Kedir Yasin Abdella

Kedir Yasin Abdella ያአላህ ለተፈጠርኩበት ዓላማ ኖሬ የሚያልፍ ባሪያህ እንድታደርገኝ ዘንድ እማፀንሃለሁ!!!

06/03/2026
28/01/2026
03/01/2026
09/12/2025
30/08/2025
03/07/2025
ለሁለት ቀናት ስሰጥ የነበረዉ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና  ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቀዋል።በ2017 የትምህርት ዘመን በወረዳችን  በስድስት የፈተና ጣቢያዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የ...
18/06/2025

ለሁለት ቀናት ስሰጥ የነበረዉ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቀዋል።

በ2017 የትምህርት ዘመን በወረዳችን በስድስት የፈተና ጣቢያዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም አጠናቅቀናል።

ፈተናው ከኩረጃ ነፃ በሆነ መልኩ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የተሰጠ ሲሆን ተማሪዎች የየራሳቸዉን ስሰሩ የነበሩበት መሆኖን ባደረግናቸዉ ምልከታዎች ለማረጋገጥ ችለናል።

አጠቃላይ የፈተና ሂደቱ ተጠናቆ የተማሪዎች መልስ መስጫ ወረቀት ከሁሉም ጣቢያ ወደ ማዕከሉ ተሰብስበዋል።

በዚህ ዓመት ያስፈተንናቸዉ 821 ተማሪዎች በ17 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ስማሩ የነበሩ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 95.2% ፈተና ላይ ተቀምጠዉ ቀሪ ተማሪዎች በተለያዩ ማህበራዊ ምክንያቶች ትምህርታቸዉን አቋርጠዋል።

የፈተና ህግጋቶች ተጠብቆ ፈተናዉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት እንድጠናቀቅ ሙያዊ ድጋፍ ላደረጋችሁ ለትምህርት ባለሙያዎች፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት፣

የወረዳ መንግስትና ኮማንድ ፖስት አባላት፣የፀጥታ አስከባሪ አካላት፣የዞን ደጋፊ ባለሙያዎችና አመራሮች፣የሚዲያ አካላት፣የወረዳ ፖለቲካ አመራሮች፣ዓመታትን ለፍታችሁ ተማሪዎችን ለዚህ ደረጃ ላበቃችሁ ለዕውቀት አባቶች ወይም መምህራን እና በየደረጃ ላላችሁ ለተግባሩ መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ሁሉ በጽ/ቤቱ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ልያቀርብላችሁ እወዳለሁ።

በመጨረሻም ተማሪዎች በክረምት ወቅት ከማንበብ ሳትዘናጉ በማንበብ እንዲትተጉና ወላጆችም እንዲደግፉኣቸዉ መልዕክተን እያስተላለፍኩ መልካም ዉጤት እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኛለሁ።

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሚሰጠዉ ለሀገር ዓቀፍ ፈተና አስፈላጊውን ሁሉ ቅድሜ ዝግጅት ተጠናቀዋል።ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ስከታተሉ ቆንተዉ በዕውቀታቸዉ ልክ በመመዘን ወደ ቀጣይ የክፍል ደረጃ ለ...
09/06/2025

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሚሰጠዉ ለሀገር ዓቀፍ ፈተና አስፈላጊውን ሁሉ ቅድሜ ዝግጅት ተጠናቀዋል።

ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ስከታተሉ ቆንተዉ በዕውቀታቸዉ ልክ በመመዘን ወደ ቀጣይ የክፍል ደረጃ ለመሻገር የሚያስችላቸዉን የመካከለኛደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 3/2017 ጀምሮ ይፈተናሉ።

የተማሪዎች፣የመምህራን፣የትምህርት ቤት አመራር እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ልፋት ፍሬያማነቱ የሚረጋገጠዉ በተማሪዎች ዉጤት መሻሻል ነዉ።

ይህንኑ ዕውን ለማድረግ መምህራኖች ከመደበኛ ክፍል ጊዜያቸዉ ባሻገር ጊዜያቸዉንና ዕውቀታቸዉን ሳይሰስቱ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትም ሆነ ሙያዊ የሚፈቅደዉን በመፈፀም ስሰሩ የቆዩ ሲሆን የትምህርት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎችም ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተሰርተዋል።

ለትምህርት ጥራትና ለተማሪዎች ዉጤት መሻሻል ብቁ የሰዉ ኃይልን ከመመደብ በተጨማሪ የግብዓት አቅርቦትናፈ እና ለትምህርቱ ማህበረሰብ ምቹና ማራክ የሆነ የትምህርት ሥፍራን ማዘጋጀት ሁነኛ ተግባራቶች ናቸዉ።

ለዚህም በተያዘዉ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለማብቃት በጽ/ቤቱ እና በወረዳ መንግስት ከ327ሺህ ብር በላን በሆነ ገንዘብ በአድሱ ሥርዓት ትምህርት የተቀረፁ የተለያዩ ማጣቀሻ መፅሐፍቶችን ገስተን ተማሪዎች አንብበዉ እራሳቸዉን እንዲያዘጋጁ አድርገናል።

ከነገ ከሰኔ 3 ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለሚሰጠዉ ለ8ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ ፈተና ተማሪዎችን በህልና ከማዘጋጀት ጀምሮ የፈተና ሂደቱን ለማሳለጥ በቅንጅት ለመሥራት ከተዋቀረ ኮማንድ ፖስት ጋር በመጣመር አስፈላጊውን ሁሉ ቅድሜ ዝግጅት አጠናቂቀናል።

በ2017 የትምህርት ዘመን እንደ ቡሌ ወረዳ በአሥራ አራት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስማሩ የቆዩ 698 ተማሪዎች በሶስት ማዕከላት ፈተናዉን ለመውሰድ ዝግጁ ሆነዋል።

ለዚህም በዛሬዉ ዕለት በፈተና ህግጋቶች ዙሪያ ፈተናዉን ለማስፈፀም ኃላፊነት ከተሰጣቸዉ ከሚመለከታቸዉ አካላት በኩል ኦሬንተሽን ወይም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በክህሎት፣በአመለካከት እና በዕውቀት የተገነቡ ዜጎች ለሀገር እንድበቁ በማድረግ የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት የተወጣችሁ በየደረጃ ያላችሁ የትምህርት ባለድርሻ አካላትን እያመሰገንኩ የፈተና ሂደቱ ተጀምሮ እስክጠናቀቅም ጭምር የሚጠበቅባችሁን ሁሉ በተገቢ እንድትወጡ አሳስባለሁ።

ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት እንድተገብሩ የተሰጣቸዉን ህግጋቶችን በሙሉ በማክበር የተፈቀደላቸዉን ሰዓት በአግባቡ እንድጠቀሙ እና በራስ መተማመን መንፈስ እንድፈተኑ መልዕክተን እያስተላለፍኩ በዉጤት የሚታጀቡበት መልካም ፈተና እንድሆን እመኛለሁ።

Address

BULE➙ DILLA➙ GEDE'O
Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kedir Yasin Abdella posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share