የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች  መምሪያ -  SWZRs Office of Revenues Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues, Government Official, South Wollo zone, Dessie.

🙏ሰ     በ  ር   ዜ  ና🙏✍️በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት የዕቅዱን 100% በላይ ገቢ  መሠብሰቡን አስታወቀ ።     ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨      ሰኔ 30/1...
08/07/2026

🙏ሰ በ ር ዜ ና🙏

✍️በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት የዕቅዱን 100% በላይ ገቢ መሠብሰቡን አስታወቀ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰኔ 30/10/2018 ዓ.ም ደሴ

✍️የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ይማም እንድሪስ በሰጡት መረጃ በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደው አጠቃላይ ገቢ 151 ሚልዮን 589 ሽ 181 ብር ሲሆን፣ እስከ ሰኔ 30 ድረስ 155 ሚልዮን ዐዐ8 ሽ 069 ብር መሰብሰብ ተችሏል። ይህም የዕቅዱን 102.31% ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።

✍️በአፈጻጸም ሂደቱም ከቃሉ ወረዳ ቀጥሎ የ2ተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል እንኳን ደስ አላችሁ

✍️ለዚሁም ዉጤት መገኘት አስተዋጽኦ ለነበራችሁ ለወረዳዉ አመራር: ለገቢ ተቋሙ ማኔጅመንትና ባለሙያዎች:ለአጋርና ባለድርሻ አካላት:ለጸጥታ አካሉና ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በሙሉ :

የደቡብ ወሎዞን ገቢዎች መምሪያ ታላቅ ምስጋና አቅርቧል።

🙏እንኳንደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🙏

@ዘገባዉ የዞኑግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራሂደት
"ግብር ለሀገር ክብር!!

"ሪፎርሙ የገቢ ተቋሙን የመፈጸም ዓቅም ይበልጥ የሚያሳድግ ነው" መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ “ነፃና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ እና የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ም...
03/07/2026

"ሪፎርሙ የገቢ ተቋሙን የመፈጸም ዓቅም ይበልጥ የሚያሳድግ ነው" መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ “ነፃና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ እና የመንግስት ሰራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ስርዓት ግንባታ” በሚሉ ሁለት ቁልፍ የሪፎርም አምዶች ላይ ያተኮረ ውይይት ከሰራተኞች ጋር አካሄዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፤ የሪፎርሙ ዋና ዓላማ የሰራተኞችን ሙያዊ እና የተቋም ብቃት ለማሳደግ አስፈላጊ ግብዓቶችን አሟልቶ የቢሮውን የመፈጸም አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ነው ብለዋል፡፡

የተቋሙ የመፈጸም ዓቅም ከዓመት ዓመት እያደገ መምጣቱን ያነሱት ቢሮ ኃላፊው፣ ይህ የሪፎርም ስራ ሙሉ በሙሉ ሲተገበር የተጣሉበትን ህዝባዊና መንግስታዊ ኃላፊነቶች በስኬት የሚያጠናቅቅ "ግዙፍ ተቋም" መገንባት እንደሚያስችልም አስገንዝበዋል።

አክለውም ሪፎርሙ በቀጣይ በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በዘላቂነት በመፍታት የክልሉን የገቢ ዓቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ሪፎርም በባህሪው በሰው ኃይል ላይ የሚካሄድ ተግባር በመሆኑ፣ ለሰራተኛው ተከታታይነት ያላቸውን ውይይቶች በማዘጋጀት የጋራ ግንዛቤና ቁርጠኝነት መፍጠር ወሳኝ ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረክ ላይ በአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የታክስ አማካሪ የሆኑት አቶ አግማስ ጫኔ እና አቶ እንግዳወርቅ ገዛኸኝ የተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

መረጃው የአማራ ገቢዎች ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው።

በአማራ ክልል 84 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበበአማራ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን 84 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ፡፡የቢሮው የኮሙኒኬሽን...
03/07/2026

በአማራ ክልል 84 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

በአማራ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን 84 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል አለ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ፡፡

የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ እንዳሉት ፥ በክልሉ ፍትሃዊ የግብር ሥርዓትን ለማስፈንና የገቢ አቅምን በመለየት አሟጦ ለመጠቀም ቴክኖሎጂ መር የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡

በዚህ መሰረትም በክልሉ ከተለያዩ ዘርፎች የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን አመልክተዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን 84 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 83 ነጥብ 9 በመቶ ማሳካት መቻሉን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 74 ነጥብ 3 ቢሊየን ብሩ ከመደበኛ ገቢ የተገኘ ሲሆን÷ 9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከከተማ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰቡን ዘመናዊ ለማድረግ በተደረገው ጥረት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡

የግብር አሰባሰቡን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡

ኤፍ ኤም ሲ

የቃሉ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ከ100 % በላይ ገቢ መሠብሰቡን አስታወቀ                              24/10/2018 ኮምቦልቻ አቶ ሰለሞን ጌቶ የቃሉ ወረዳ ገቢዎች ጽሕ...
03/07/2026

የቃሉ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ከ100 % በላይ ገቢ መሠብሰቡን አስታወቀ

24/10/2018 ኮምቦልቻ
አቶ ሰለሞን ጌቶ የቃሉ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ኃላፊ በላኩት መረጃ በበጀት ዓመቱ 218 ሚልዮን 902 ሽ 281 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ ሰኔ 24 /2019 ዓ.ም 219 ሚልዮን 920 ሽህ 281 ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል።
አፈጻጸሙ የዕቅዱን 100.5 በመቶ መሆኑን አብስረዋል!

ገቢው ከቀጥታ ከታክስ 164,885,767.16 ብር፣ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች 33,237,329.44 ብር እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 21,797,184.4 የተገኘ መሆኑን አስታውሰዋል።

ለገቢው መገኘት፤ የወረዳው የታክስ ማሻሻያና ኮሚቴና አስተባባሪ ኮሚቴ የዘረጋው ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለው የተቀናጀ አሠራር፣ የግብር ከፋዩ ቁርጠኝነት እና ማኔጅመንቱና ባለሙያው በቅንጅት በመሥራታቸው፣ የራስ ጥረት በሚጠይቁ ገቢዎች ላይ በተሻለ የስራ ተነሳሽነትና በቁርጠኝነት በመሰራቱ እና ስራን እየገመገሙ መምራት በመቻሉ መሆኑን ጽ/ቤት ሃላፊው አብራርተዋል።

በቀሪ ቀናትም ተጨማሪ ገቢ ሰብስበው ለአካባቢው እና ለክልሉ ህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ ለማበርከት እየሰሩ መሆኑን አብራርተዋል።

ዘገባው የቃሉ ወረዳ ገቢዎች ፅ/ቤት የግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን የስራ ሂደት ነው

በቀሪ ቀናት የጋራ ርብርብ በማድረግ የገቢ ዕቅዱን ማሳካት እንደሚገባ  መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) አሳሰቡሰኔ 23/2018 ዓ.ም (የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የተቋሙ...
03/07/2026

በቀሪ ቀናት የጋራ ርብርብ በማድረግ የገቢ ዕቅዱን ማሳካት እንደሚገባ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) አሳሰቡ

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ከሰራተኞች ጋር አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) በቀሪ ቀናት የጋራ ርብርብ በማድረግ የበጀት ዓመቱን የገቢ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድን ለማሳካት የገቢ ተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቢሮው እስከ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም ድረስ ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ ከ83 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ (83.4 በመቶ) ገቢ መሰብሰቡን አስታውሰው፣ በቀሪዎቹ ቀናት ርብርቡ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በተቋሙ የሚሰሩ ተግባራትን ሁሉም ሰራተኞች ተረድተው፣ የጋራ ዓላማ የሆነውን ዓመታዊ የገቢ ዕቅድ ለማሳካት እኩል መሳተፍ እና ተቀናጅተው መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፣ የቢሮውን የሪፎርም ስራ ተግባራዊ ለማድረግ የተሰየሙ የአብይ ኮሚቴ አባላት ሌት ተቀን በመስራት በጥቂት ቀናት የተሰጣቸውን ተልዕኮ አከናውነው ሪፖርት በማቅረባቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የክልሉ ገንዘብ ቢሮ እና ባለድርሻ አካላት የገቢ አሰባሰብ ጥረቱ እንዲሳካ ያደረጉት ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ የኔሰው መኮንን፡ ሪፎርም ሰፊና ብዙ ተግባራት ያሉት እና የሁሉንም ሰራተኞች ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሰራተኞች ሪፎርሙን "የእኔ ነው" ብለው እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በክልሉ የተጀመረውን ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ከሚያካሂዱ ተቋማት አንዱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ስራው በአሁኑ ወቅት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በሰው ሀብት ስራ አመራር ልማት ዋና የስራ ሂደት ዳይሬክተር በአቶ ሽመልስ አዱኛ አማካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም በአቶ አትንኩት በላይ የግብር አወሳሰን፣ አሰባሰብና ክትትል ዋና ስራ ሂደት ዳይሬክተር እና በአቶ ስንታየሁ ታደለ የገቢ ክትትልና ታክስ መረጃ አስተዳደር ቡድን መሪ አማካኝነት የቢሮው ወቅታዊ የገቢ አሰባሰብ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች ለሰራተኞቹ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

✍️፡- ሲሳይ አስማማው
📸፡-ማስተዋል ሁነኛው

አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ
በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.
በቴሌግራም:- Amhara Region revenue bureau
በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
Website:- https://www.abor.gov.et/
እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ
መደበኛ ስልክ ቁጥሮች 058 220 57 49/ 09 47

Welcome to Amhara Revenue Bureau on Facebook

በ9 ወራት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።የመም...
09/05/2026

በ9 ወራት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።

የመምሪያው አቶ አህመድ መሐመድ እንደገለጹት፤ የገቢ አሰባሰብ ሥራውን ለማጠናከር ከአመራሮች፣ ባለሙያዎችና ግብር ከፋዮች ጋር ሰፊ የግንዛቤ መድረኮች ማካሄዱን ጠቅሰው በዚህም 965 አዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ንግድ መረቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

በአፈጻጸም ኩታበር፣ ሐይቅና ቃሉ ከፍተኛ ውጤት ሲያስመዘግቡ፤ ወገልጤና፣ ደላንታና አቀስታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አሳይተዋል ሲሉም አብራርተዋል።

የሐሰተኛ ደረሰኝ ስርጭት፣ የሲስተም መቆራረጥና የፀጥታ ችግሮች በገቢ አሰባሰቡ ላይ ተግዳሮት መሆናቸውም ሃላፊው አያይዘው ገልጸዋል።

የተሰበሰበው ገቢ የትምህርት፣ ጤናና መንገድ ዘርፎችን እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው የጠቆሙት።

መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Ticktock: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uQMisH1Hd7&_r=1
Website: https://www.amharacomm.gov.et

በ9 ወራት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።የመም...
09/05/2026

በ9 ወራት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊዮን 749 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።

የመምሪያው አቶ አህመድ መሐመድ እንደገለጹት፤ የገቢ አሰባሰብ ሥራውን ለማጠናከር ከአመራሮች፣ ባለሙያዎችና ግብር ከፋዮች ጋር ሰፊ የግንዛቤ መድረኮች ማካሄዱን ጠቅሰው በዚህም 965 አዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ንግድ መረቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

በአፈጻጸም ኩታበር፣ ሐይቅና ቃሉ ከፍተኛ ውጤት ሲያስመዘግቡ፤ ወገልጤና፣ ደላንታና አቀስታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አሳይተዋል ሲሉም አብራርተዋል።

የሐሰተኛ ደረሰኝ ስርጭት፣ የሲስተም መቆራረጥና የፀጥታ ችግሮች በገቢ አሰባሰቡ ላይ ተግዳሮት መሆናቸውም ሃላፊው አያይዘው ገልጸዋል።

የተሰበሰበው ገቢ የትምህርት፣ ጤናና መንገድ ዘርፎችን እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው የጠቆሙት።

መረጃው የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/
Ticktock: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8uQMisH1Hd7&_r=1
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Ensure smooth flow of information between the Regional Government and the public and facilitate the process of building a society enriched with information

 # ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ።          "የደቡብ  ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ"  # በአሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳ...
11/04/2026

# ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ።

"የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ"

# በአሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ በዓል እንድሆንላችሁ ከልብ ይመኛል ።

# ይህ ታላቅ በዓል ለመላዉ ህዝባችንና ለንግዱ ማህበረሰብ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን፣ መተሳሰብን አንድነትን እና ፍቅርን ይዞልን እንዲመጣ ልባዊ ምኞቱን የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ በታላቅ አክብሮት ይገልጻል ።

**መልካም የፋሲካ በዓል!**

እንኳን  ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ  የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ🌙🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ የረመዳን ጾምን በጸሎትና በዒባዳ አሳልፋችሁ ...
19/03/2026

እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ🌙

🌙ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ የረመዳን ጾምን በጸሎትና በዒባዳ አሳልፋችሁ ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር እንኳን አደረሳችሁ!

🌙በዓላት ሁልጊዜም የደስታ፣ የቤተሰብ መገናኘትና የፍቅር መግለጫ መድረኮች ናቸው። የዞኑ ገቢዎች መምሪያም የዞናችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እና በራሳችን በምንሰበስበዉ ገቢም ለመመለስ ዘወትር ከጎናችሁ ነው።

🌙በመሆኑም መምሪያዉ በሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡-

1ኛ በበዓል ዋዜማ የገበያ ቦታዎች በእጅጉ ስለሚጨናነቁ እና ፈጣን ግብይቶች ስለሚፈጸሙ፣ከሀምሳ ሽህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ግብይት እንዳይፈጽሙ: ትክክለኛዉን የዲጂታል (የኤሌክትሮኒክስ) ክፍያ አማራጮችን መጠቀም ተመራጭና አስተማማኝ መሆኑን አንዘንጋ።

2ኛ በአሉን ምክናየት በማድረግ ለሚከናወኑ ግብይቶች ደረሰኝ መስጠትዎን አይዘንጉ።

🌙 በመጨረሻም፤ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ለ1447ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላም፣ የፍቅር፣ የመረዳዳት እና የደስታ በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

🌙 ዒድ ሙባረክ

"ግብራችን ለልማታችን ለሰላማችን!!



የዞኑ ግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን ስራ ሂደት

Address

South Wollo Zone
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ - SWZRs Office of Revenues posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share