19/08/2026
"ፅዱ ኢትዮጵያ ለተተኪው ትውልድ"በሚል መሪ ቃል የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት “ፅዱ ኢትዮጵያ ለተተኪው ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በማንኩሳ ከተማ የጽዳትና አካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።
ንቅናቄው የከተማዋን ንጽህና ለማስጠበቅ፣ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና የህብረተሰቡን የንጽህና ባህል ለማጠናከር ያለመ ነው።
የጃቢ ጠህናን ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ታደሰ እንደገለፁት አካባቢን ከብክለት መጠበቅና ንጽህናን ማስጠበቅ የጤና፣ የውበትና የዘላቂ ልማት መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ፣ የጋራ ቦታዎችን በመጠበቅና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በመደገፍ የራሱን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ዳኛቸው አክለውም፣ የንጽህናና የአካባቢ ጥበቃ ሥራ የአንድ ቀን ዘመቻ ሳይሆን ቀጣይነት ያለው የሁሉም የጋራ ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። በመሆኑም የአሁኑ ትውልድ ለተተኪው ትውልድ ንጹህ፣ ጤናማና ተስማሚ አካባቢ ለማስረከብ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የጃቢ ጠህናን ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሆድአዲስ አማረ እንደገለጹት፣ ንጹህና ለኑሮ ምቹ አካባቢ መፍጠር የመንግሥትና የአንድ ተቋም ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይም ማኅበረሰቡ በንጽህና ሥራዎች በንቃት በመሳተፍ የከተማውን ውበትና ንጽህና ለመጠበቅ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አሳስበዋል።
ወ/ሮ ሆድአዲስ አክለውም፣ “ፅዱ ኢትዮጵያ ለተተኪው ትውልድ” የሚለው መሪ ቃል ንጽህናን የዕለት ተዕለት ተግባርና የኑሮ ባህል ማድረግ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ መሆኑን ገልጸው፣ ከቤተሰብ ጀምሮ በማኅበረሰብ ደረጃ የንጽህና ባህልን ማጎልበት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውይይት ሰነዱ በጃቢ ጠህናን ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የአካባቢ ትምህርትና ግንዛቤ ማስፋፊያ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሀብታሙ ደምሴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም የጽዳትና አካባቢ ጥበቃ ሥራው በአንድ ቀን ንቅናቄ የሚጠናቀቅ ሳይሆን በየጊዜው በመቀጠል ዘላቂ የሆነ የንጽህና ባህል መፍጠር እንደሚገባ ተጠቁሟል። “ፅዱ ኢትዮጵያ ለተተኪው ትውልድ” የሚለው መሪ ቃልም አሁን ያለው ትውልድ ለሚመጣው ትውልድ ንጹህ፣ ጤናማና ተስማሚ አካባቢ የማስረከብ ኃላፊነትን የሚያሳስብ መልዕክት መሆኑ ተገልጿል።
የበለጠ መረጃዎችን ለማግኘት ቀጣዮችን ሊንክ ይጫኑ !!
Facebook http://facebook.com/westgojjamenvironmental
Telegram https://t.me/Westgojamzoneenvirometalprotecti
You Tube https://www.youtube.com/
titoki www.tiktok.com/