17/05/2026
መንግስት ባለፉት አመታት በክልሉ ግንባታቸው ተቋርጦ የቆዩትን መንገዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኑዌር ዞን በመንግስት እየተሰሩ ያሉ መሠረተ ልማቶችን ምልከታ አካሂደዋል።
አኮቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ
ግንቦት 8/2018 ዓ/ም
******************
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት የለውጡ መንግስት ባለፉት አመታት በክልሉ ግንባታቸው ተቋርጦ የቆዩትን መንገዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት የዜጎችን ማኅበራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የመንገድ፣ የጤና እንዲሁም የትምህርት መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረትና ቁርጠኝነት በአካባቢው ይከሰት የነበረውን የተለያዩ ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ነው ብለዋል።
የክልሉን ልማት ለማፋጠን እና ከፍ ለማድረግ መንገዶችን ሰርቶ ማጠናቀቅ እና ሌሎች የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ትኩረት በመስጠት መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኑዌር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጃክ ጆሴፍ በበኩላቸው ባለፉት አመታት የዞኑን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
ቀደም ሲል በአካባቢው የተሟላ የመሠረተ ልማት ግንባታ ባለመኖሩ ምክንያት ነዋሪዎች ረጅም መንገድ በእግራቸው ለመጓዝ ይገደዱ እንደነበር አቶ ጃክ በወቅቱ ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም ማህበረሰቡ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይደርስባቸው እንደነበር ገልጸው በአሁን ሰዓት ከመታር ከተማ እስከ ካንካን ያለው የመንገድ ስራ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ብለዋል።
በመጨረሻም ከአኮቦ ወረዳ የተወጣጡ የማህበረሰብ ተወካይ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን ከማህበረሰቡ ለቀረበላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) መልስ እና ማብራሪያ ስጥተዋል።