Kassaye

Kassaye Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kassaye, Library, Kassaye www, com, Dessie.

28/08/2024

5608 likes, 311 comments. “📞0916144641 📞0917016535”

23/09/2022
02/09/2022

ዳዳ ተክለሃማኖትና ዘንዶ መንገድ
ይህ ቦታ በአሁኑ 043 ቀበሌ እየ ተባለ በሚጠራው ከደንሳ ከተማ በስተሰሜንየሚያዋስ035ና034ቀበሌዎችን አቋርጠን በግምት12ኪሎ ሜትር ርቀት ላይየሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው፡፡ይህ ታሪካዊ ቦታ በፊት በጥንት ጊዜ በዚያ አካባቢ ያለው ህዝብ በዘንዶ ያመን /ያመልክ / ነበር ፡፡ በዚህም ምክንያት የበኩር ልጅ ለዘንዶው ህብረተሰቡ እያዋጣ ለምግብነት ይሰጡ /ይገብሩ/ እንደነበርና በዚህ አካባቢም ሌላ የማምለኪያ ቦታ እንዳልነበር እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ያወሳሉ። ዘንዶው ደልዳሊተት ከተባለው ቦታ አንድ ትልቅ የወይራ ዛፍ ላይ ጅራቱን ሳይንቀሳቀስ ዙሃ ከተባለው ወንዝ ውሃ ጠጥቶ ከዚያ ሲመለስ ለዘንዶው ለምግብነት የሚነት የሚያገለግል ልጅ በአካባቢው ህብረተሰብ ደንብ መዋጮ መሰረት ከእለታት አንድ ቀን ግብሩ የደረሰበት ሰው የበኩር ልጁን ከወይራው ዛፍ ላይ ለዘንዶው ምግብነት ሰቅሏት ሄዶ ነበር። በዚህ ወቅት ከወይራው ዛፍ ላይ እንደተሰቀለች አባ አቡነ…ተክለ ሃይማኖት የተባሉ ድንግላይ መነኩሴ ከዛፉ ስር ቁጭ ብለው የፆለት መፅሃፋቸውን እንደገለፁ የተሰቀለችው አንድ ሴት ልጅ እንባዋ ከመፅሃፉ ላይ ጠብ አለባቸው። አባተክለ ሃይማኖትም ቀና ብለው በማየት ምንድነሽ ብለው ጠየቋት ። በዚህ ወቅት ልጅቱ ለዘንዶ እራት ተሰቅየ ነውና ዘንዶው ይመጣል እንዳይበላህ ከዚህ ይሂዱ ብላ ነገረቻቸው። የዘንዶው መምጫ ሊደርስ ስለሆነ ከዚህ ልቀቅ አለቻቸው ልጅቱ፡፡ አባ ተክለ ሃይማኖትም ፀሎታቸውን እያደረጉ እንደተቀመጡ ዘንዶው አፉን ከፍቶ ሲመጣ በስመአብወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ብለው በመስቀል አሳይተው በጦራቸው ወጉት ።
ሲወጉትም ዘንዶው ለሁለት ተሰንጥቆ ሞተ ። ለዘንዶው እራት የተባለችው ልጅ ከዛፉ ለይ ወርዳ ከአባተክለ ሃይማኖት እግር ወደቀች። ከዚህ በኀላ ም ልጅቱ ወደ ቤት ሄደች። በዚህ ምክንያት የአካባቢው ማህበረሰብ የሚያመልክበት ዘንዶ ስለሞተ ወደ አባ ተክለሃይማኖት ዘንድ የጦር መሳሪያ እየተያዘ አባተክለሃየማኖትን ለመገደል መጡባቸው፡፡
የአካባቢው ማህበረሰብም አባተክለሃይመኖትን ለመግደል ጥይትሲተኮስባቸው ጥይቱ ኩበት፣ጦር ሲወረወርባቸው ጦሩ አገዳ ፣ድንጋይ ሲወረወርባቸው ኩበት እየሆነ ለሶስት ቀን ያህል ህብረተሰቡ ዙሪውን በመክበብተዋጋ ። ከዚህ በኀላ የዘንዶው ሬሳ መሽተት ጀመረ ። የአካባቢው ማህበረሰብም አባ ተክለሃይማኖትን ምን አይነት ሰው ነህ በማለት ጠየቋቸው ። አባ ተክለሃማኖትም ህዝቡን በመሰብሰብ ማስተማር ፣መስበክ ጀመሩ ። ህዝቡንም በመሰቀላቸው ባርከው አሳመኑት ። ህብረተሰቡም ካመነ በኀላ አንተ አምላካችን ከሆንክ ይህንን የዘንዶ ሬሳ አንሳልን … አላቸው አባተክለ ሃይማኖትም …በስመአብ ወልድ ወመንፍስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ …ብለው ደግመው …እፍ … ቢሉት ዘንዶው ከቦታው ተነስቶ አጨቅ በሚባለው ጎራ ለጎራ በድናምባ ፣ በመጥሪያ ፣ በየሾብ ላይ አባይን ተሻግሮ የቀንዳች ከተባለው ጫካ /ጎጃም/ ውስጥ አረፈ ይባላል፡፡ ጎጃም ውስጥ ልዩ ቦታው የቀንዳች እየተባለ በሚጠራው ቦታ የዘንዶው አፅም ይታያል አለ እየተባለ ይወራል፡፡ አባተክለ ሃይማኖትም ከዚህ ቀጥሎ ቤተክርስቲያኑን ከተሰራበት ቦታ ላይ መጥተው ተቀመጡ ፡፡ ቦታውንም ባረኩት ያሉበትን አካባቢም /ቤተክርስቲያኑ የተሰራበት / አንድክንድ ከስንዝር መሬቱን ካለበት ቦታ ከፍ አደረጉት፡፡ የአካባቢውን ህብረተሰብ አተመቁት ። ህዝቡም ወደ ክርስትና ሃይማኖት ተቀየረ ።
በአሁኑ ወቅት ቤተክርስቲያኑ በሚገኝበት ቦታ ላይ አባተክለ ሃይመኖት ለ40ቀን ያክል ተቀመጡ፡፡ በዚህም አጋጣሚ ህብረተሰቡ ወደክርስትና እምነት ሲቀላቀል አገሩን ..አማራ ሳይንት …ብለው ሰየሙት። ዘበዚህም ቆይታቸው አርባ ተንሳይ የተባለ ጽላት ቀርጸው፣ የእጃቸውን መስቀል ሰጥተው ቦታውን ..ዳዳ.. . ተክለ ሃይማኖት …አሰኝተው ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲሄዱ ህዝቡ ተከትሎ እያለቀሰበአሁኑ ወቅት ወግድና ከላላ ከተባለ ቦታ ድረስ በመሄድ ሸኝተዋቸው ተመለሱ ። እሳቸውም ደብረ ሊባኖስ ሄደው እዚያው አረፉ ይባላል፡፡
ዳዳ ያሉበትም ምክንያት ቦታው ከዚያአካባቢ ካሉ ቦታዎች ከፍ ያለና ህዝቡ የዋህ ስለሆነና አባተክለሃይማኖት አገሩን ለመባረክ ስለተመቻቸው ..ዳዳ ብለው ሰየሙት ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቦታው ዳዳ በመባል ይጠራ ጀመር፡፡ በስማቸውም ዳዳ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ቤተ-ክርስቲያኑ በ2006 ኣ.ም ከጎንደር በመጡ 4 ባለሞያዎች በ60000ብር ኩንትራት በመውሰድና የአካባቢው ምዕመናን በገልበት በመርዳት በድንጋ የውጨኛው የእንጨት ስለነበር በድንጋይ፣በጭቃና በጭድ እያቀላቀሉ የውጨኛውን ቤተክርስቲያኑ አድሰውታል። ይህም ሲታደስ በበፊት የተሰሩት መቅደስና ማህሌቱ ከግንብ የተሰሩ ስለሆነ እነሱ ሳየነኩ ነው። በአሁኑ ወቅት የአካባቢው ህብረተሰብ እየተገለገለበት ይገኛል፡፡የዳዳ ተክለሃይማኖት አመታዊ ክብረ-በዓል በየአመቱ ነሃሴ 24 እና ታህሳስ 24 በደማቅ ስነ-ስረዓት ይከበራል፡፡

31/07/2022
22/07/2022

የሞባይል ሚስጥራዊ አገልግሎቶች!!
😁1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111 #
😁2ኛ. የሞባይል የተሰራበት ዘመንና ባትሪን ለማወቅ፡-* #* #4636 #* #*
😁3ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-* #06 #
😁4ኛ. የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማገኝት፡-* #0* #
😁5ኛ.የሞባይል ኮሜር መረጃ ለመግኘት፡ * #* #34971539 #* #*
😁6ኛ. ሞባይሉ ላይ ሙሉ ፋይል ለማግኛት፡-* #* #273282*255*663282* # * #*
😁7ኛ. የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት፡-* #* #232339 #* #*
😁8ኛ. ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፡-* #* #197
328640 #* #*
😁9ኛ. የሞባይልን ግልጽ ማብራት ለማየት፡-* #* #0842 #* #*
😁10ኛ. የሞባይልን የእስክር መያዥ ለማየት፡-* #* #2664 #* #*
😁11ኛ.የሞባይልኑ ቫይቭረሽን ለማየት፡-* #* #0842 #* #*
😁12ኛ.የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትወሩን ለማየት፡-* #* #1111 #* #*
😁13ኛ. የሞባይሉን ሶፍትወር እና ሃርድወር መረጃ ለማየት፡-* #125080*369 #
😁14ኛ. የሞባይሉን ኮንፍግረሽንና ዳያጎሽትክ ለማየት፡-* #9090 #
😁15ኛ. የሞባይሉን ሴታፕና ድሞድ(Dump Modef) ለማያት፡-* #9900 #
😁16ኛ. የሞባይሉን ሜኑ(HSDPA/HSUPA:- * #301279 #
😁17ኛ. የሞባይሎን ዩስፕ(USB) ለማየት፡-* #872564 #
😁18ኛ. የሞባይሎን ጽፈት ለማየት፡- * #7465625 #
😁19ኛ. የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመሜልስ፡- * #* #7780 #* #*
😁20ኛ. የሞባይሉን ወደ ፈብርካ ምርት ለመሜልስ፡-*2767*3855 #
😁21ኛ. የሞባይሎን Motorola droids ለማግኘት፡- # #776426

11/07/2022

Address

Kassaye Www, Com
Dessie
8590

Telephone

+251949917293

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kassaye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category