Dire Dawa Police

Dire Dawa Police የድሬዳዋ ፖሊስ ራዕይ::
👉በ2022 በኢትዮጵያ በላቀ ሙያዊ ብቃት ቀዳሚ የፖሊስ ተቋም ሆኖ ማየት::

This is the official page of the Dire Dawa Police Department
ይህ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ኦፊሻል የፌስብ ቡክ ገፅ ነው።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በ2018 ዓ.ም የላቀ የስራ አፈጻጸም ውጤት ላስመዘገቡ አባላት እውቅና ሰጠ።​የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ...
29/08/2026

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በ2018 ዓ.ም የላቀ የስራ አፈጻጸም ውጤት ላስመዘገቡ አባላት እውቅና ሰጠ።

​የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ላይ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በ2018 ዓ.ም ውስጥ ህብረተሰቡንና አሽከርካሪዎችን በማስተባበር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ላከናወናቸው አበረታች ስራዎች እውቅና እና ምስጋና የሚሰጥበትን መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሄዷል።

​በመርሀ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አብድ ሙክታር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ከሪማ አሊ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ም/ኮምሽነር ጉሌድ ድርዬ እና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ ስራ ሀላፊዎች፣ ዳይሮክተሬቶች የፖሊስ ጣቢያ ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አጋዥ አካላት ተገኝተዋል።

​የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ ከባድ የትራፊክ ቁጥጥር አመራርና አባላት የዝናብና የፀሀይ ግለት ሳይበግራቸው በከተማችን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ህይወትና ንብረት ለማዳን እያከናወኑት ያለው የሚደነቅ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥብቅ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

አክለውም ትራፊክ ፖሊሶች የህግ የበላይነትን ከማክበር ጎን ለጎን ለአሽከርካሪዎች እና ለእግረኞች አርዓያ በመሆን በየዕለቱ የሚያሳዩት የላቀ የሙያ ስነ-ምግባርና ጽናት የከተማችንን ሰላም እና ጸጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ላላቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ልዩ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ምክትል ኮምሽነር ጉሌድ ድርዬ በበኩላቸው፣ በአስተዳደራችን የትራፊክ አደጋን በዘላቂነት ለማስቀረት ከአጋዥ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማችን እየተከናወነ ያለው ዘመናዊ የኮሪደር ልማት ግንባታ ሰፊና የተስተካከሉ ተሽከርካሪና የእግረኛ ምቹ መንገዶችን በመፍጠሩ የትራፊክ ፍሰቱን ለማሻሻልና አደጋዎችን ለመከላከል ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ተናግረዋል።

​ምክትል ኮምሽነሩ አክለውም፣ እንዲህ አይነት የምስጋና መርሃ ግብሮች መዘጋጀታቸው የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አመራርና አባላት ለቀጣይ ዓመታት የሚኖራቸውን የስራ ተነሳሽነትና የዲሲፕሊን ጥረት በእጥፍ እንደሚያሳድገውና ህብረተሰቡም ከፖሊስ ጎን ሆኖ ስራዎችን እንዲደግፍ የሚያደርግ ትልቅ መነቃቃት እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ሰአዳ መሀመድ በበኩላቸው፣ በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ ዋና ዋና የስራ አፈፃፀሞችን አቅርበዋል። ዳይሬክተሯ በመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ላይ ትኩረት ተደርጎ በከተማና በገጠር አካባቢዎች ሰፊ የህዝብ ንቅናቄና የትምህርት መድረኮች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም የፍጥነት ወሰን ጥሰትን በመቆጣጠር፣ እና የተሽከርካሪዎችን ቴክኒካል ብቃት በየጊዜው በመፈተሽ ከባድ እና ቀለል ያሉ የትራፊክ አደጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀነሱ የተደረገባቸውን ስልታዊ እንቅስቃሴዎች በዝርዝር አስረድተዋል።

​በመርሀ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ በ 2018 ዓ/ም በተከናወኑ የቁጥጥር ስራዎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የትራፊክ ቁጥጥር አመራርና አባላት እንዲሁም ለአጋር ተቋማት የእውቅናና የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል።

=================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

በመልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ አዘጋጅነት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የተደረገው የ“ኮሚሽነሩ ቡና ጠጡ” መድረክ በዛሬው ዕለት ተከናወነ ።​ሕዝብንና ፖሊስን በይበልጥ የሚያቀራርብ፣ የመልካም አስተ...
27/08/2026

በመልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ አዘጋጅነት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የተደረገው የ“ኮሚሽነሩ ቡና ጠጡ” መድረክ በዛሬው ዕለት ተከናወነ ።

​ሕዝብንና ፖሊስን በይበልጥ የሚያቀራርብ፣ የመልካም አስተዳደርና የፀጥታ ጥያቄዎች በቀጥታ የሚፈቱበት አዲስ አሰራር በድሬዳዋ አስተዳደር መልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ ተጀመረ።

​በመልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ አስተባባሪነት ከአካባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የተካሄደው ይህ የውይይት መድረክ ዋና ዓላማ ማህበረሰቡ በቀጥታ የሚያጋጥሙትን የጸጥታ ስጋቶች፣ የወንጀል መከላከል ክፍተቶች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በቀጥታ ለሚመለከታቸው የፖሊስ አመራሮች አቅርቦ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው።

“የኮሚሽነሩ ቡና ጠጡ” በሚል ማራኪ ስያሜ የተጠራው ይህ መድረክ፣ ከቢሮ ውጪ በባህላዊ እና ወዳጃዊ መንፈስ በመወያየት የህዝብና የፖሊስን ትብብር ወደር የሌለው ደረጃ ለማድረስ ያለመ ነው።

​በዚህ ታሪካዊ የምክክር መድረክ ላይ የደሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ይሄነው ሺፈራው፣ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ታክቲክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ምስራቅ ተሻገር፣ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ትግስት ተሾመ፣ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ሰአዳ መሀመድ የጣቢያው ሀላፊ ኢንስፔክተር ሠላም ወርቁ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።

​በውይይቱ መድረክ ላይ የተገኙት የ01 ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በአካባቢያቸው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ የጸጥታ ስጋቶችን እና አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ የፖሊስ አገልግሎት ጥያቄዎችን አንስተዋል።

ነዋሪዎቹ ባነሷቸው ሀሳቦች በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ የፖሊስ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እና የክንውን መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

​የህብረተሰቡ ተወካዮች አክለውም፣ ውይይቱ ከተለመደው የቢሮ ስብሰባ ወጥቶ በቡና መድረክ መዘጋጀቱ እና የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ሰፊውን ማህበረሰብ ያካተተ መሆኑ የሰላምና ጸጥታ ስራዎችን በባለቤትነት ለመምራት ትልቅ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ይህ መልካም ተሞክሮ በሌሎችም አካባቢዎች በስፋት ሊሰፋ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

​በመድረኩ ለተነሱት የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የፖሊስ አመራሮቹ አጠቃላይ ማብራሪያዎችን እና ምላሾችን ሰጥተዋል።

አመራሮቹ በሰጡት ምላሽ፣ የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ከማረጋገጥ አንፃር ከማህበረሰቡ ጋር የሚደረገው አጋርነት ይበልጥ እንደሚጠናከር ገልጸዋል። በተለይም አነስተኛ የሚባሉ ነገር ግን ህብረተሰቡን ሲያማርሩ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሎ በመጣል፣ የህዝብን እርካታ የሚያረጋግጥ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

​ዛሬ በመልካ ጀብዱ ፖሊስ ጣቢያ የተጀመረው ይህ ህዝባዊ የውይይትና የ“ቡና ጠጡ” መድረክ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በየጊዜው እየተገመገመ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ከወጣው አቅጣጫ ለመረዳት ተችሏል።

=================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

ለድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን እውቅና ተሰጠው!«ግብር ለአገር ክብር!» በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ተዘጋጅቶት የነበረው የ...
26/08/2026

ለድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን እውቅና ተሰጠው!

«ግብር ለአገር ክብር!» በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ተዘጋጅቶት የነበረው የክብርና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር፣ የከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የከተማዋ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከድሬዳዋ ገቢዎች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለህግ የበላይነት መከበር፣ ለሰላምና ጸጥታ አስተማማኝነት እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ በስኬት እንዲካሄድ ላበረከተው ከፍተኛ እና አንጸባራቂ አስተዋጽኦ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የፖሊስ ሰራዊቱ የዜጎችን ሰላም ከማስጠበቅ ባሻገር የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና የልማት መሰረቶች ከጎን በመሆን በማስጠበቅ ረገድ የሚያበረክተው ሚና የላቀ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፤ ተቋሙም ላከናወነው አርአያነት ያለው ተግባር የክብር ዋንጫ ተበርክቶለታል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር በመድረኩ ላይ ባደረጉት ሰፊ ንግግር፤ ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ ከመሆንም በላይ ለሀገር እድገት እና ለነጻነት ዋስትና ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

አያይዘውም የሀገሪቷ መሰረተ ልማቶች እንዲፋጠኑ፣ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እና የከተማችን ሁለተናዊ ብልጽግና እውን እንዲሆን ግብርን በታማኝነት መክፈል እንደ መልካም ባህል እና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡን በማስተባበርና ሰላምን በማጽናት የልማት አጋርነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ።

#ድሬዳዋ #ፖሊስ #ልማት #ሰላም #እውቅና

=================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

25/08/2026

"ፖሊስነት ማለት በልብ ሙሉነት፣ በአእምሮ ብሩህነት፣ በእጅ ንጹህነት ህዝብን ማገልገል ነው"
— ኮሚሽነር አለሙ መግራ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣​እንኳን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ !​ይህ ታላቁ በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላች...
25/08/2026

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣

​እንኳን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ !

​ይህ ታላቁ በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

በዓሉ በተለመደው የወንድማማችነት፣ የእርስ በርስ የመዋደድና የመረዳዳት እሴቶቻችን እና ሰላማችንን አስጠብቀን እንድናሳልፍ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያስተላልፋል።

​መልካም በዓል!
— የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ —

 !!የድሬዳዋ ፖሊስ መረጃ መቀቢያ ክፍል ለህብረተሰቡ ደህንነት እና ጸጥታ በግንባር ቀደምትነት ላይ!የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመረጃ መቀቢያ ክፍል አባላት 24 ሰዓት ሙሉ (7/24) በ...
22/08/2026

!!

የድሬዳዋ ፖሊስ መረጃ መቀቢያ ክፍል ለህብረተሰቡ ደህንነት እና ጸጥታ በግንባር ቀደምትነት ላይ!

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመረጃ መቀቢያ ክፍል አባላት 24 ሰዓት ሙሉ (7/24) በንቃት በሥራ ላይ ይገኛሉ።

ከህብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎችን እና መረጃዎችን በፍጥነት በመቀበል ለሚመለከተው የሥራ ክፍል በማስተላለፍ ላይ ያሉት እነዚህ አባላት፣ ህብረተሰቡ የትኛውንም የድንገተኛ አደጋ ወይም የጸጥታ ችግር ሳያጋጥመው ፈጣን እና ቀልጣፋ የፖሊስ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

የህግ ማስከበር ሥራው ውጤታማ የሚሆነው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ባለው ጠንካራ መተማመን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በሰዓቱ ማድረስ ሲችል ነው። በዚህ ረገድ የመረጃ መቀቢያ ክፍል ሠራተኞች የህዝብን እና የፖሊስን ግንኙነት በማስተሳሰር፣ ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት በመከላከል እና አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሂደት ውስጥ የጀርባ አጥንት በመሆን የላቀ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ።

📞 !
ማህበረሰባችን ድንገት የድሬዳዋ ፖሊስ አገልግሎት ቢያስፈልግዎ፣ ማንኛውንም የጸጥታ ወይም የድንገተኛ ጊዜ መረጃ በፍጥነት ለማድረስ 620 አጭር ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ፈጣን የፖሊስ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

22/08/2026
21/08/2026

1. የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አጭር የስልክ መስመር ስንት ነው?
2. ​በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ሪፖርት ማድረጊያ እና ጥቆማ መቀበያ አጭር የስልክ ቁጥር ስንት ነው?

​መልስ ይስጡ፣ ይሸለሙ! 🏆
እነዚህን ቁጥሮች በትክክል በማወቅ ለህብረተሰቡ ደህንነት እና ለህግ ማስከበር ስራ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበርክቱ፤ አሸናፊም ይሁኑ!

20/08/2026

የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ ማህበር አባላት ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ ሰፊ የዘመቻ ስራ አከናወኑ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ የቀጣይ መቶ ቀን እቅድ አፈፃፀም ላይ ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አባላት ጋር ውይይት አካሄደየድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መ...
20/08/2026

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ የቀጣይ መቶ ቀን እቅድ አፈፃፀም ላይ ከማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ በስሩ ከሚገኙ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የስራ ክፍሎች እና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ከሚገኙ ኦፊሰሮች ጋር በተቋሙ የተቀመጠውን ቀጣይ የመቶ ቀን እቅድ ትግበራና አፈፃፀም አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ተወካይ ኃላፊ እና የወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ይሄነው ሽፈራው፤ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ህዝብንና ፖሊስን የሚያቀራርብ ወሳኝ ድልድይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮማንደሩ አያይዘውም የኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ጽንሰ-ሀሳብ ዋና ዓላማ የፀጥታ አካላትና ህዝቡ በጋራ በመመካከር የወንጀል ስጋቶችን በምንጭ ደረጃ ማድረቅ እንደሆነ ጠቁመው፣ እቅዱን ስኬታማ ለማድረግ ለወንጀል ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚችሉ አካባቢዎችን ቅድሚያ ሰጥቶ በማስወገድ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ድሬዳዋን ከወንጀል የፀዳች ከተማ ለማድረግ እና የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት አደንዛዥ እጾች፣ ህገ-ወጥ የሺሻ ቤቶች እና ለተለያዩ ወንጀሎች መንስኤ የሚሆኑ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ማደረግ ፣የወንጀል መከላከል ስራዎችን በብቃት ለማከናወን የጥበቃና የሮንድ ስራዎች ይበልጥ አጠናክረው በማስቀጠል ሁሉም አባልና አመራር ለእቅዱ ስኬታማነት ከአሁኑ በመዘጋጀት ድርሻውን መወጣት አለበትም ብለዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ኮማንደር ሙና ጀማል በበኩላቸው፣ ኦፊሰሮች ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመስራት ማህበራዊ ትስስሮች
ማጠናከር እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። ቀደም ሲል በስራ አፈፃፀም ላይ የታዩ ድክመቶችን በማረም የተሻለና ሞዴል የሆነ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲንግ ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ተናግረዋል።

በመከላከል ዘርፍ ስር የሚገኙ አመራሮች በሰጡት አስተያየት፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች ለሰላምና ጸጥታ መረጋገጥ ያላቸውን ትልቅ ሚና አንስተው፤ ኦፊሰሮችን በመደገፍና በቅንጅት በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የመቶ ቀን እቅዱን በብቃት ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊ ክፍሎች የክትትልና ድጋፍ ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።
=================
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#በፌስቡክ:-👇
📌በአማረኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100071007202116

📌በኦሮምኛ :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100068806916386

📌ስፖርት :-https://www.facebook.com/profile.php?id=100063887688997

📌ዩትዩብ፦https://youtube.com/?feature=shared

📌በቴሌግራም ቻናላችን
👉https://t.me/direpoli

📌ቲክቶክ፦https://www.tiktok.com/?_t=8fY2fIbUgSs&_r=1

፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Address

Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Police:

Shortcuts

Share