05/09/2025
Visit iconic Gedeo
Mati Ai
የ5ቱ ቀለማት ትርጉም በጌዴኦ!
====================== የጌዴኦ ባህላዊ ልብስ Borro aadati uffana/ቦሮ አዳቲ ኡፋና/ቦሮ የባህል ልብስ ይባላል።
ይህ ባህላዊ ልብስ በዉስጡ 5ት የቀለም አይነቶች ያሉት ሲሆን እነርሱም....(ሰማያዊ፣ነጭ፣ቢጫ፣ቀይ፣ጥቁር) ናቸዉ።
ለመሆኑ እነዚህ 5 ቀለማት ምን ትርጉም እንዳላቸዉ አብረን እንመልከት....
======================
👉ሰማያዊ---የጌዴኦ አከባቢን ልምላሜና ጥምር ግብርናን የሚገልጽ
👉 ነጭ:- የጌዴኦ ማህበረሰብ ከምንም በላይ ሰላማዊና ሰላም ወዳድ መሆኑን የሚገልጽ ለዚህም/Gede'i nage'ake saamataan/ጌዴኢ ናጌኣኬ ሳማታን ይባላል።
👉 ቀይ:-የጌዴኦ ማህበረሰብ ሰርቶ፣ለፍቶ አዳሪ፣ በራሱ ጉልበትና ላብ የሚተዳደር፣ጀግና(የደም ታሪክን የማያወድስ ለዚህም Gondoora &Hulluussa/ጎንዶሮና ሁሉሳን የሚያደርግ) መሆኑን ለመግለጽ
👉 ቢጫ:- የማህበረሰቡ ጥንታዊ ታሪካዊ መነሻዉን(መዳዎላቡ,ሐርሱ,ሐዋጣ,ሶቾ,ሶያሞ,ሶላሞ,ጋናሌ,በኮ,ስሪሪ,ሐሮዎላቡ,ካራ,ኦዳያኣን) ለማስታወስ፣አሁናዊ ማንነቱን(በBaalle Gada/ባሌ ጋዳ ስርዓት፣በሐይቻ፣ባልተጻፈዉ ህገመንግስት/Seera/ሴራ) እንደሚመራ ለዚህም የህዝቡ ብሔራዊ መዝሙር የሆነዉን ''Fago/ፋጎ''ን በሚያዜምበት ወቅት Kulaa-Kuloo/ኩላ-ኩሎ'' በማለት ማንነቱን በዜማ የሚገልጽ ሲሆን መጻኢ ሁኔታዉን ለማመላከት....
(ካዮ ቢሬጣ ሂሴኔ,
ፋያ ቢሬካ ሂሴኔ,
ሚሳ ቢሬካ ሂሴኔ,
ሚርጋ ቢሬካ ሂሴኔ,
ጎዳ ቢሬካ ሂሴኔ) ብሎ የሚያዜም ሲሆን... የጌዴኦ ማህበረሰብ ከሁሉም ጋር በሰላምና በፍቅር ለመኖር ያለዉን መጻኢ ተስፋን ለመግለጽ
👉 ጥቁር:- በጌዴኦ ባህል ይህ ቀለም የተመረጠዉ እዉነተኛ የተፈጥሮ ሐይልን የሚያዝና ፍጹም የማይለወጥ ሐይልን ለማመላከት... (ሰማይንና ምድርን ያጸና፣ጋራ ሸንተረሩን፤የሰማይ ብርሃናትን፣ዉሓን፣የምድር ዕጽዋትን አእዋፋትንና አራዊትን፣ሰዉን የፈጠረ፣ምድር የተለያዩ ቡቃያዎችን በወቅቱ እንድታበቅል የሚያደርግ እዉነተኛ ሓይልን፣የሰዉን ልጅ ክፋት ፈጽሞ የማይወድ ለዚህም የቁጣ መዓትን የሚያወርድ፣የሚቀጣ ልመናን የሚሰማና መዓቱን የሚመልስ፣መሓሪ በደልን ይቅር የሚልና የማይቆጥር፣አድማሳትን ያጸና፣ዘላለማዊ ሀይልን ለመግለጽ ሲሆን.......
ይህን ሐይል የጌዴኦ ማህበረሰብ Mageno! ማጌኖ/ፈጣሪ,እግዚአብሔር ነዉ! ብሎ ያምናል።
👉ጥቁር ቀለምን ለዚህ ሐይል ወካይ ተደርጎ የተወሰደበት ምክንያት ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ሁሉም ነገር ምንም እንዳልነበረና ድቅድቅ ጨለማ እንደነበረ.... ነገር ግን ይህ ሐይል ዘላለም እንደነበረ ለማመላከት ነዉ።
ለዚህም ነዉ በጌዴኦ ባህል የጸሎት ስርዓት ሲጀመር (''Ee Magenoo! ኤ ማጌኖ!'') ተብሎ የሚጀመረዉ።
👉 Ee!ኤ!:- እዉነትን፣ሐቅን፣ይሁንታን፣መስማማትን ለማሳወቅና በጌዴኦ የሐሳቦችና የንግግሮች ሁሉ መክፈቻ ተደርጋ ትወሰዳለች!
👉 Magenoo!/ማጌኖ:-ዘላለማዊ የማይለዋወጥ፣የፍጥረት ሁሉ መሰረት፣ፈጣሪ፣ እዉነተኛ,እግዚአብሔር ማለት ነዉ።
ይህን ከቀደምት አባቶች፣ከዕድሜ ባለጸጋዎች ዘንድ ሰማሁ።
ምንጭ፦ ማንነቱን መግለፅ ያልፈለገ ሰዉ
ጌዴኦ page B-Family Promotion Gedeo zone GOV,CoMuncation Adane Bali Salempicture Gedeo Media Center