በድሬዳዋ አ/አሰሊሶ ክላስተር ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • በድሬዳዋ አ/አሰሊሶ ክላስተር ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

በድሬዳዋ አ/አሰሊሶ ክላስተር ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጠንከር ኢንስፔክሽን ለ ጠንከር ፓርት!

21/06/2026
21/06/2026

የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ ነው፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
***************************

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት መግለጫ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ምርጫው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ታየ በንግግራቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምርጫ ያሳየው ከፍተኛ ተሳትፎ የሰላማዊ ሽግግርን ፋይዳ መገንዘቡን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ከ94 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው መሳተፉ፣ የጸብና የአምባጓሮ ባህልን በመተው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣንን የመወሰን ፍላጎት እንዳለው በግልጽ ያሳየ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

ይህ ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ያላቸውን ቀናዒነትና ፍቅር በተግባር ያሳዩበት መሆኑንም ነው የተናገሩት።

″ከአሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ ነው″ ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ ለሚመኙ አካላት መልዕክት አስተላልፈዋል።

አያይዘውም፣ የሀገራችን የፖለቲካ ኃይሎች አካሄዳቸውን ከዘመናዊው የዴሞክራሲ ሥርዓት ጋር እንዲያስተካክሉ አሳስበዋል።

ከሕዝብ ድምፅ ውጭ የሚንቀሳቀሱ አካላት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርሳን በ"ግርጌ ማስታወሻ" ብቻ የሚቀመጡ እንደሚሆኑም ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቆሙት።

የምርጫ ውጤቱ የዜጎች አደራና የክብር ማኅተም መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንት ታየ፣ አሸናፊ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ይህን ከባድ ኃላፊነት በታማኝነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ መገናኛ ብዙኃንና ታዛቢዎች ለምርጫው ስኬት ላደረጉት አስተዋጽኦ ፕሬዝዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።

የምርጫ ቦርድን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የተቋማዊ አቅም ግንባታ አድንቀው፣ በቀጣይ ደግሞ የተሻለ ሥራ እንደሚያከናውን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የሚመሩትን አካላት በመምረጡ አሸናፊዎች በታማኝነትና በቅንነት ለሕዝብና ለሀገር እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በሃና ምንዳሁን

በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን አሸነፈ👍*********************
21/06/2026

በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ 438 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን አሸነፈ👍
*********************

21/06/2026
20/06/2026
20/06/2026
20/06/2026

Address

አሰሊሶ ክለስተር
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በድሬዳዋ አ/አሰሊሶ ክላስተር ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share