07/04/2026
የምዕራብ ጎጃም ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ::
==============================
መጋቢት 25/2018 ዓ/ም
ፍ/ሠላም፣
የምዕራብ ጎጃም ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አለልኝ አሰፋ በመክፈቻ ንግግራቸዉ የንግድ መሠረቱን በማስፋፋት፣ህጋዊ የንግድ ሽፋንን በማጠናከር፣የሸማቹን መብት በማስከበር፣ የገበያ መሠረተ ልማቱን በማስፋፋት፣ የግብይት ስርዓቱን በማዘመንና ሰንሰለቱን በማሳጠር፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት እና የኤክስፖርት ግብይትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፣ በዚህም
ከንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች አኳያ:-
አዲስ ምዝገባ ማድረግ፡- ዕቅድ 7,000 ክንዉን 4695 አፈፃፀም ከአመቱ 67.07%፣
አዲስ ፈቃድ መስጠት፡- ዕቅድ 9,000 ክንዉን 6323 አፈፃፀም ከአመቱ 70.26%፣
ፈቃድ እድሳት፡- ዕቅድ 13,746 ክንዉን 11111 አፈፃፀም ከአመቱ 80.83% ማከናወን የተቻለ ሲሆን
19,407 ድርጅቶች ላይ የአስተያየት መስጫ ደብተር በማስቀመጥ ነጋዴዎች የንግድ ሪፎርሙን እንዲያሟሉ የድጋፍና የክትትል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
19407 ድርጅቶችን በመጎብኘት የንግድ ህግ የሚጥሱትንና ሸማቹን የሚጐዱትን የንግዱን ማህበረሰብ ከህገ-ወጥ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እየተሰራ ይገኛል፣በዚህም 1437 ጉድለቶች ተገኝተው 1430ቱን እንዲስተካከሉ የተደረገ ሲሆን፣638 የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣792 ደግሞ በማሸግ፣እንዲሁም 2 እገዳና 7 በፍርድቤት ክስ በመመስረት እዲስተካከሉ ተደርጓል፡፡
በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ መሠረታዊ ምርት
በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር የህጋዊ ነጋዴዉ ተባባሪነትና በአካል በመጠቆምና በመታገል እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም 1305 ድርጅቶች ካለ ፍቃድ ሲነግዱ ተገኝተው 1295ቱ አዲስ ፍቃድ እንዲያወጡ ተደርጓል፣
እንዲሁም መሰረታዊ ምርት - ስኳር 6.5 ኩ/ል፣ነዳጅ 6327 ሊትር፣ 180.5 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ፣100 ቀረጢት ከሰል፣52 ኩ/ል በቆሎ፣151 የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን ከጎዳና ላይ በማስነሳት ህጋዊ ሆነው እዲሰሩ በማድረግ፣18 ኩ/ል በርበሬና 50 ኪ/ግ ዱቄት፣ 280 ኪ/ግራም ማር በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተገኝቶ ምርቱ ተይዞ በሞዴል 85 ወደ መንግስት ካዘና እንዲገባና ሌሎች ምርመራ ላይ ያለ መሆኑ፣
13,767 ድርጅቶች ደረሰኝ እንዲሰጡና 18984 ድርጅቶች ላይ የዋጋ ዝርዝር እንዲለጥፍ በማድረግ እየተሰራ ይገኛል፣
ጊዜ ያለፈባቸውንና መገለጫ የሌላቸውን ምርቶች በድርጅቶች ክትትል በማድረግና በማስወገድ የሸማቹን ጤንነትና ደህንነት መጠበቅ፣
11,593 ድርጅቶች የተሟላ የንግድ እቃ መግለጫ እንዲኖራቸዉ በማድረግ እና 11,593 የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች መከታተልና ማስወገድ ስራ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፣
በዋጋ ሲተመን 201123 ብር የሚያወጣ ምርት 1,070.4 ኪ/ግ በጠጣር እና 562 ሊትር በፈሳሽ የመጠቀሚያ ጊዜዉ ያለፈበት ምርት ተይዞ በቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት እንዲወገድ ተደርጓል፡፡
የመሰረታዊ ምርት አቅርቦትና ስርጭት፡-
ስኳር አቅርቦትና ስርጭት፡- የቀረበ 4,000 የተሰራጨ 4,000 አፈጻጸም እስከዚህ 100%፣
ምግብ ዘይት ስርጭት፡- የቀረበ 200,000 የተሰራጨ 200,000 አፈጻጸም እስከዚህ 100%፣
380279 ኩ/ል የሃገር ዉስጥ የሰብል ምርት ግብይት ትስስር መፈፀም ተችሏል፡፡
118552 ኩ/ል የስንዴና በቆሎ ተኪ የግብርና ምርት ማቅረብ ተችሏል፣
በግብርና ምርት (በሰብል፣አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስትና እንስሳት ተዋፅኦ) እና በፍጆታ የኢንዲስትሪ ምርቶች ተሰማርተው የሚገኙ ደላላዎችን 100% ከገበያ ማስወጣት፣
በህገ ወጥ መንገድ ተከፍተው የሚገኙ ኬላዎችን 100% በማስወገድ ያልተገቡ ክፍያዎችን/ ቀረጦችን በማስቀረት የምርት ዝውውር ቀልጣፋ እንዲሆን እና ሸማቹ ለኑሮ ውድነት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ማድረግ ከዚህ ተግባር አኳያ መምሪያዉ ለሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም ለሚመለከታቸዉ አካላት ኬላዉ እንዲነሳ ደብዳቤ ተጽፎ በማዉረድ ሁሉም ኬላዎች እንዲነሱ ተድርጓል፡፡
2ኛ ደረጃ አምራችና ሸማችን የሚያገናኝ ገበያ ማዕከላት ለመገንባት ቦታ የመለየትና የርክክብ ስራ ተፈፅሟል፣ካርታና ፕላን ተሰርቶ የፀደቀ ሲሆን በጀት ተመድቦለት የተቋራጭ ልየታ ተሰርቶ ዉል ተይዞ ስራዉ ተጀምሯል፡፡
ነባር ገበያ ማዕከላት በማሻሻል በመጠገን፣አዲስ ልዩ (እሁድ) ገበያ ማዕከላት ማቋቋም፣ ነባር የእሁድ ገበያ ማዕከልን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፡፡
የግብይት ትስስሩን በማጠናከርና የፋይናንስ አቅርቦቱን በማሳደግ ገበያውን ማረጋጋት፣
62,199,950 ብር ለገበያ ማረጋጋት የሚዉል ተዘዋዋሪ ብድር ማስመደብ የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በማቅረብ ገበያ የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም የቀረበ ምርት
36,848 ኩ/ል የግብርና ምርት፣ 19,478 ኩ/ል ኢንዱስትሪ ምርት በጠጣር፣666,966 ሊ/ር የኢንዱስትሪ ምርት በፈሳሽ ማቅረብ ገበያዉን የማረጋጋት ስራ ተሰርቷል፡፡
የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች በትስስር ከማገበያየት አኳያ
የአሳ ምርት 19.66 ቶን፣105,853 የቁም እንስሳት በመሸኛ ተልከዋል፣2.292 ቶን የስጋ ምርት፣3,005,360 ሊትር የወተት ምርት፣ 945.24 ቶን የማር ምርት፣152.19 ቶን የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ፣107,320 ዶሮ፣801,997 የእንቁላል ምርት ትስስር ተፈፅሟል፡፡
በሌላ በኩል ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ፡-
በነዳጅ ማደያዎች የሥራ ለ20 ሰዎች፣በኤክስፖርት ምርት ዝግጅት ለ21 ሰዎች፣በመሰረተ ልማት ግንባታ ለ55 ሰዎች፣በሽርክና ለ13 ሰዎች፣በአጠቃላይ ለ384 ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፣ እንዲሁም የሴቶችን፣የወጣቶችን፣የአካል ጉዳተኞችንና የአረጋዊያንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
ያለንግድ ፈቃድ የሚሰሩ ጫት ቤቶችን 100 በመቶ በመዝጋት ህግን ለማስከበር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፣
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቀረበውን የዕቅድና ክንውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ከባለሙያዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል። በቀጣይም ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የተያዘውን ዕቅድ በስኬት ለማጠናቀቅና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የሚገባውን አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል አቅጣጫ መድረኩ ተጠናቋል።