23/06/2025
የመኸር እርሻ ሥራ - የነገው የአዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ ነው
**************
መኸር የተፈጥሮ ዝናብን በመጠቀም በኢትዮጵያ ብዙ ሰብል የሚሰበሰብበት የምርት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት በቂ ግብዓት ከቀረበና ድጋፍ ከተደረገ ዓመታዊ የተትረፈረፈ ምርት ስለመገኘቱ ዋስትና ይስጣል።
አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ የሀገር ጉዳይም “የዚህ ዓመት የመኸር እርሻ ሥራ ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል?” ሲል ይጠይቃል።
አርሶ አደሩ ለመኸር እርሻው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ቀርበውለት እንደሆነም በአዲስ ቀን ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ ይሰጥበታል።
በመኸር እርሻ ወቅት በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ለአርሶ አደሩ ብሎም ለሰብል ልማቱ ያላቸውን ፋይዳ በተመለከተ ማብራሪያ በአዲስ ቀን የሀገር ጉዳይ ይቀርብበታል።
የዚህ ዓመት የመኸር እርሻ ሥራ ምን ያህል ለግብርናው የተመቸ እንደሆነም አዲስ ቀን የሚመለከታቸውን አካላት ስቱዲዮ ጋብዞ ይጠይቃል።
አዲስ ቀን ይህን የሀገር ጉዳይ እና ሌሎች ጥንቅሮችን አካቶ ነገ ጧት ከ1:00 እስከ 3:00 ከአብዮት ይግዛውና ከመቅደላዊት ደረጀ ጋር ይጠብቃችኋል።
አዲስ ቀን!