ድሬዳዋ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • ድሬዳዋ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት

ድሬዳዋ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት ይህ የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት ፌስቡክ ገጽ ነው::

10/06/2026

በድሬደዋ አስተዳደር የተዘረጋው የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታና ግብይት ስርዓት የዘርፉን አገልግሎት ለማቀላጠፍና የገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ።

በድሬደዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታና ግብይት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ጌዲ እንደገለጹት በድሬደዋ የተዘረጋው የግምት ስርዓት በሀገር አቀፍ የተሞክሮ ማዕከል ሆኖ እየተጠቀሰ ይገኛል።

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት የንብረት ግመታ ስርዓቱ ራሱን የቻለ መዋቅር እንዲኖረው በመደረጉ የተገልጋዮችን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ማሟላት እና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ተችሏል።

ባለፉት አምስት ዓመታትም ወደ 77 ሺህ የሚጠጉ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ለካሳ፣ ለስም ዝውውር፣ ለግብር እና ለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግምት አገልግሎቶች ተሰጥቷል።

የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ይበልጥ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በአራት ወረዳዎች የብዝሃ ግመታ (Mass Valuation) ስራ መከናወኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከግምት ስራዎች ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ከእጅ ንክኪ በማላቀቅ በሲስተም አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉ ተጠቅሷል።

እንዲሁም ከ10 ዓመታት በላይ ያልተሻሻለው የነባር ይዞታዎች የኪራይ ተመን እንዲሻሻል መደረጉን እና ለ7 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግምት ዋጋም በወቅታዊ የገበያ ዋጋ መሠረት እንዲሻሻል ተደርጓል። በዚህም በቁርጥ ዋጋ ስሌት የተመሰረተ ዘመናዊ የግምት ስርዓት ተዘርግቷል።

በተጨማሪም የቦታ ደረጃና የሊዝ መነሻ ዋጋ ወቅታዊ በመደረጋቸው እና ልዩ ባህሪ ያላቸው ንብረቶች ላይ የልየታና የግምት ጥናቶች በመካሄዳቸው ከመሬት የሚሰበሰበውን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አቶ መሃመድ ጌዲ ገልጸዋል።

ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም።

10/06/2026
10/06/2026

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባለፉት አስራ አምስት ወራት በተሻሻለው ሲስተም 16 ሺህ የሚጠጉ አገልግሎቶችን ሰጠ።

ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የሲስተም ማሻሻያ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል።

የቢሮው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሳ አብዱረህማን እንደገለጹት ቢሮው ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በየጊዜው የሲስተም ማሻሻያዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በዚህም ባለፉት 15 ወራት 16 ሺህ የሚጠጉ አገልግሎቶችን በተሻሻለው ሲስተም መስጠት ተችሏል።

በተሻሻለው ሲስተም የሚሰጡት የይዞታ ማረጋገጫዎች የልዩ መለያ (Barcode) ያላቸው በመሆናቸው ትክክለኛነታቸውን በቀላሉ ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

አቶ ሙሳ አክለውም ይበልጥ ዘመናዊና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በቢሮው የሚሰጡ የተለያዩ ሲስተሞችን ወደ አንድ የማቀናጀት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በማንዋል ሲከናወኑ የነበሩ የልማት ተነሺዎች መረጃዎች ወደ ዲጂታል ሲስተም እንዲገቡ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ቢሮው ከሚሰጠው አገልግሎቶች መካከል ግማሽ ያህሉን በ“መሶብ አንድ ማዕከል” አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን ሲስተሙ የተሳሰረ በመሆኑ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ገልጸው፣ በዚህም በሀገር ደረጃ የተሞክሮ ማዕከል መሆን እንደቻለ ጠቁመዋል።

እንዲሁም ቀጠሮ መያዝ፣ ቅሬታ ማቅረብ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በስልክ ለማግኘት እንዲቻል እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ሥርዓትን ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት በተከናወነ ማሻሻያ ወደ ሙሉ ትግበራ ለመግባት ሙከራውን ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ይህን ሥራ በተሟላ ሁኔታ ለማሳካት ባለይዞታዎች የይዞታ ማህደሮቻቸውን ከፋይዳ መለያቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም

10/06/2026

አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት የደንበኞችን እርካታ 74 በመቶ ማድረስ መቻሉ ተገለጸ።

ቢሮው ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረትና እርምት ለመወስደት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በድሬደዋ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የተቋም ለውጥ አፈጻጸም አገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ አሜ እንደገለጹት ባለፉት ወራት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራት የተገልጋይ እርካታን 74 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በበጀት አመቱ ከቀረቡ 226 ቅሬታና አቤቱታዎች መካከል ለ187ቱ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ቀሪ 39 ቅሬታና አቤቱታዎች በመታየት ላይ መሆናቸው ገልጸዋል።

በተጨማሪም አገልግሎት ያገኙ ማህደራትን ኦዲት በማድረግ የአሰራርና የመመሪያ ጥሰት የተገኘባቸው ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

አክለውም የደንበኞች ፍላጎትን መሠረት ያደረገ አገልግሎትን ለመስጠት የአገልግሎት ስታንዳርዶችን የማሻሻል እና በአዲስ መልክም የማዘጋጀት ተግባር መከናወኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም የፈጻሚውን የአመለካከት፣ የክህሎትና የህግ እንዲሁም ሙያዊ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅምን የመገንባት ስራ በስፋት መሰራቱን ተናግረዋል።

ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም

10/06/2026

ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ436 አልሚዎች 306 ሄክታር መሬት ተላለፈ።

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባለፉት ሁለት ዓመታት በካቢኔ ውሳኔ ለ436 አልሚዎች 306 ሄክታር መሬት ማስተላለፉን የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አልዪ ገልጸዋል።

ከተላለፉት መሬቶች ውስጥ 83.33 በመቶው ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሲሆን፣ ቀሪው ለገበያ ማዕከላት፣ ለሆቴሎች፣ ለከተማ ግብርና እና ለሆስፒታሎች አገልግሎት መዋሉ ተገልጿል።

ኃላፊው እንዳስታወቁት፣ መሬት ከተረከቡት 436 አልሚዎች መካከል 177ቱ ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ 66ቱ በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም 158 አልሚዎች በዲዛይን ዝግጅት ደረጃ ላይ ሲገኙ፣ 35 አልሚዎች የካቢኔ ውሳኔ ቢኖራቸውም እስካሁን መሬት አለመረከባቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊው ጨምረው እንደገለጹት መሬትን ለአልሚዎች በግልጽነትና በተጠያቂነት ማስተላለፍ የከተማዎችን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ እና ለነዋሪዎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር ወሳኝ ነው።

እንዲሁም የልማት ፕሮጀክቶቹ ተግባራዊ በመሆናቸው በግንባታ፣ በአገልግሎት እና በምርት ዘርፎች በቋሚና በጊዜያዊ መልኩ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ መሆኑን አብራርተዋል።

ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

27/05/2026
👉 ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!!✍️ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የሀገሪቱን ክብር ከፍ ለማድረግ፣ የባሕር በር ፍላጎትን ለማረጋገጥ እና ጠንካራ የሕገ መንግሥት ሥርዓት ለመገንባት ያስችላል። ...
26/05/2026

👉 ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!!

✍️ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የሀገሪቱን ክብር ከፍ ለማድረግ፣ የባሕር በር ፍላጎትን ለማረጋገጥ እና ጠንካራ የሕገ መንግሥት ሥርዓት ለመገንባት ያስችላል።

👉 ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!!

👉 የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ነዋሪዎች የብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ።

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ድሬዳዋ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ብልጽግና ፓርቲ ህብረት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share