣ 2ኛ ባትሪ ከነዳጅ ማጣርያው ጀርባ ፣ 3ኛ ባትሪ ከሳሊና ጨው ማምረቻ ፊት ለፊት አስፓልቱን ተሻግሮ ከተራራው አጠገብ ሠፍረው አገራቸውን መጠበቅ ጀመሩ።

በሌላ በኩል ቀደም ብለው አሰብ የሠፈሩና የተማሩ ወጣት ስብስብ ወታደሮችና የበታች ሹማምንት ያሉበት የ57 ሚ.ሜ አየር መቃወሚያ መድፍና RPK ራዳር የታጠቁ የ17ኛ ሻለቃ ተዋጊ ጦር አሰብ ውስጥ በሶስት ቦታዎች ላይ ሠፍርው ነበር።

ይኽውም 1ኛ ባትሪ ከሆስፒታሉ አጠገብ ፣ 2ኛ ባትሪ ከነዳጅ ማጣርያው ጎን ፣ 3ኛ ባትሪ ከነዳጅ ማጣርያው ፊት ለፊት ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ በመሠማራት አገርን ከጠላት የመጠበቅ ግዳጅ ተወጥተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ድጋፍ ስጪ የብርጌድና የሻለቆች ጠቅላይ ሠፈሮች ፣ ፒ-12 እና ፒ-15 የታጠቁ የሻለቃና የብርጌድ የራዳሮች ቅኝትና የመገናኛ ባትሪዎች ከተለያዩ ማዘዣ ጣቢያዎች ጋር ነበሩን። የጥገናና የጋራዥ ክፍሎቻችንም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ።

በ1971 ዓ.ም አካባቢ የአሰብ ነዳጅ ማጣርያ ላይ ባልታወቁ ሃይሎች በርቀት ከባህር የከባድ መሳርያ ተኩስ መከፈቱን በቦታው የነበርን እናስታውሳለን።

በዚያን ወቅት 42ኛ የወደብ ብርጌድ በመድፍ ፣ 2ኛ ሚሳይል ሬጅመንት ደግሞ በሚሳይል አጭር መላሽ መስጠታችን ይታወስል።
በመቀጠልም ተመሳሳይ የጠላት እንቅስቃሴ ዳግም እንዳይከሰት በማሰብ ፣ የ42ኛ የወደብ ብርጌድ የ17ኛ አየር መቃወሚያ ሻለቃ 2ኛ ተዋጊ ባትሪ ከሙያ አጋሮቻችን ከ30ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ ጋር በመሆን በፍፁም ሰው አልባዎቹና በቀይ ባህር መሃል በሚገኙት ሁለት ማክዋርና ፉጡማ በሚባሉ ደሴቶች ላይ በመስፈር አገርን ለመጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት አሁን ላይ ማስታወስ ግድ ይላል።

በነኚህ ሞቃታማና ቀናትን እንኳን ማስታወስ በማይቻልበትና በማያስፈልግበት ሰው አልባ ደሴቶች ላይ ብዙዎች የሠራዊቱ ጓዶቻችን የከፈሉት መስዋዕትነትን በዓይኔ ስላየሁት አስታውሰዋለሁ።
በያኔው ባህር ሐይላችን ላንዲንግ ክራፍት መርከብና አልፎ አልፎ በሄሎኮፕተር የሚቀርብላቸውን ወታደራዊ ስንቅን ከቀይ ባህርውስጥ ከሚወጡ የባህር ኤሊዎች ጋር እንዴት ለምግብነት ይጠቀሙባቸው እንደነበር አስታውሳለሁ።

በሃይለኛው በደሴቶቹ ሙቀት ምክንያት ብብት ላይ ሽፍ የሚለውና እንደአሞራ ክንፎች ክንዶችን የሚያዘረጋው የበረሃ አምበግብግ ሽፍታ ከነበረው የውሃ ዕጥረት ጋር ሊረሳ የሚችል አይመስለኝም።

አባቶቻችን ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው ያቆዩልንን ታላቅ አገር ፣ እኛም እንደአአቅማችን የዚህ ዓይነት መስዋዕትነት ከፍለን የጠበቅናት አገራችን ፣ ዛሬ ላይ ከመገነጣጠልና ወደብ አልባ ከመሆን አልፉ ፣ ወንድም ከወንድሙ ጋር በዘርና በጎጥ ደም ሲፋሰስባት ማየት በእጅጉ ያስቆጫል። ያሳዝናል።

ባጠቃላይ በዚያን ጊዜው የ42ኛ ብርጌዳችን ውስጥ ያገለገሉት ፣ የተለያዩ ነባር የሠራዊቱ መኮንኖች ፣ የበታች ሹማምንትና ወታደሮች ሲሆን ፣ የ33ኛ ፣ የ34ኛና ሌሎች የሆለታ ገነት ጦር ት/ቤት ተመራቂዎች እንዲሁም በሶማሊያ ወረራ ምክንያት በዕጩ መክንንነት የዘመቱ የሐረር ጦር አካዳሚ 21ኛ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችና ሌሎችም ይገኙበታል።

"42ኛ አየር መቃወሚያ የወደብ ብርጌድ" ተብሎ ይጠራ የነበረው ክፍል ፣ በታጠቀው ዘመናዊ መሳርያ ምክንያት በ1972 ዓ.ም አካባቢ በአዲስ ስያሜ "42ኛ አየር መቃወሚያ ሬጅመንት" ተብሎ ከማዕከላዊ ዕዝ አስተዳደር በመውጣት በአየር መከላከያ ስር እንዲተዳደር ተደረገ።

42ኛ አየር መቃወሚያ ሬጅመንት በአየር መከላከያ ስር መተዳደር ከጀመረ በኋላ የመዋቅር ለውጥ መደረግ ተጀመረ። የብዙ ዓይነት ትምህርቶችም በር በሰፊው ተከፈተ።

በዚህም መሠረት በዚያን ጊዜ ሻለቃ በነበሩት አበበ አያና የሚመራ 4ኛ ሚሳይል ሬጅመንት ተብሎ የሚጠራ አዲስ የቮልጋ ሚሳይል ክፍል ለማቋቋም ታስቦ እኔንም ጨምሮ ከ42ኛ የተወጣጣን መሉ ሬጅመንት በ1976 -1977 ዓ.ም አካባቢ ወደቀድሞው ሶቭየት ኅብረት ፣ ቱርክሜኒያ ሪፐብሊክ ፣ ከክራስኖቮስክ ከተማ አለፍ ብሎ ወደሚገኘው ያንጋጃ በማምራት የአጭር ወራት የቮልጋ ሚሳይል ኮምፕሌክስ ትምህርታችንን ከተከታትለን በኋላ አስፈላጊውን የዒላማ ተኩስ አድርገን ወደ አገራችን ኢትዮጵያተመለስን።

ወደአገራችን ከተመለስንም በኋላ የሚሳይል ሳይት የሆነ የመስፈርያ ዘለቄታዊ የጦር ሠፈር እስከሚዘጋጅልን ድረስ በደብረዘይትና አካባቢ በሚገኙ የአየር መከላከያ ክፍሎች ውስጥ በተደራቢነት ተበትነን መስራት ቀጥልን።

በዚህም መሠረት እኔም ደብረዘይት ከአየር ሐይል ጀርባ ፣ በ13ኛ የሚሳይል ተዋጊ ሻለቃ ቆርኬ ተራራ ላይ በመደረብ በቺፍ ኦፍ ስታፍነት ሠርቻለሁ።

በ1980 ዓ.ም ላይ እኔ ለሌላ የስድስት ዓመት የስቪል ኢንጂኔሪንግ ትምህርት ለመማር ወደሞስኮ ፓትሪስ ሉሙምባ ዩንቨርሲቲ ከሄድኩኝ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ወያኔ የሚባል ዘረኛ ቡድን ወደስልጣን በመምጣት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ላይ የምንገኝ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በሙሉ በዘረኛው ቡድን አገራችንን ከመጠበቅ ሙያ በጅምላ ተባረናል።

በዚህም የተነሳ እኔ እስከማውቀው ድረስ በአውሮፓ በብዙ የሶሻሊስት አገሮች ይማሩ የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ ከፍተኛ ኢትዮጵያውያን ወታደራዊ ምሁራን ፣ ወታደራዊ ዶክተሮች ፣ ኢንጂነሮች ፣ ኢኮኖሚስቶችና ሌሎችም አገር ውስጥ እንደተበተኑት የሙያ ጓዶቻቸው ሁሉ ለስደትና ለእንግልት ተዳርገዋል።

ከዚያ በኋላ በአገር ውስጥ የሆነውን እኔ አገር ውስጥ ስላልነበርኩኝ በደምብ አላውቅም።
ስለዚህ "ማን ይመስክር ያየ ፣ ማን ይናገር የነበረ" እንደሚባለው ቀጥሎ ለታሪክ መተላለፍና መፃፍ የሚገባውን አገር ውስጥ የነበሩ ወንድሞች እንዲፅፉት ለእነርሱው እተወዋለሁ።

ኢትዮጲያ ለዘላለም በሰላም በፍቅርና በአንድነት ትኑር።

ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ።
ታደለ ካሣ
መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ለንደን

ሐምሌ 1989 ዓ/ም የኢትዮ - ኤርትራ ጦርነት ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት ወደ ኤርትራ የሄደው የኢትዮጵያ አየር መከላከያ ሙያተኞች ቡድን፤ ከማስታውሳቸው ውስጥ ፤ 1. ዳኜ አበበ - አንቴና...
03/10/2023

ሐምሌ 1989 ዓ/ም የኢትዮ - ኤርትራ ጦርነት ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት ወደ ኤርትራ የሄደው የኢትዮጵያ አየር መከላከያ ሙያተኞች ቡድን፤ ከማስታውሳቸው ውስጥ ፤
1. ዳኜ አበበ - አንቴና ስፔሻሊስትና የቡድን መሪ ፤
2. ድምፁ ግርማይ - ራዳር ኢንጂነርና የቡድን መሪ ፤
3. አዳነ ተክሉ - MTI ሙያተኛ ፤
4. ካሳሁን አበበ - ላውንቸር ሙያተኛ በሞት የተለየ ፤
5. ብርሃኑ ደሜ - KIPS ሙያተኛ፤
6. ታደሰ ገብረየስ - ጋይዳንስ ኦፊሰር፤
7. መሐሪ - የዲዝል ቴክኒሽያን፤
8. መኩሪያ ቸኮል - CTS ሙያተኛ ፤
9. መሠረት ለታ - CCS ሙያተኛ ፤ በሞት የተለየ ፤
10. ደባስ ዓለሙ - CGS ሙያተኛ በሞት የተለየ ፤
11. ቦጋለ - MGS ኢንጂነር በሞት የተለየ፤
12. አየለ - የሚሳይል አሰምብሊ ሙያተኛ፤
13. አለማየሁ በደቄ - KIPS ሙያተኛ ፤
14. አበራ በርሲሳ - የላውንቸር ሙያተኛ ፤
15. አንቶኒዮስ ገ/ማርያም- የሚሳይል ሙያተኛ በሞት የተለየ ፤
16. ዱላ ተረዳ - የኮምፕሬሰር ሙያተኛ ፤
17. ገ/ እግዚአብሔር ነጋሲ - ኤርትራዊ ዲዝሊስት ፤
18. አስመላሽ - ኤርትራዊ KIPS ሙያተኛ ፤

የሻለቃ አለማየሁ መርዕድ አጭር የሕይወት ታሪክ።።።።።።።////።።።።።።።።።።ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ ተምትም ከአባታቸው ከአቶ መርዕድ ተምትምና ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺ ዘውዴ በሲዳሞ ክፍለሃ...
03/10/2023

የሻለቃ አለማየሁ መርዕድ አጭር የሕይወት ታሪክ
።።።።።።።////።።።።።።።።።።

ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ ተምትም ከአባታቸው ከአቶ መርዕድ ተምትምና ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺ ዘውዴ በሲዳሞ ክፍለሃገር ፣ በዲላ ከተማ ፣ ሚያዚያ 7 ቀን 1950 ዓ.ም ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በዲላ ከተማ ፣ ዓፄ ዳዊት ት/ቤት እስከ አምስተኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ ከቤተሰባቸው ጋር ወደ አለታ ወንዶ ከተማ በመሄድ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምረዋል።
በመቀጠልም ወደአዲስ አበባ በመጓዝ በቀድሞው ተፈሪ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

በ1968 ዓ.ም እና በ1969 ዓ.ም በቀድሞው ሐረር ጦር አካዳሚ ወታደራዊ መሠናዶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ በዕጩ ዕጩ መኮንንነት ተመልምለው በመግባት የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ፣ የአካዳሚክስና ተዛማጅ ወታደራዊ ትምህርቶችን ተከታትለዋል።

በ1969 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የሶማሊያ ወራሪ መንግስት ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ፣ የሐረር ጦር አካዳሚ ዕጩ መኮንኖች በሙሉ ወደሆለታ ገነት ጦር ት/ቤት ተዛወረው ወራሪውን ጠላት ለመመለስ ዝግጅት ውስጥ ገቡ።
ሻለቃ አለማየሁ መርዕድም በሆለታ ገነት ጦር ት/ቤት በአፋጣኝ በመግባት የተሰጣቸውን አገርን ከጠላት የመከላከል የጦር ትምህርታቸውን ተከታትለው በአሰብ ግንባር ተሠማሩ።

ሻለቃ አለማየሁ በ1970 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብቸኛ የነበረውን የአሰብ የነዳጅ ማጣርያና የአሰብ ወደብን ከሶማሊያ አውሮፕላኖችና ከሌሎች ጠላቶች ለመከላከል ፣ ለአገሪቱ አዲስ የነበረውን ከባድ የአየር መቃወሚያ መድፍና ራዳር የያዘ ተዋጊ ባትሪ አዛዥ በመሆን አገራቸውን ጠብቀዋል።

ከዚያም የአየር መቃወሚያ ሻለቃ አዛዥና የ42ኛ አየር መቃወሚያ ሬጅመንት የትምህርትና ዘመቻ መኮንን በመሆን ሠርተዋል።

በመቀጠልም በቀድሞው ሶቪየት ኅብረት የኮማንድ ኤንድ ስታፍ ትምህርት ተምረው ወደ አገራቸው በመመለስ ደብረዘይት፣ በአየር መከላከያ ፣ አየር ሐይል ውስጥ አገልግለዋል።

ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ በ1976 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በመግባት ፣ በማኔጅመንትና በሕዝብ አስተዳደር ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል።

ከዚያም ወደእናት የሠራዊቱ ክፍላቸው አየር መከላከያ በመመለስ የተወሰነ ጊዜ ካገለገሉ በኋላ ፣ ወደ አዲስ አበባ ወታደራዊ ኮሚሳርያት ተዛውረው ሠራዊቱ እስከተበተነበት 1983 ዓ.ም ድረስ ፣ አገራቸውን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል እስከ ሻለቃነት ማዕረግ ደርሰዋል።

ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ ከ1985 እስከ1987 ዓ.ም ድረስ ፣ በቀድሞው ደቡብ ብሔር ፣ ብሔረሰቦች ክልል ፣ ሃዋሳ ሲቪል ሰርቪስ ፅህፈት ቤት ውስጥ በባለሙያነት አገልግለዋል።

ከየካቲት ወር 1987 ዓ.ም ጀምሮ ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ሃዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ፣ ወደ አዲስ አበባ በመዛወር ፣ የተክለሃይማኖትና የኮርፓሬት ቅርንጫፎች ስራ አስኪያጅ ሆነው ሰርተዋል።

በመቀጠልም በዋናው መስርያ ቤት በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ በመስራት ፣ በድርጅቱ Resource Management Executive Director ደረጃ የSenior Management Team አባል በመሆን እስከ2011 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል።

ከዚያም ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በኒያላ ኢንሹራንስ ውስጥ በልዩ የሃላፊነት ደረጃ ሲያገለግሉ ቆይተዋል ።

ሻለቃ አለማየሁ መርዕድ ፣ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ነበሩ።
ሻለቃ አለማየሁ ቅን ፣ በጣም ለሰው አዛኝ ፣ ርኅሩኁና የቤተዘመድ ሰብሳቢ ፣ አቀራራቢ ፣ ለተቸገሩ ጓደኞችና ሰዎች ቀድመው የሚደርሱ ደግ ሰው ነበሩ።

ሻለቃ አለማየሁ በሃይለኛ ህመም ምክንያት የሆስፒታል አልጋ ይዘው ባሉበት በመጨረሻው ሰዓት እንኳን በችግር ላይ የነበረ ጓደኛቸውን ቤተሰብ ለማቋቋም ፣ በመላው ዓለም የሚኖሩ ጓደኞቻቸውን በማስተባበርና በመማፀን ወደእሩብ ሚሊዮን ብር አካባቢ አሰባስበው መስጠት የቻሉ በጣም ቅንና ደግ ሰው ነበሩ።

በመጨረሻ ላይ ሻለቃ አለማየሁ በኮርያ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሆስፒታል መጥታችሁ ለጠየቃችሁ ፣ በሻለቃ አለማየሁ መኖርያ ቤት በመምጣት ላፅናናችሁ ሁሉ ፣ እግዚአብሔር ብድራችሁን ይክፈላችሁ።

በሻለቃ አለማየሁ መርዕድ መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡትን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።
የሁሉንም ስም መዘርዘር ቢረዝምብንም የሚከተሉትን አበባ ያስቀመጡ ለአብነት ያህል እንጠቅሳለን።

1. ባለቤታቸው ወ/ሮ ይመኙሻል ታከለና ልጆቻቸው
2. ወንድማቸው አቶ ንጉሴ ዘውድነህ
3. የግራዝማች ተምትም ቤተሰብ ማኅበር
4. የሐረር ጦር አካዳሚ 21ኛ ኮርስ መረዳጃ ማኀበር
5. ኒያላ ኢንሹራንስ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ፣ እንዲሁም ሌሎች።

የሻለቃ አለማየሁ መርዕድን ነፍስ ፈጣሪ በዓፀደ ገነት ያኑርልን።
ዓሜን!!

"የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል ፤
ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም!"
(ዮሐ 11:26)

Girma Wendaferaw Gizachew Kebede Seboka Debela Tesfa Kibkab Getahun belhu Wehib tesema
29/09/2023

Girma Wendaferaw Gizachew Kebede Seboka Debela Tesfa Kibkab Getahun belhu Wehib tesema

Dear friendsWe would like to invite you to the funeral service of Yafet Desta, held september 9th at 10am in Dublin. For...
06/09/2023

Dear friends
We would like to invite you to the funeral service of Yafet Desta, held september 9th at 10am in Dublin. For our friends that can't attend at the funeral in Dublin are welcome to join us online through the link down below.

The death has occurred of Yafet DESTA of Naas, Kildare Ireland, on 06/09/2023. You can view the full death notice and add your condolences here.

ውደ ጋደኞቺ የክፍላቸን ባልደረባ የሆኑት ሻንበል ያፈት ደስታ ባደረባቸው ህመም በ ህከምና ሲረዱ ቆይተው በሚኖሩበት አየርላንድ ዱብሊን ከተማ ከዚህ አለም በሞት በዛሬው ቀን (6/09/2023 ...
06/09/2023

ውደ ጋደኞቺ የክፍላቸን ባልደረባ የሆኑት ሻንበል ያፈት ደስታ ባደረባቸው ህመም በ ህከምና ሲረዱ ቆይተው በሚኖሩበት አየርላንድ ዱብሊን ከተማ ከዚህ አለም በሞት በዛሬው ቀን (6/09/2023 ) መለየታችወን ሰንገልጽ በከፍተኛ ሃዘን ነው
ወንድማቸን ያፌት ቅን ትሁት እና ለጋደኞቹ እና ለሃገሩ ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ተናግሮ ከማስቀየም ዝምታን የሚመርጡ ለቀረባቸው ደግሞ አዛኝና አስተዋይ እንዲሁም ተጫዋች የሆኑ ባለትዳር እና አንድ ሴት እና የሁለት ወንዶች አባት ነበሩ የተፈጥሮ ህግ ሆኖ ዛሬ ቢለዩንም
በህሊናችን ግን ሁል ጊዜ የኖራሉ ለ ቤተሰቦቹ እና ለጋደኞቹ መጽናናትን እየተመኘን የ ወንደማችንን ነብስ አምላክ ከመንበሩ ጎን በአጸደ ገነት ያኑርልን

This is In the former USSR AIR DEFENCE SCOOL. I think most of of were assigned as plotters in command post.
18/05/2023

This is In the former USSR AIR DEFENCE SCOOL. I think most of of were assigned as plotters in command post.

የክፍላችን ባልደረባ የነበሩት ሻንበል ተስፋዬ ጉተማ  ፓፓ ከዚህ አለም በሞት መለየት የሰማነው በከፍተኛ ሃዘን ነው የወድውማችንን ነብስ በአጸደ ገነት እንዲአኖርልን አምላከን እይተማጸን ለልጆ...
22/01/2023

የክፍላችን ባልደረባ የነበሩት ሻንበል ተስፋዬ ጉተማ ፓፓ ከዚህ አለም በሞት መለየት የሰማነው በከፍተኛ ሃዘን ነው የወድውማችንን ነብስ በአጸደ ገነት እንዲአኖርልን አምላከን እይተማጸን ለልጆቹ እና ለሞላው ቤተሰቡ እና ጋደኝቹ መጸናናትን እንመኝለን

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፈራቸው ምርጥ የአየር መከላከያ  አመራሮች አንዱ የሆኑት ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃዲቅ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በጦር ኃይሎች ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 5ቀ...
14/01/2023

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፈራቸው ምርጥ የአየር መከላከያ አመራሮች አንዱ የሆኑት ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃዲቅ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በጦር ኃይሎች ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 5ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ከፍተኛ መኮንኑ በክንፍ አዛዥነት፡በምድብ አመራርነትና በመምሪያ ሃላፊነት ተቋማቸውንና ሃገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ሲሆን የእኚህ የሃገር ባለውለታ ጀግና ቀብራቸውም ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ቃጅማ ጊዮርጊስ ቤ/ክ መካነ መቃብር ይፈፀማል።
ኮ/ል አስጨናቂ ጡረታ ከወጡም በኋላ ወደ አየር ኃይል ተመልሰው በሙያቸው ሃገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ ታላቅ የጦር መኮንን ነበሩ።ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን።'

07/01/2023

ውድ ወገኖቼ, እንኳን ለጌታችን ለመድኅኒታችን ለእየሱስ ክርቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን:: በዓሉን የሰላም የፍቅርና የአንድነት ያድርግልን::

Melkam Gena! Merry Ethiopian Christmas! May Christ’s love fill our beloved Ethiopia, our home and life, and bring countless blessings upon us this festive day! 🙏❤️❤️❤️

ለሞላው ጋደንኞቺ
25/12/2022

ለሞላው ጋደንኞቺ

Fundet på Google fra pixabay.com

10/09/2022

Hittades på Google från addiscards.net

28/03/2022
መልካም ተግባር መልሶ ይከፍላል!የግል አየር መንገዶች የቀድሞውን  የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በክብር ሸኙ በኢትዮጲያ የሚንቀሳቀሱ የግል አየር መንገዶች በመተባበር የኢትዮጲያ...
22/03/2022

መልካም ተግባር መልሶ ይከፍላል!
የግል አየር መንገዶች የቀድሞውን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በክብር ሸኙ
በኢትዮጲያ የሚንቀሳቀሱ የግል አየር መንገዶች በመተባበር የኢትዮጲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለ12 አመታት በዋና ዳይሬክተርነት ለመሩት ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው በዛሬው እለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጁት የምሳ ግብዣ እና የሽኝት ፕሮግራም ላይ አዲስ የቤት መኪና ሽልማት አበርክተዋል፡፡
በስነ ስርአቱ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ፤ አዲሱ የኢትዮጲያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ፤ ሌሎች የባለስልጣኑ ሀላፊዎች እና የግል አየርመንገዶች ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል፡፡
የግል አየርመንገዶችን በመወከል ንግግር ያደረጉት የአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት እና አቪየሽን አካዳሚ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ካፒቴን ሰለሞን ግዛው እና የአኳሪየስ አቪየሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍሬህይወት ተሰማ ኮሎኔል ወሰንየለህ 12 አመታት በታታሪነት ለሰጡት መልካም አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው "12 አመታት ረዥም ጊዜ ነው፡፡ ሁሉንም አግባብቶ ረዥም ጊዜ ማገልገል ከባድ ሀላፊነት ነው፡፡ ለእኔ ታላቅ ወንድሜ መካሪዬ ነህ፡፡ ውለታህን አንረሳም፡፡" ብለዋል፡፡
አክለውም"ብዙ ጊዜ ሀላፊ ሲሔድ ሄደልን ይባላል ፡፡ ኮሎኔል ወሰንየለህ በዚህ መልኩ በክብር በመሸኘትህ እንኳን ደስ አለህ እንኳን ለዚህ አበቃህ ፡፡ በቅን ልብ ማገልገል በስተመጨረሻ ይከፍላል፡፡" ብለዋል፡፡
ኮሎኔል ወሰንየለህ ለተደረገላቸው የሽኝት ፕሮግራም እና ለተበረከተላቸው ስጦታ አመስግነው ስራውን ብቻቸውን ሳይሆን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመተጋገዝ እንደሰሩት ገልጸዋል፡፡(ኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

Address

Debre Zeit
Debre Zeyit
22201

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Air Defence 1970.1983 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Nearby government services