Itang Special Woreda Press Secretariat Offices

Itang Special Woreda Press Secretariat Offices Government Service

''ነገን ዛሬ እንትከል'' በሚል መሪ ቃል በአታንግ ልዩ ወረዳ በአንድ ጀምበር  የአረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ  ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄዷል።የኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳ...
17/07/2023

''ነገን ዛሬ እንትከል'' በሚል መሪ ቃል በአታንግ ልዩ ወረዳ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄዷል።

የኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም
***********************************
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአገር አቀፍ ፕሮግራም ሆኖ ዛሬ የአንድ ጀምበር ዘመቻ በወረዳ ደረጃ አጠቃላይ በወረዳ ያለው የቀበሌዎች ማህበረሰብ ችግኝ እንዲተከሉ ተደርገዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የወረዳው አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሀይማኖት አባቶች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የመንግስት ሠራተኞቾና የፀጥታ አካላት ተሳተፈዋል።

‘ግብር ለሀገር ክብር’’ በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የታክስና የህግ ተገዢነት የንቅናቄ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል::*************************************ከኢ...
13/07/2023

‘ግብር ለሀገር ክብር’’ በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የታክስና የህግ ተገዢነት የንቅናቄ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል::
*************************************

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ሀምሌ 6/ 2015 ዓ.ም)

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የንቅናቄ መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ከግብር ከፋዮች የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም የታክስ ህግ ተገዥነትንና በገቢ ልክ ግብር የመሰብሰብ አቅምን ለማሳደግ የተጀመረው ”ግብር ለሀገር ክብር” ሀገር አቀፍ ንቅናቄን በክልል ደረጃ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ቀጣይና አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው ሃገሪቱ የምታመነጨዉን የገቢ አቅም አሟጦ መሰብሰብ ሲቻል ነው ብለዋል።

‘‘ግብር ለሀገር ክብር’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የታክስ ንቅናቄ መርሃ-ግብር የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ የግብር መክፈል ባህሉን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጁል ናንጋል በበኩላቸው የንቅናቄው ዋና ዓላማ ከግብር ከፋዮች ተገቢውን ግብር በመሰብሰብ የክልሉን ልማት ማፋጠን ነው ብለዋል፡፡

በዘርፉ ባለፉት የለዉጥ አመታት እንደ አገርም ሆነ እንደ ክልል በተሰሩ ተከታታይነት ያላቸው ስራዎች አመርቂ ዉጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና በብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የንቅናቄ መርሃ ግብሩ ከሀምሌ 2015 ጀምሮ እስከ የካቲት 2016 አመተ ምህረት እንደሚቆይም ተመልክቷል።

ዘገባው የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው!

በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 26 ጀምሮ ይሰጣል።ከኢታንግ ልዮ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትሰኔ 19/2015 ዓ.ም     ኢታንግ********************...
26/06/2023

በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 26 ጀምሮ ይሰጣል።

ከኢታንግ ልዮ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ሰኔ 19/2015 ዓ.ም ኢታንግ
*****************************************

በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከ22 ሺህ በላይ ተማሪዎችም ለፈተና እንደሚቀመጡ ቢሮው አመልክቷል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ክልል አቀፍ ፈተናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀው በ205 የፈተና ጣቢያዎች 670 ፈታኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በፈተናው ላይ 12 ሺህ 805 ወንድ እና 9 ሺህ 746 ሴት ተማሪዎች በድምሩ 22 ሺህ 551 የቀንና የማታ ተማሪዎች እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል፡፡

ጋምቤላ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ሁሉም ወረዳዎች ሰኔ 23/2015 ዓ.ም ክልል ትምህርት ቢሮ በመገኘት ፈተናውን እንዲረከቡም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ሆነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን በየዘርፉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
#የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሸን

ለጋምቤላ ክልል ሰላምና ለተጀመረው የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት ሁሉም ኃላፊነቱን በትጋት ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።ከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽ...
22/06/2023

ለጋምቤላ ክልል ሰላምና ለተጀመረው የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት ሁሉም ኃላፊነቱን በትጋት ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሰኔ 15/2015 ዓ.ም
************************************
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢታንግ ልዩ ወረዳ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ እያካሄዱ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰላም ኮንፈረንሱ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት በኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለፋት አራት የለውጥ አመታት የፀጥታ ችግር እንዳልነበረ ያነሱ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የነበረውን ሰላም የሚያጠለሽ ተግባራት እየተስተዋሉ ይገኛሉ ብለዋል።

ኢታንግ ልዩ ወረዳና አካባቢው በሰላም እጦት ምክንያት ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በአካባቢው የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍና ወረዳውን ወደ ቀድሞ ሰላም ለመመለስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የዜጎች በሰላም ወጥቶ የመግባት መብታቸውና ነፃነታቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንንም ለማስጠበቅ የአካባቢው ማህበረሰብን ጨምሮ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

መድረኩ በክልሉ የሚታዩትን አለመግባባቶች በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ወደ ግጭት ለሚያመሩ ጉዳዮችም መፍትሔዎች ተለይተው የሚቀመጡበት ነው ብለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ በበኩላቸው የሰላም ትርጉሙ ሰፊ ቢሆንም ወንድማማችነት፣ ፍቅር፣ አብሮነት፣ መከባበር፣ እንዲሁም ነባር እሴትን በዘላቂነት አጎልብቶ አብሮ መኖርን ይጠይቃል ሲሉ አብራርተዋል።

ሰላም ዋጋው የማይተመን መሆኑንና ያለ አስተማማኝ ሰላም ህብረተሰቡ ሰርቶ መግባት፣ ነግዶ ማትረፍ እንደማይቻል ስለሚታወቅ ሁሉም ህብረተሰብ የሰላም እሴቶችን በማጎልበት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሰላም ኮንፈረንሱ ኢታንግ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በሶስቱ የብሄረሰብ ዞኖች እየተካሄደ ይገኛል።

ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል - አቶ ኦርዲን በድሪከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት*******************...
20/06/2023

ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል - አቶ ኦርዲን በድሪ

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
******************************************
ሴነ 13/2015 ዓ.ም

የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር በህዝቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ አሳሰቡ።

በአቶ ኦርዲን በድሪና ሌሎች አመራሮች መሪነት ሲካሄድ የቆየው የጋምቤላ ክልል የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ አመራሮቹ የክረምት በጎ ፈቃድና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በጋምቤላ ከተማ አካሂደዋል።

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅቱ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶች በማስቀጠልና ፈተናዎችን በድል በመሻገር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግቶ መስራት ይገባናል ብለዋል።

ፓርቲው የሚመራው መንግስት ባለፉት ዓመታት የገጠሙትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በድል በመሻገር በማህበራዊ ሆነ በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በቀጣይም ፈተናዎችን በድል በመሻገር የተገኙትን የልማት ድሎች ፍጥነትና መፍጠርን በመጨመር አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም አሁን ላይ ዘላቂ ሰላምና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም ለተጀመረው የልማት ጉዞ መሰናክል የሆኑትን ብልሹ አሰራሮችና ሌብነት አብሮ መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው፤ እንደ ብልጽግና ፓርቲ ግብርናንና ኢንዱስትሪን ጨምሮ እየተገበራቸው በሚገኙት አምስት የብዝሃ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ስራዎች በርካታ ስኬቶች መገኘታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም የተገኙትን ስኬቶችና ጥንካሬዎች በማስፋት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

በጅምር የቀሩ የልማት ፕሮጀክቶችና የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት የማስቀጠሉ ሂደትም ሌላው በፓርቲው የተመላከቱ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑም አመላክተዋል።

ከስልጠና ተሳታፊዎች መካከል አቶ ቲቶ ሐዋሪያት በሰጡት አስተያየት፤ በስልጠናው የተቀመጡ አቅጣጫዎች በከፍተኛ ተነሳሽነት ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ለህዝቡ ቃል የተገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን መፍጠርና መፍጠን በሚለው መርህ ለመፈጸም እንደሚሰሩ የገለጹት ሌላው ተሳታፊ አቶ ጆዶ ኡሞድ ናቸው።

በዕለቱ አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በጋምቤላ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት ስራ አስጀምረዋል።

03/06/2023

ማስታወቂያ:-

የጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት በመቱ ሬዲዬ ማሰራጫ ጣቢያ በክልሉ በሚነገሩ ሶስት ቋንቋዎች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በመልካም አስተዳደርና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ገንቢ መረጃዎችን እንዲሁም አነቃቂ ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመስራት ለማህበረሰብ የተሟላ መረጃዎችን በማስተላለፍ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

በመሆኑም በአኙዋ ቋንቋ ፣በኑዌርኛ፣በማጃንግ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ ሬዲዬ ሲተላለፍ የነበረው የመቱ እስቱዲዮ ወደ ክልል መዛወሩን እየገለፅን በእጃችሁ በቀላሉ ማዳመጥ በሚያስችላችሁ መንገድ FM አዲስ 97.1 ጣቢያ በኩል በቀን 28/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከቀኑ 9:00-9:45 በአኙሃ ቋንቋ፣ከ9:45-10:30 በኑዌርኛ ቋንቋ ፣ከ10:30-11:00 በማጃንግ ቋንቋ የሚያሰራጭ በመሆኑ እንድትከታተሉን በታላቅ አክብሮት እየገለፅን ምርትና አገልግሎትዎን ማስትዋወቅ ለምትፈልጉ ወደ ክልሉ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎት በመምጣት መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በጋምቤላ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ መዘጋጀቱ አርሶ አደሩ ምርቱን ለሌሎች ለማስተዋወቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ...
02/06/2023

በጋምቤላ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያስተዋውቅ አውደ ርዕይ መዘጋጀቱ አርሶ አደሩ ምርቱን ለሌሎች ለማስተዋወቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።

በሳይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ላይ በጋምቤላ ክልል በግብርናው ዘርፍ ላይ የተገኙ ውጤቶች ለእይታ ቀርበው ተጎብኝተዋል።

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ግንቦት 25/2015 ዓ.ም
*******************

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት የግብርና ምርቶችን በማስተዋወቅ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ ክፍት የሆነው የግብርና ሳይንስ አውደ-ርዕይ የግብርናው ዘርፍ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ማየት የቻልንበት እና ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ እድል የሚፈጥር አውደ-ርዕይ እንደሆነ ገልፀዋል።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው ክልሉ በርካታ የተፈጥሮ ሀብት ያለበት ክልል በመሆኑ ለበርካታ የምግብና የገበያ ሰብሎች ምቹ ነው ብለዋል።

ክልሉ በዓይነቱ ከ100 በላይ የዓሳ ዝርያዎችና ለንብ ማነብ ምቹ ስነ ምህዳር መኖሩን የጠቆሙት አቶ አጃክ አውደ ርዕይ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ኤግዚቢሽኑ ከተጀመረ አራት ሳምንታት የሆነው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ከ50 ሺህ በላይ ጎብኚዎችን አስተናግዷል ብለዋል።

ሚኒስትሩ የጋምቤላ ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ገልፀው በቀጣይም ክልሉ ለግብርና ስራ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ክልሎች የራሳቸውን የግብርና ፀጋዎች በተለያየ መንገድ በኤግዚቢሽኑ በማምጣት ለጎብኚዎች ማጋራት መቻላቸውም የሚያኮራ ነው ያሉት ደግሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ናቸው።

ኤግዚቢሽኑ የጋምቤላ ክልል በእርሻ፣ በፍራፍሬ ሰብል፣ በእንስሳት ተዋጽኦ እና በሌሎች የግብርና ስራዎች ከየት ተነስቶ ወዴት እንደደረሰ ለማሳየት እድል የፈጠረ መሆኑንም አስረድተዋል።

በጋምቤላ ክልል የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የዓሳ ፣ ማር፤ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች ቀርበዋል።

28/05/2023

በኢታንግ ልዩ ወረዳ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳ መንግስት አስታወቀ።

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት /ግንቦት 19/2015 ዓ.ም/
***********************************************

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ኡበንግ ጊሎ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በወረዳው ተከስቶ የነበረዉን የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌዴራል የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ ስራ በቁጥጥር ስር እንዲዉል ተደርጓል ብለዋል።

ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር የከፋ ጉዳት እንዳይደረስ በቁጥጥር ስር እንዲዉል ላደረጉ የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት ምስጋናም ቀርቧል።

ሰሞኑን በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌዎች በሚኖሩ ግለሰቦች መካከል የተነሳዉ አለመግባባበት ወደ ግጭት አምርቶ በወረዳው መጠነኛ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የአምስት ሰው ህይወት ሲያልፍ 9 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ በመከናወኑን በየደረጃ የሚገኙ የቀበሌዎች ማህበረሰብ ውይይቶች ተካሄዶ አንፃራዊ ሠላም መፈጠሩን አመልክተዋል።

ለዘመናት በአብሮነትና ወንድማማችነት ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት የሚሞክሩ አካላት መኖራቸውን የጠቀሱት የወረዳው መንግስት በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ጥረት ሴራቸው ሳይሳካ መቅረቱን አስረድተዋል።

በቀጣይም በህዝቦች መካከል ያለውን አንድነትና ወንድማማችነት በማስቀጠል ዘላቂ ሰላምንና ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ በክልሉም ሆነ በወረዳችን ያለውን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ የሚጥር ግለሰብም ሆነ ቡድን ሲያጋጥማቸው በአቅራቢያ ለሚገኝ የመንግስት አካል ጥቆማ በመስጠት ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል።

በመጨረሻም በወረዳችን በተፈጠረው አንፃራዊ ሠላም ማህበረሰቦቻችን ወደ ነበራቸው የመደበኛ ሥራዎቻቸው የተመለሱ መሆኑን ለቀጣይ ሥራ ከቀያቸው የተፈናቀሉ አራቱ(4) ቀበሌዎች አስቸኳይ የመልሶ ማቋቋም ሥራ እንደሚሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 2ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤዉን በጆር ወረዳ ማካሄድ ጀምሯል።************************************ከኢታንግ ልዩ...
27/02/2023

የአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 2ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤዉን በጆር ወረዳ ማካሄድ ጀምሯል።
************************************
ከኢታንግ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት(የካቲት 20/2015 ዓ.ም)

የብሄረሰብ ዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አፒየው ኡዊቲ ጉባኤውን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት፣ የዞኑ ምክር ቤት አባላት ለመልካም አስተዳደር፣ ልማት፣ ፍትህ መረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በትጋት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በተለይም በዞኑ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በማስወገድ የዞኑን ህዝብ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት ከጉባኤ አባላቱ የሚጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።

የዞኑ ምክር ቤት አባላት የዞኑን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ሆነው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነቱን በማቃለልና የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም አካላት ተቀናጅተው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸውም አፈ ጉባኤዋ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠዉን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ለመወጣት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የአኙዋኣ ብሔረሰብ ዞን ምክር ቤት በ6ኛ የምርጫ ጊዜ በ2ኛ የስራ ዘመን በ3ኛ መደበኛ ጉባኤዉ የ2015 ያለፉት 6 ወራት የዞኑ መስተዳድር ምክር ቤት፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበዉ በጉባኤ አባላቱ ዉይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የቀጣዩ ግማሽ የበጀት ዓመት የተከለሰ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግበት ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ: ክልሉ_መንግሥት_ኮሙኒኬሽን

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ስድስተኛ ምርጫ ሁለተኛ የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ በጋምቤላ ከተማ ተጀ...
22/02/2023

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ስድስተኛ ምርጫ ሁለተኛ የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤ በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።

ከጋምቤላ ክልል ምክር ቤት
(የካቲት 15/2015 ዓ.ም)

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ትሁት ሃዋሪያት በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች ከግብ እንዲደርሱ ሁሉም በአንድነት ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በተለይም በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የመስክ ምልከታ በማድረግ ደካማ ጎኖች እንዲታረሙና ጠንካራ ጎኖች እንዲጎለብቱ አቅጣጫ መቀመጡን አብራርተዋል።
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ባደረጋቸው የመስክ ምልከታና የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከተለዩት ቁልፍ ችግሮች መካከል በሆስፒታል እና በጤና ጣቢያዎች የመድኃኒት እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንደሚገኝበት አስታውቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የግንባታዎች የጥራት ችግር እና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቅ፣ የትምህርት ግብዓቶች አለመዳረስ፣ በጀትን ያላገናዘበ የባለሙያ ቅጥርና ምደባ እንደ ችግር መነሳቱን ወይዘሮ ትሁት ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባላት የልማት ማነቆ የሆኑትን ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በመታገል እንደ ሀገር የተጀመረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ዳር ለማድረስ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ የክልሉ አስፈፃሚ አካላት የ2015 የግማሽ በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የስራ ክንውን ሪፖርት ጉባኤው አድምጦ ያፀድቃል።
በተጨማሪም የቀጣዩ ግማሽ የበጀት ዓመት የተከለሰ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድና የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ከወጣው መርሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከ350 በላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራር አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
# ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

በኑዌር ብሔረሰብ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 19 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።ከኢታንግ ልዩ ወረዳ  የመንግስት ኮሙ...
06/02/2023

በኑዌር ብሔረሰብ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 19 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።

ከኢታንግ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ጥር 29/2015 ዓ.ም)

የኑዌር ብሄረሰብ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኢንስፔክተር ዶሎሰ ቾል እንዳስታወቁት በዞኑ ማኩዌይ ወረዳ ቶርሞሮክ ቀበሌ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር የዋለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ 17 ክላሽንኮቭ እና ሁለት መትረየስ እንደሆነ ተናግረዋል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ የማጣራት ስራ እየተከናወነ ነው ያሉት ኢንስፔክተሩ ኅብረተሰቡ የጦር መሳሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረገውን ትብብር ወደፊትም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ምንጭ: ክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

Address

Itang Woreda
Gambela
MESSENGER

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Itang Special Woreda Press Secretariat Offices posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Itang Special Woreda Press Secretariat Offices:

Shortcuts

Share