South Ethiopia Region Road Authority

South Ethiopia Region Road Authority Official page of South Ethiopia Region Road Authority

በዛላ ወረዳ የባዮ–ዝማ ማዕከል ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር የገጠር መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረነሐሴ 1/2018 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የ2019 በጀት ዓመት ከሚያ...
08/08/2026

በዛላ ወረዳ የባዮ–ዝማ ማዕከል ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር የገጠር መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ

ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም.

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የ2019 በጀት ዓመት ከሚያስፈጽማቸው የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል የሻምባራ–ዝማ–የላ ሻቤ መንገድ አካል የሆነው፣ የባዮ–ዝማ ማዕከል ቀበሌዎችን በማኅበረሰብ ተሳትፎ የሚያስተሳስር የገጠር መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

ይህ መንገድ ዛላ ወረዳን ከዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ጋር በሚያገናኘው ዋና መንገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በአካባቢው የመጓጓዣ አገልግሎትን በማሻሻል ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

በመንገዱ የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ እንደተናገሩት፣ መንግሥት ለመንገድ መሠረተ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ከከተማ እስከ ገጠር የሚደርሱ መንገዶችን በስፋት እየገነባ ነው ብለዋል።

በጎፋ ዞንም ወረዳዎችን ከወረዳዎች፣ ቀበሌዎችን ከቀበሌዎች የሚያገናኙ የገጠር መንገዶች በቅድሚያ እየተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የመንገድ ተደራሽነትን ማስፋት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ዳግማዊ አክለውም፣ በዛላ ወረዳ የመንገድ ተደራሽነት የህዝቡ የዘመናት ጥያቄ እንደነበር ጠቅሰው፣ የዛሬው የመንገድ ግንባታ ጅማሮ ለዚህ ጥያቄ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሣውላ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ድምሬ ድበታ በበኩላቸው፣ የመንገዱ ግንባታ ከተማውን፣ ወረዳውንና በርካታ ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር መሆኑን ገልጸው፣ በፕሮጀክቱ ውስጥ በደላሌ ወንዝ ላይ 16 ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ እንደሚገነባ ገልጸዋል።

የዛላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንበስ ሀነና በበኩላቸው፣ የመንገዱ ግንባታ ለህዝቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ መሆኑን ገልጸው፣ ፕሮጀክቱን በማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ሙሉ ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በፕሮግራሙ ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎች የመንገዱ መጀመር እንዳስደሰታቸው ተናግረው የዘመናት ጥያቄያቸው ተመልሶ ለህክምናም ይሁን ለምርት ሽያጭ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ የጎፋ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ጋሻያለው ገላ፣ የጎፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ምናሴ ኤልያስ፣የሣውላ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ድምሬ ድበታ፣ የዛላ ወረዳ አመራሮች፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት የመንገዱ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ 2018 የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯልየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ 2018 የበጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ...
05/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ 2018 የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ 2018 የበጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና ምዘና መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ ጥንካሬዎችን ለማስፋት፣ ተሞክሮዎችን ለመቀመር እንዲሁም የተስተዋሉ ድክመቶችን ለማረም ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ በ 2018 የበጀት ዓመት በፓርቲ እና በመንግስት የተከናወኑ ተግባራትን በመፈተሽ አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮ የማዘጋጀት ዓላማ እንዳለዉም ተጠቁሟል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ የበጀት ዓመቱ በመንግስት እና በፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ዉጤት የተገኘበት ነዉ ብለዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በሀገር እና በክልል ደረጃ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በስነ-ምግባር፣ በአመለካከትና በተግባር የላቀ አፈፃፀም ያላቸዉን አመራሮች ለመፍጠር እየሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የግምገማ መድረኩ በእዉነት ላይ በመቆም በበጀት ዓመቱ ሁለተኛ ግማሽ ዓመት በጥንካሬ የተለዩትን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ጉድለት የታየባቸውን ደግሞ ለማረም ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የ 2018 የበጀት ዓመት በምርጫው የተቀመጡ መንቲያ ግቦች የተሳኩበትና በመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ረገድም አመርቂ ድሎች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

በተለይም በ 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የተገኘው ስኬት "ከምርጫ ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው መድረክ በጥልቀት መገምገሙን አንስተዋል።

መድረኩ የተቀመጡ የምዘና መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የፓርቲና የመንግስት ተግባራት አፈፃፀም እንዲሁም በ 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የአመራር፣ አባላትና የሕዝቡ ሚና የሚፈትሽበት መሆኑን አስረድተዋል።

መድረኩ እስከ ታችኛው መዋቅሮች በመቀጠል ኃይል የሚሰባሰብበት ሲሆን ጠንካራ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መሆኑም ተመላክቷል።

በመድረኩ የክልሉ መንግስት አስተባባሪ አካላት፣ የክልል ማዕከል እንዲሁም የ 12ቱ ዞኖችና 3ቱ ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች አስተባባሪ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 26.2 ሚሊየን ሰዎች 805.3 ሚሊየን ችግኞችን ተክለዋል
03/08/2026

በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 26.2 ሚሊየን ሰዎች 805.3 ሚሊየን ችግኞችን ተክለዋል

የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአረንጓዴ አሻራ 2018 መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አከናወኑሐምሌ 27/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎችና ሰራተኞች በዲላና ...
03/08/2026

የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአረንጓዴ አሻራ 2018 መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አከናወኑ

ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎችና ሰራተኞች በዲላና ወናጎ ከተማ በተዘጋጀው ተከላ ቦታ በመገኘት የችግኝ ተከላ በማከናወን አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር እድሬ ኢርኮ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እና የአካባቢ መራቆትን በመቀነስ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ ጀንበር ከ69 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው የአረንጓዴ ኢትዮጵያን ግብ ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጠቁመው፣ የተተከሉት ችግኞችን ህብረተሰቡ በትኩረት ሊንከባከባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለስልጣኑ አንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በንቃት ከመሳተፋ ባሻገር ዓመታዊ ዕቅዱ አካል በማድረግ በየዓመቱ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ሥራዎች በቀጣይነት በማከናወን ለአረንጓዴ አካባቢ፣ ለዘላቂ ልማትና ለትውልድ የሚተላለፍ የተፈጥሮ ሀብት ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ እያጠናከረ ይገኛል።

"መንገድ እንገነባለን፤ አረንጓዴ አሻራ እናሳርፋለን፤ ዘላቂ ልማትን እናረጋግጣለን!"

SERA Communication

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የዲላ ክላስተር ሰራተኞች ከዲላ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱሐምሌ፣27/2018 ዲላየደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የዲላ ...
03/08/2026

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የዲላ ክላስተር ሰራተኞች ከዲላ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ

ሐምሌ፣27/2018 ዲላ

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የዲላ ክላስተር አመራሮችና ሰራተኞች ከዲላ ከተማ አስተዳደር የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከ 96 ሺህ 979 በላይ ችግኞች ለመትከል ታቅዷል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሩ በተመረጡ 34 ቦታዎች ላይ የሚከናወን ሲሆን ህብረተሰቡ ከማለዳው አንስቶ በነቂስ በመውጣት አረንጓዴ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛሉ።

በመርሃ-ግብሩ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኢድሬ ኢርኮ የከተማ አስተዳዳሩ ም/ከንቲባ አቶ ታሪኩ በየነ ፣ የጌዴኦ ፣ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ ገሪማ ፣ የከተማው ሥራ ኃላፊዎች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ክላስተር ሰራተኞችና አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል።

በሀገራችን እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፍ ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገን ነው።

የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 :00 ቆይታ የሚኖረው ነው ሲል የዘገበው የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው ።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ማለት የነገን ተስፋ ዛሬ መትከል ነው- ኢንጂነር ኢድሬ ኢርኮ ዲላ፡ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በዲላ ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በደማቅ ...
03/08/2026

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ማለት የነገን ተስፋ ዛሬ መትከል ነው- ኢንጂነር ኢድሬ ኢርኮ

ዲላ፡ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በዲላ ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የደን ሽፋንን በማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጽኑ መሠረት እየሆነ መምጣቱንም ተገልጿል።

በከተማ አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ነው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተካሄደው።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር እድሬ ኢርኮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ማለት የነገን ተስፋ ዛሬ መትከል ነው ብለዋል።

በክልሉ በአንድ ጀንበር ከ69 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ይህም የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥና የአካባቢ መራቆትን የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል።

አክለውም ችግኝ መትከል ከጊዜ ወደ ጊዜ የህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ባህል እየሆነ መምጣቱን አድንቀዋል።

የዲላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በየነ በበኩላቸው ንቅናቄው የዲላ ከተማን አረንጓዴነት ይበልጥ እያስቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል።

የተከልናቸው ችግኞች የነገ ልጆቻችንን እስትንፋስና ዕድገት የሚወስኑ ናቸው ያሉት ምክትል ከንቲባው መርሃ-ግብሩ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የበለጸገች ሀገር ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን የፍቅር የአንድነትና የወንድማማችነት እሴቶችን ይበልጥ እንዲያጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በአንድ ጀንበር ከ92 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን የገለጹት ደግሞ የዲላ ከተማ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልዬ ናቸው።

ከተተከሉት ችግኞች መካከል የደን ዛፎችና የተለያዩ ፍራፍሬዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፣ ህብረተሰቡ የተተከሉት ችግኞች ጸድቀው ፍሬ እንዲሰጡ በጥንቃቄ መንከባከብ እንዳለበት አሳስበዋል።

የጌዴኦ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገሪማ በመድረኩ ላይ ተገኝተው እንዳስተላለፉት፤ ችግኝ መትከልና የተፈጥሮ አካባቢን መጠበቅ በሃይማኖትም በእጅጉ የሚደገፍ ተግባር ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የጌዴኦ ህዝብ ደን ውስጥ እየኖረ ደንን ያኖረ ለዓለም ትልቅ ተሞክሮ መሆን የሚችል ማህበረሰብ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው የአሁኑ ትውልድም ይህንን በጎ ባህል በማስቀጠል የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ መክረዋል።

ቤተክርስቲያኗም ምዕመኖቿን በማስተባበር የድርሻዋን እንደተወጣች አረጋግጠዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በአንድ ጀንበር ከ90 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን የገለጹት የዲላ ከተማ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልዬ ከተተከሉት የደን ዛፎችና ፍራፍሬዎች መካከል አብዛኛዎቹ እንዲጸድቁ ከተፈለገ ህብረተሰቡ የተከላውን ያህል ለእንክብካቤውም ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት በአጽንዖት አሳስበዋል።

በዚህ ደማቅ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የከተማው የሥራ ኃላፊዎች፣የሃይማኖትና የባህል አባቶች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ተሳትፈዋል።

በዚህ ደማቅ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የከተማው የሥራ ኃላፊዎች የሃይማኖትና የባህል አባቶች እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው መሳተፋቸውን የዲላ ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዘገባ ያመላክታል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ በወላይታ ዞን የአንድ ጀንበር ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል    ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ በ...
03/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ በወላይታ ዞን የአንድ ጀንበር ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በክልሉ በወላይታ ዞን፤ በዳሞት ጋሌ ወረዳ ሻኪሾ ሾኔ ቀበሌ የዘንድሮው ሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በክልሉ "ተስፋን እንተክላለን" በሚል መሪ ሃሳብ በመከናወን ላይ ለሚገኘው የዘንድሮ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አስቀድሞ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ተከላው በዛሬው ዕለት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ በልዩ ትኩረት የሚከናወን ይሆናል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የአንድ ጀንበር ተከላውን አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር በይፋ የሚያስጀምሩ ሲሆን፤ በመላው የክልሉ ህዝብ ግንባር ቀደም ተሳትፎ 69 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል እንደ ሀገር 800 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ለተያዘው ግብ ስኬት የጎላ አስትዋጽኦ በማበርከት ሌላ ታሪክ ለማስመዝገብ ርብርብ የሚደረግ ይሆናል፡፡

በዛሬው የአንድ ጀንበር ተከላ የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ችግኞች፤ በርግጥም አረንጓዴ አሻራ ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ምርታማነትን የማሳዳግ፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

ለዚህም የአግሮ ፎረስትሪ ዛፎችን ጨምሮ የአቮካዶ፣ የፓፓያ፣ የማንጎና የአፕል የፍራፍሬ ችግኞች እንዲሁም የቡና፤ የእንሰት እና ለሎች የመኖ እፅዋት፣ የጥላና የጌጥ ዛፍ ችግኞች ለተከላው መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡

በክልሉ በአምናው የ2017 ዓ.ም የአንድ ጀንበር ተከላ፤ 60 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ተፈጥሮን መንከባከብ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በውል በተረዳው በክልሉ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ፤ ከዕቅድ በላይ 69 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሉ የሚታወስ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም በተመሳሳይ በወጣቶች፤ ተማሪዎች፤ ሴቶች፤ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሠራተኞች፤ የንግዱ ህብረተሰብ፤ የኃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ የፀጥታ አካላት እና አርሶ አደሮችን ጨምሮ በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የላቀ ተሳትፎ ዳግም ተስፋን በመትከል ሌላ ደማቅ የወል ታሪክ ይጻፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለተከላው ጆግራፊያዊ መገኛቸው በጂኦ-ሎኬሽን የተመላከተ 1 ሺህ 345 የተከላ ቦታዎች የተዘጋጁ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በዕለቱ የአንድ ጀንበር ተከላ መርሃ ግብር 16 ሺህ 861 ሄ/ር መሬት በተከላው የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የክልሉ መንግስት ባለፉ ጊዜያት ለአረንጓዴ አሻራ እና ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፤ በክልሉ የደን ሽፋን ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ከመቻሉም በላይ የአፈርና የውሀ ሀብትን በማጎልበት ምርታማነትን በማሳደጉ ረገድ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

03/08/2026
ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ታሪክ የሚሰሩበት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ ይተገበራል
03/08/2026

ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ታሪክ የሚሰሩበት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ ይተገበራል

ባለስልጣኑ በ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በንቃት ይሳተፋልበክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገራችን በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ...
02/08/2026

ባለስልጣኑ በ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በንቃት ይሳተፋል

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገራችን በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምን፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን እና የአርሶ አደሩን ገቢ በማሳደግ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

በነገው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ 800 ሚሊዮን ችግኞች፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደግሞ ከ69 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል የተያዘውን ታላቅ ግብ ለማሳካት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች ሁሉንም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በማጠናቀቅ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ ሆነዋል።

ባለስልጣኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን እንደ አንድ ጊዜ ተግባር ሳይሆን የዓመታዊ ዕቅዱ አካል በማድረግ፣ በየዓመቱ በችግኝ ተከላና በችግኞች እንክብካቤ ሥራዎች በቁርጠኝነት በመሳተፍ አረንጓዴና ዘላቂ አካባቢን ለመገንባት አስተዋጽኦውን በቀጣይነት እያበረከተ ይገኛል።
# ለነገ ተስፋን_እንትከል

Address

Dilla Front Of Donbosko School
Dilla
P.O.BOX404

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Road Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share