የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office

የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ  Diredawa Justice Security and Law Affairs Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office, Government Organization, Dire Dawa.

23/08/2026
የፍትህ ጸጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ እና  የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የኦዲት ሪፖርት የሂሪንግ መድረክ ተካሄደ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ ...
19/08/2026

የፍትህ ጸጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ እና የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የኦዲት ሪፖርት የሂሪንግ መድረክ ተካሄደ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት ባካሄደው የኦዲት ሂሪንግ መድረክም የሁለቱን ተቋማት የ2016 እና የ2017 በጀት አመት የፋይናንሻል ኦዲት መድረክ የቋሚ ኮሚቴው አባላትና የተቋማቱ አመራሮች እንዲሁም የዋና ኦዲተር መ/ቤት ኦዲተሮች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡

በመሆኑም የተቋማቱ የፋይናንሻል ግኝት ሪፖርት በቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር ቀርቦ በተቋም አመራሮች ምላሽ ከተሰጠበት በኋላ በኦዲተሮች ሙያዊ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡

የመድረኩን የማጠቃለያ አቅጣጫ የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ የፍትህና ጸጥታ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮን በተመለከተ ተሰብሳቢ ሂሳብ ላይ ጥሩ ለውጥ መታየቱን ገልጸው የተቋሙን የበጀት ፍሰት በተመለከተ የፋይናንስ ክፍል ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የአነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽንን በተመለከተም ለኦዲት የሚቀርቡ ሰነዶች የተሟሉ መሆን እንዳለባቸው ፣ የተሰብሳቢ ሂሳብን ዜሮ ለማድረግ መሰራት እዳለበት አቅጣጫ ሰጥተውበታል ፡፡
{ምንጭ የአስተዳደሩ ም/ቤት ህ/ግ}

05/08/2026
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፦ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመት...
03/08/2026

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

፦ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።

በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡

በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ከድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ #| ሐምሌ 22 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ::::::ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እና ድረ-ገጾች ላይ የአስተዳደ...
29/07/2026

ከድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ

#| ሐምሌ 22 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
::::::
ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እና ድረ-ገጾች ላይ የአስተዳደሩን ከፍተኛ አመራሮች ስም በመጥቀስ "ሚስጥራዊ ስብሰባ ተደረገ፣ የብሔር እና የጥቅም ክፍፍል ተነሳ" እየተባሉ የሚናፈሱት ወሬዎች ሙሉ በሙሉ መሰረተ-ቢስ፣ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬዎች መሆናቸውን ለድሬዳዋ እና ለመላው የሀገራችን ህዝብ በጽኑ ልናረጋግጥ እንወዳለን።

የተባለው አይነት ምንም አይነት ስብሰባም ሆነ የተነሳ አጀንዳ በጭራሽ የሌለ ሲሆን ይህ የበሬ ወለደ ታሪክ ከተማዋን እና አመራሩን ለማጠልሸት የተወረወረ ከንቱ የፈጠራ ወሬ ነው።

ድሬዳዋ ከጥንት ጀምሮ የብሔር፣ የቋንቋ እና የሃይማኖት ልዩነት ሳይበግራት ህዝቦቿ በሰላም፣ በፍቅር እና በመከባበር የኖሩባት የሁላችንም ኩራትና የፍቅር ማዕከል ናት። በከተማችን ውስጥ የእገሌ እና የእገሌ የሚባል የብሔር ድንበር የሌለ ሲሆን ድሬዳዋ ሁሌም የሁሉም የጋራ ቤት ሆና ትቀጥላለች።

ይህንን የዘመናት የአብሮነት እሴት በሀሰተኛ ወሬዎች ለመናድ መሞከር የድሬዳዋን ህዝብ ስነ-ልቦና ካለመረዳት የሚመነጭ ከንቱ ጥረት ነው። በአስተዳደራችን ውስጥ የፖለቲካም ሆነ የሥራ ሹመት የሚሰጠው በችሎታ፣ በዕውቀት፣ በታማኝነት እና ህዝብን ለማገልገል ባለ ዝግጁነት ላይ ብቻ ተመስርቶ ነው። ስልጣን የህዝብ ታላቅ አደራ እና ንጹህ አገልጋይነት እንጂ በአሉባልታ እንደሚወራው ጠያቂ የሌለው የሀብት ማከማቻ ሊሆን አይችልም።

የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ሌት ተቀን በቁርጠኝነት የሚሰሩትና ሚወያዩት ስለ ስልጣን ሽኩቻ ሳይሆን የድሬዳዋን ልማትና የብልፅግና ግስጋሴ ስለሚያፋጥኑ ስራዎች ፣ ስለ መሰረተ-ልማት ግንባታዎች እና የህዝባችንን የኑሮ ውድነት ስለሚያቃልሉ ተግባራት ብቻ ነው።

የድሬዳዋ አመራር በአሁኑ ወቅት የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ እጅግ በጣም ስራ በዝቶበት በትጋት እየሰራ በመሆኑ ለአሉባልታና ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ የሚባክን አንድም ሰከንድ የለውም።

በከተማችን ውስጥ የሃሳብ ነፃነት እና የፖለቲካ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፊና ዲሞክራሲያዊ ቢሆንም ይህ ሰፊ ምህዳር ግን ህዝብን በብሔር ለመከፋፈልና ጥላቻን ለመዝራት ለሚንቀሳቀሱ አካላት መሸሸጊያ አይሆንም።

ስለዚህ የፈጠራ ታሪክ በማናፈስ የድሬዳዋን ስም ለማጠልሸት እና ህዝብን ለማደናገር የምትሞክሩ የአሉባልታ ነጋዴዎች ከአፍራሽ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ አስተዳደሩ በጥብቅ ያሳስባል።

የድሬዳዋ ህዝብ ንቁ፣ አስተዋይና የሀሰት ወሬዎችን ከእውነት መለየት የሚችል በመሆኑ በሴራችሁ አይታለልም፤ የአስተዳደሩም ከተማዋን ወደ ላቀ ከፍታ ለማድረስ ከህዝቡ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ስራውን በቁርጠኝነት ይቀጥላል። ድሬዳዋ የፍቅር፣ የሰላም እና የሁሉም ከተማ ሆና ለዘላለም ትኖራለች።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

28/07/2026
 #መግለጫ:- ከድሬዳዋ አስተዳደር የሰጠው አስቸኳይ መግለጫ | ሐምሌ 13/2018ከአስተዳደሩ ዕውቅና ውጪ በሚደረጉ ሕገ-ወጥ የሙዚቃ ኮንሰርቶችና የትኬት ሽያጮች ላይ የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ...
20/07/2026

#መግለጫ:- ከድሬዳዋ አስተዳደር የሰጠው አስቸኳይ መግለጫ
| ሐምሌ 13/2018

ከአስተዳደሩ ዕውቅና ውጪ በሚደረጉ ሕገ-ወጥ የሙዚቃ ኮንሰርቶችና የትኬት ሽያጮች ላይ የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ
;::::::::
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ፣ እንዲሁም የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የተለያዩ ቁጥጥሮችንና የአሰራር ስርዓቶችን ዘርግቶ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

ከዚህ አንጻር በአሁኑ ወቅት በአስተዳደሩ ዕውቅናና ፈቃድ ሳይሰጣቸው የሚዘጋጁ የሙዚቃ ድግሶች (ኮንሰርቶች) እና ተያያዥ የትኬት ሽያጮች እየታዩ ይገኛሉ። በተለይም በአስተዳደሩ እውቅና ያልተሰጠውና በፈረንጆቹ July 25, 2026 (ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም) ሊካሄድ ታቅዶ ትኬቱ እየተሸጠ የሚገኝ የኮንሰርት ዝግጅትን ጨምሮ፣ መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመግታት አስተዳደሩ ይህንን ጥብቅ መግለጫ አውጥቷል።

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

የፈቃድ ግዴታ፦ ከአስተዳደሩ ዕውቅናና ሕጋዊ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም ዓይነት የሙዚቃ ድግስም ሆነ የኮንሰርት ዝግጅት ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ለማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ፦ ሕዝባችን ይፋዊ ዕውቅና የሌላቸውንና ሕገ-ወጥ የሆኑ (የ July 25, 2026 ቱንም ጨምሮ) የኮንሰርት ትኬቶችን ከመግዛት እንዲቆጠብና ራሱን ከአላስፈላጊ ኪሳራና ሕገ-ወጥ ድርጊት እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ለአዘጋጆችና ለቦታ አከራዮች የተላለፈ መልዕክት፦ በዚህ ሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርታችሁ ትኬት የምትሸጡ ወይም ለዝግጅቱ ቦታ የምታከራዩ አካላት በሙሉ ከዚህ ድርጊታችሁ በአስቸኳይ እንድትቆጠቡ አስተዳደሩ ያሳስባል።

ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሳውቃል።

ማንኛውም ሕጋዊ ፈቃድ የሌለው የኮንሰርት ዝግጅትና የትኬት ሽያጭ ሕገ-ወጥ መሆኑን አውቆ ህብረተሰቡ ራሱን ከገንዘብና ከጊዜ ኪሳራ እንዲጠብቅ አስተዳደሩ በጥብቅ ያሳስባል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ምክክር ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው************************የአንድ ሀገር ህልውና ሊረጋገጥ የሚችለው በዜጎች መካከል በሚኖር የጋራ መግባባት ...
18/06/2026

ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ምክክር ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው
************************

የአንድ ሀገር ህልውና ሊረጋገጥ የሚችለው በዜጎች መካከል በሚኖር የጋራ መግባባት እና ትብብር ላይ ነው።

ለዚህም በሀገራዊ ምክክር እና ሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ምክንያታዊነት ወሳኝና መሪ ሚና ይጫወታል።

በምክክር አውድ ውስጥ ምክንያታዊነት ሲባል ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ እና ከቂም በጸዳ መልኩ አመክንዮንና ማስረጃን መሰረት ማድረግ ማለት ነው።

ይህ መርህ ዜጎች በሀገራቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄዎችን በሰከነ መንፈስ እንዲፈልጉ ያስችላቸዋል።

ምክንያታዊነት ዜጎች ከጥላቻ ንግግሮች በመራቅ በምክክሩ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ሚዛናዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ በር ይከፍታል።

በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ላይ እና በመሰረታዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን ማጥበብ የሚቻለው በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ሰላማዊ ውይይት ብቻ ነው።

በጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረግ ድርድር ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ብቸኛው የችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያካሂደው ዋና የምክክር መድረክ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በባለቤትነት በማሳተፍ ዘላቂ ብሄራዊ መግባባት የመፍጠር እምቅ አቅም አለው።

ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት ልሂቃን ሳይሆን የሁላችንም የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰንበት ብሄራዊ መድረክ ነው።

በመሆኑም እያንዳንዱ ዜጋ ምክንያታዊነትን መሰረት አድርጎ ሂደቱን በቅንነት የመደገፍ እና ለስኬታማነቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ የማበርከት ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።(ebc)

በሐሳብ የበላይነት የሚገነባ ዘላቂ ሰላም፦ ከመደመር እሳቤ እስከ ሀገራዊ ምክክር**********************የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉዟችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም፣ ከስሜታዊነት ...
07/06/2026

በሐሳብ የበላይነት የሚገነባ ዘላቂ ሰላም፦ ከመደመር እሳቤ እስከ ሀገራዊ ምክክር
**********************

የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉዟችንን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም፣ ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም የግድ ይላል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው "የመደመር መንግሥት" መጽሐፍ እንደሚያስገነዝበው፣ መደመር ከአክራሪ ማንነቶች በመውጣት በሐሳብ የበላይነት ላይ የቆመ ፖለቲካን ይከተላል።

ይህ መርሕ በጠበበ ማንነት እና በፅንፈኝነት ላይ የተመሠረቱ የፖለቲካ አካሄዶች ለኢትዮጵያ ሕልውና እና አንድነት ትልቅ አደጋ መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል።

አክራሪ ማንነቶች በልዩነቶች ላይ ብቻ በማተኮር ማኅበራዊ ትስስርን የሚያላሉ እና ግጭትን የሚጋብዙ ናቸው።

ሀገራችን ከዚህ አዙሪት ወጥታ በሐሳብ ገዢነት እና በምክንያታዊነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ሥርዓት መገንባት ይኖርባታል።

ፖለቲካ በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ስሜታዊ መድረክ ሳይሆን በሕዝቦች መካከል ሀገራዊ ስምምነትን እና ገዢ ትርክትን የሚፈጥር የሐሳብ ገበያ መሆን እንዳለበት የመደመር መንግሥት ጽኑ አቋም አለው።

እውነተኛ ሰላም፣ ዕድገት እና ዘላቂ ብልፅግና የሚረጋገጡት በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በኃይል አማራጭ ሳይሆን፣ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይትና ምክክር ብቻ ነው።

የጦርነት እና የግጭት አካሄድ ሁሉንም ተሸናፊ የሚያደርግ የጥፋት መንገድ ነው። በጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረግ ውይይት ግን ለሁሉም ወገኖች እኩል ዕውቅና የሚሰጥ፣ ፍላጎቶችን የሚያስማማ እና እያንዳንዱን ዜጋ አትራፊ የሚያደርግ አስተማማኝ ጎዳና ነው።

መንግሥት ይህን የተቀደሰ ዓላማ ማዕከል በማድረግም ዋነኛ ትኩረቱን ውይይትን፣ እርቅን እና የሰላም አማራጮችን ማስፈን አድርጎ እየሠራ ይገኛል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በሥራ ላይ ሲሆን፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲም ወጥቶ ዝግጁ ሆኗል።

ይህም መንግሥት ውይይትን፣ እውነትን እና የሐሳብ የበላይነትን የመፍትሔዎች ሁሉ ማዕከል አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው።

ከሀገራዊ ምክክር መድረኩ የሚፈልቁ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን በቅንነት ለመቀበል እና ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጹም ለተፈጻሚነቱ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።

በመሆኑም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሰላም እና ለውይይት ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል። በፍቅር፣ በወንድማማችነት እና በዕውቀት ላይ የቆመውን "የመደመር መንግሥት" እሳቤን መላበስ እና በተግባር መተርጎም ይገባል።

ያለፈ ታሪካችንን በመነቃቀፍ እና በጥላቻ ለመተራመስ ለማዋል ሳይሆን፣ ካለፉ ስህተቶቻችን ተምረን የጋራ እሴቶቻችንን በማጎልበት የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በጋራ መቆም አለብን።

በጠመንጃ ኃይል የሚመጣ ዘላቂ ድል እንደሌለ እስከአሁን ከመጣንበት ታሪካችን በላይ ቋሚ ምስክር አይኖርም።

ዘላቂ እና አስተማማኙ ድል የሚገኘው ልዩነቶቻችንን በውይይት እና በሀሳብ የበላይነት መፍታት ስንችል ብቻ ነው።

ሁላችንም የሰላም መልዕክተኞች እና የውይይት ጀማሪዎች በመሆን ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ የበኩላችንን አዎንታዊ አሻራ እናኑር!
(ምንጭ Ebc

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ Diredawa Justice Security and Law Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share