Dire Road Safety

Dire Road Safety የትራፊክ አደጋ በጋራ እንከላከል ። Let's prevent traffic accidents together!! Balaa tiraafikaa waliin taane haa ittifnu!!

26/07/2026
26/07/2026
የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና የምስራቅ ሀረር...
25/07/2026

የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጋር በ ጋራ ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በማስመልከት በቁልቢ ከተማ በመንገድ ደህንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አካሂደዋል።

በባለስልጣኑ የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጅነር ሁሴን ጀማል በዓሉን በማስመልከት ወደ ከተማችን የመጡ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ እንዲሁም አሽከርካሪዎችም ሆነ ምእመኑ ራሱን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠብቅ ከሀምሌ 16 ጀምሮ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ እንዳለ ገልፀዋል።
የንቅናቄው አላማ የህዝባችንን ህይወት ከትራፊክ አደጋ መታደግ ነው ያሉት ሀላፊው ይኸንኑ በማጠናከር መነሻውን ከድሬደዋ መዳረሻውን ቁልቢ ከተማ ላይ ያደረገ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባሳተፈ መልኩ በዋዜማው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብር መካሄዱን ጠቁመዋል።
በዋዜማው ሰፊ የመንገድ ደህንነት ትምህርቶች የተሰጡ በራሪ ወረቀቶችና በድምፅ ማጉያም ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን ይህም በበዓሉለትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።

"የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል!"
የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ትምህርትና አቅም ግንባታ።

የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት የዘንድሮውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በማስመልከት ወደ ድሬደዋ  ...
24/07/2026

የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት የዘንድሮውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በማስመልከት ወደ ድሬደዋ ለመጡ እንግዶች አቀባበል እና የመንገድ ደህንነት የጥንቃቄ መልእክት ተከናውኗል

24/07/2026

የዘንድሮውን የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በማስመልከት በኢትዮ ጅቡቲ ድረደዋ ባቡር ጣቢያ የመንገደኞች አቀባበል እና የመንገድ ደህንነት የጥንቃቄ መልእክት ተከናውኗል

24/07/2026

Address

Dire Dawa
295

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Road Safety posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share