05/09/2026
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል ሆኖ እንዲቀጥል የወጣቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የሀዲያ ዞን እና የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አመራር አካላት 'በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!' በሚል መሪ ቃል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካሂደዋል፣
በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጠችሁ መልዕክት ያስተላለፊት የከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ስዩም እንደገለጹት ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ቆይታ ቢሆንም በሁሉም መስኮች የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆኑንና ጠቅሰው በበጎ ፈቃድ አገልግሎትም በርካታ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፣
አቶ ተክሌ ስዩም አክለውም ወጣቶች ነገ የተሻለች ለሁም የምትመች ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ወጣቶች በጎ ስራቸው ገዥ ትርክት በመገንባት የእርስ በእርስ ትስስርን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ማጠናከር ተገቢነት እንዳለው ገልጸው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና እድሳት፣ ለተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ፣ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፣
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱ ዲንቁ እንደገለጹት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፣
አቶ አብዱ ዲንቁ አክለውም የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማህበራዊ ዘርፍ በህዝቦች አንድነትና አብሮነት ለማጠናከር አጋዥ መሆኑንና በሌሎችም በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካው ዘርፎች ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፣
በመርሃግብሩ ወቅት በጎ ወሰን ተሻጋሪ ፈቃደኛ ወጣቶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላቱ ማቴዎስ በበኩላቸው ወጣቶ ያላቸውን ዕውቀትና ጉልበት የበጎ ፈቃድ ስራ በመስራት ለሀገር ግንባታ ለዜጎች ተጠቃሚነት ምክንያታዊና አሳማኝ በሆነ መንገድ ማበርከት ይገባል ስሉ ገልጸዋል፣
በመርሃግብሩ ለአቅመ ደካማ እናት የቤት ግንባታ የሚሆን የቆርቆሮና የምስመር ድጋፍ፣ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የትምህት መማሪያ ደብተርና እስክብርቶ፣ የእህልና የምግብ ዘይት ድጋፍ በማድረግ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሰርቷል።
ከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት