Gambella Region Ethics&Anti-Corruption Comission

Gambella Region Ethics&Anti-Corruption Comission እንኳን ወደ ጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ በደህና መጡ
የጥቆማ መቀበያ የነፃ ጥሪ አገልግሎት ቁጥር 8623

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችድጋፍ አደረገ!    *** **** ***** ****** የጋምቤላ ክልል የሥነ...
27/08/2026

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች
ድጋፍ አደረገ!
*** **** ***** ******

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት አቅም የሌላቸው ተማሪዎች በቁሳቁስ እጥረት
ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይለዩ ለማድረግ ያለመ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አድርጓል።

በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የፕላን ቢሮ የሥራ ኃላፊ በ3 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ፤   *** **** ***** ******(የጋም.ሥፀ.ኮ 15/12/2018 ዓምጋም)የጋምቤላ ክልል ፍትህ ቢሮ የ...
24/08/2026

በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የፕላን ቢሮ የሥራ ኃላፊ በ3 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ፤
*** **** ***** ******
(የጋም.ሥፀ.ኮ 15/12/2018 ዓምጋም)
የጋምቤላ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ወንጀል ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ በአቶ በኋይሉ ወርቁ ላይ የመሰረተው የሙስና ወንጀል ክስ ውሳኔ አገኘ።

የክሱ ዝርዝር፦ የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፕላን ቢሮ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ
የነበሩት አቶ በኋይሉ ወርቁ፣ ከአቶ ዋለልኝ ታመነ ከ(2ኛ ተከሳሽ ድርጅት) ጋር ያልተገባ የሥራ ግንኙነት በመፍጠር የመንግሥትን
የግዥ አፈጻጸም መመሪያ በመጣስ ክስ ተመስርቶባቸው ቆይቷል።

ተከሳሹ ለቢሮ ዕድሳትና ማስዋቢያ በሚል ባልተሠራ ሥራ ውል በመዋዋል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እጅ በእጅ ሽያጭ ሰነድ
በመቀበል፣ የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13/ሀ እና የመንግሥት የግዥ አፈጻጸም
መመሪያ ቁጥር 02/2003 በመጣስ በመንግሥት ሥራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ተከሷል።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ፦ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በቀረበው ማስረጃ መሠረት ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ
በመገኘቱ በ05/12/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ3 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ይግባኝ ስለመጠየቁ፦ የክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ወንጀል ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ፣ የተሰጠው የ3 ዓመት የእስራት ቅጣት ከተፈጸመው
ወንጀል ክብደት አንጻር ተከሳሹንም ሆነ ሌላውን ማኅበረሰብ የማያስተምር (የማይቀጣ) ሆኖ አግኝቶታል። በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ
በቅጣት ውሳኔው ላይ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፣ ጉዳዩ በሂደት ላይ ይገኛል።
ማሳሰቢያ፦ በክልሉ የሚገኙ ማንኛቸውም የመንግሥት ተቋማትና የሥራ ኃላፊዎች፣ ማናቸውንም የመንግሥት ግዥዎች ሲፈጽሙ የክልሉን የግዥ አዋጅና መመሪያ ብቻ መሠረት በማድረግ በታማኝነትና በግልጽነት እንዲፈጽሙ እናሳስባለን።

የሃብት ምዝገባ የሚካሄድበት  ጊዜ    *** **** ***** ******ማንኛውም አዲስ ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥትሠራተኛ ሀብቱን የሚያሳውቀውና የሚያስመዘግበው ከተሾመበት፣ ከተመረጠበት...
07/08/2026

የሃብት ምዝገባ የሚካሄድበት ጊዜ
*** **** ***** ******
ማንኛውም አዲስ ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥትሠራተኛ ሀብቱን የሚያሳውቀውና የሚያስመዘግበው ከተሾመበት፣ ከተመረጠበት ወይም ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ በ45 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

ሀብቱን ያስመዘገበ ማንኛውም ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ ከዚያ በኋላ ሀብቱን የሚያሳውቀውና የሚያስመዘግበው በየሁለት ዓመት ተኩል ይሆናል፡፡

የምዝገባ ጊዜን ስለማራዘም
_________________:_
• የምዝገባ ጊዜ እንዲራዘምለት የሚጠይቅ ሰው ምዝገባውን ማራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት በጽሑፍ በመግለጽ የምዝገባ ጊዜው በተጠናቀቀ በአምስት ቀናት ውስጥ ለኮሚሽኑ ወይም ለሚመለከተው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ማመልከት ይችላል፡፡ኮሚሽኑ ወይም ጉዳዩ የሚመለከተው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል የቀረበለት ጥያቄ በበቂ ምክንያት የተደገፈ ሆኖ ሲያገኘው የምዝገባውን ጊዜ ለአንድ ጊዜ እስከ 30 ቀናት ሊያራዝም ይችላል፡፡

ዘግይቶ ስለማስመዝገብ
________________:_
በመደበኛው ወይም በተራዘመለት የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ሀብቱን ያላስመዘገበ ተሿሚ ወይም ተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ ብር 1,000 / አንድ ሺህ ብር/ መቀጫ ከፍሎ በ3ዐ ቀናት ውስጥ ሊያስመዘግብ ይችላል ፡፡ተሿሚው ወይም ተመራጩ ወይም የመንግስት ሰራተኛው በመደበኛው ወይም በየሃብት ምዝገባ የሚካሄድበት ጊዜ
ማንኛውም አዲስ ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥትሠራተኛ ሀብቱን የሚያሳውቀውና የሚያስመዘግበው ከተሾመበት፣ ከተመረጠበት ወይም ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ በ45 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
ሀብቱን ያስመዘገበ ማንኛውም ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ ከዚያ በኋላ ሀብቱን የሚያሳውቀውና የሚያስመዘግበው በየሁለት ዓመት ተኩል ይሆናል፡፡

የምዝገባ ጊዜን ስለማራዘም
_______________;-
• የምዝገባ ጊዜ እንዲራዘምለት የሚጠይቅ ሰው ምዝገባውን ማራዘም ያስፈለገበትን ምክንያት በጽሑፍ በመግለጽ የምዝገባ ጊዜው በተጠናቀቀ በአምስት ቀናት ውስጥ ለኮሚሽኑ ወይም ለሚመለከተው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ማመልከት ይችላል፡፡ኮሚሽኑ ወይም ጉዳዩ የሚመለከተው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል የቀረበለት ጥያቄ በበቂ ምክንያት የተደገፈ ሆኖ ሲያገኘው የምዝገባውን ጊዜ ለአንድ ጊዜ እስከ 30 ቀናት ሊያራዝም ይችላል፡፡

ዘግይቶ ስለማስመዝገብ
____________;-
በመደበኛው ወይም በተራዘመለት የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ሀብቱን ያላስመዘገበ ተሿሚ ወይም ተመራጭ ወይም የመንግስት ሠራተኛ ብር 1,000 / አንድ ሺህ ብር/ መቀጫ ከፍሎ በ3ዐ ቀናት ውስጥ ሊያስመዘግብ ይችላል ፡፡ተሿሚው ወይም ተመራጩ ወይም የመንግስት ሰራተኛው በመደበኛው ወይም በተራዘመለት የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ሃብቱን በተደነገገው መሰረት ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡

ከስንብት በኋላ ስለሚከተሉ ግዴታዎች
___________________;-
ማንኛውም ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ በጡረታ ሲገለል ወይም በማንኛውም ምክንያት አገልግሎቱን ሲያቋርጥ ሀብቱን በተራዘመለት የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ሃብቱን በተደነገገው መሰረት ከአምስት ዓመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡

ከስንብት በኋላ ስለሚከተሉ ግዴታዎች
_________________:-
ማንኛውም ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ በጡረታ ሲገለል ወይም በማንኛውም ምክንያት አገልግሎቱን ሲያቋርጥ ሀብቱን በ30 ቀናት ውስጥ ለኮሚሽኑ ወይም ለሚመለከተው የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል እንዲሁም ከሁለት ዓመት በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ አለበት፡፡

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የ12 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል።      *** *...
02/08/2026

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የ12 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ምክር ቤት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል።
*** **** ***** ******
(ጋብክመ.ሥ.ፀ.ኮ 26/11/18 ጋምቤላ)
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ቱት ንዑት ባቀረቡት ሪፖርት የታቀዱ ተግባራት መከናወናቸውን በመግለጽ፣ የሙስና ውስብስብነትን ለመቋቋም የፍትህ አካላት የቅንጅት አሰራር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ቋሚ ኮሚቴው መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ድክመቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ የተሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ ለቀጣይ የተሻለ ሥራ እንደሚነሳሳ አረጋግጧል።

" ትውልድን በሥነ-ምግባር
ተቋምን በአሠራር"
ለተጨማሪ መረጃ የፌስቡክ ገፃችን ይጎብኙ።

የቀድሞ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፈጸሙት የሥልጣን አላግባብ መጠቀም እና የሰብዓዊ መብት  ወንጀል ጥሰት በፈፀሙት ላይየፍርድ ውሳኔ ተላለፈ።  *** **** ***** ******...
27/07/2026

የቀድሞ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፈጸሙት የሥልጣን አላግባብ መጠቀም እና የሰብዓዊ መብት ወንጀል ጥሰት በፈፀሙት ላይ
የፍርድ ውሳኔ ተላለፈ።
*** **** ***** ******
(ጋም.ክ.ሥፀ.ኮ 20/11/18/ ጋምቤላ)
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የፖሊስ ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ላይ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሳሽነት በቀረቡ ክሶች ላይ የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

- የተከሳሾች ማንነት እና ቅጣት፦

1. አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ (የቀድሞ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ)፦ በ10 ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት እና
በገንዘብ መቀጮ።
2. አቶ ሽመልስ ቶማስ (የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር)፦ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እና በገንዘብ
መቀጮ።

- የተመሰረተባቸው ክስ፦

- ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም "የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት" የተባለ ታጣቂ ቡድን ማደራጀት።
- ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸም።

- ውሳኔውን ያስተላለፈው አካል፦ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ጥፋተኛ ማለቱን
ገልጿል።

ይህ ውሳኔ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የሚወሰድ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያሳይ ሲሆን፣ በተለይም ከታጣቂ ቡድን ማደራጀትና
ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዞ የተሰጠ ትልቅ ውሳኔ መሆኑ ተመልክቷል።
" ትውልድን በሥነ-ምግባር፤
ተቋምን በአሠራር!"

#የነፃ መስመር ጥሪ 8623

://www.facebook.com/profile.php?id=61569995963416&mibextid=ZbWKwL

የመንግስትን ሃብት ለመታደግና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚደረገው የተቀናጀ የሕግ የበላይነት ማስከበር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል     *** **** ***** ******(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ጋም...
24/06/2026

የመንግስትን ሃብት ለመታደግና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚደረገው የተቀናጀ የሕግ የበላይነት ማስከበር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
*** **** ***** ******
(ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ጋምቤላ) የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ የሥነ-ምግባር መኮንን ጋር በቅንጅት በመሆን ባደረጉት ጥብቅ ክትትልና ለክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ምርመራ ክፍል ባስተላለፉት ጥቆማ መሰረት፣ የመንግስትን የግዥ አሰራር መመሪያ በመጣስ የሙስና ወንጀል በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ይፋዊ የክስ ሂደት ተመሠረተ።
ክሱ በሰኔ 09/2018 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፣ ተከሳሾች የክልሉ ፕላን ቢሮ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ በኃይሉ ወርቁ እና የአንድ የግል ተቋም ባለቤት የሆኑት አቶ ዋለልኝ ታመነ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በፍርድ ቤት በሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን የሕግ ሂደቱም በጥብቅ በመከታተል ላይ ነው።
የተፈጸሙት ዋና ዋና የሕግ ጥሰቶችና የሙስና ወንጀሎች፡-
ሀ. ያለ ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም፡ አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ በኃይሉ ወርቁ የመንግስትን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ በጣሰ መልኩ ያለ ምንም ግልጽ ጨረታ በራሳቸው እቃዎች ገዝተው በማቅረብ 1,458,450.50 ብር ከመንግስት ካዝና እንዲወጣ ማድረጋቸው።
ለ. ያልተሰራን ስራ እንደተሰራ ማስመስከር፡ በዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ ያልተካተተን ስራ መመሪያን ባልተከተለ መንገድ በመተግበር 1,200,000.00 ብር ያለአግባብ ወደ ግል የባንክ አካውንት እንዲገባ መደረጉ።
መ. በሕገ-ወጥ ስራ መተባበር፡ ሁለተኛ ተጠርጣሪ አቶ ዋለልኝ ታመነ በጨረታ ያልተለየ ሕገ-ወጥ የሥራ ውል በመፈራረም እንዲሁም የድርጅታቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እጅ በእጅ ሽያጭ ሰነድ አሳልፈው በመስጠት ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው።
የኮሚሽኑ መልዕክት፡-
የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ግልጽና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ አሰራር የመንግስትን ሃብት ለመታደግ የሚያደርገውን ዘላቂ ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ይገልጻል።
በመጨረሻም ማንኛውም የክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤትም ሆነ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚያከናውኑትን ማንኛውንም የፋይናንስና የግዥ ስራ በሕጉና በመመሪያው መሠረት ብቻ እንዲፈጽሙ እያሳሰበ፤ የተቋማት የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች (የሥነ-ምግባር መኮንኖች) ለተቋማቸው ተጠያቂነት መስፈንና ለቅድመ-መከላከል ስራው የበኩላቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪውን ያስተላልፋል።

"ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!"

#የነፃ ስልክ መስመር 8623
://www.facebook.com/profile.php?id=61569995963416&mibextid=ZbWKwL

አገርዓቀፍ የሥነ-ምግባር ግንባታ ሥልጠና እና የሙስና መከላከል ጥናት የፋይዳ ግምገማ የባለድርሻ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል*** **** ***** ******(ጋምቤላ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ ...
15/06/2026

አገርዓቀፍ የሥነ-ምግባር ግንባታ ሥልጠና እና የሙስና መከላከል ጥናት የፋይዳ ግምገማ የባለድርሻ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

*** **** ***** ******

(ጋምቤላ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሰኔ 8/2018 ዓ.ም) የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አገርዓቀፍ የሥነ-ምግባር ግንባታ ሥልጠና እና የሙስና መከላከል ጥናት የፋይዳ ግምገማ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ በሀገር ደረጃ በመንግስት የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ማዕቀፍ ውስጥ በተከናወኑ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራዎች ላይ ምክክር በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው፡፡

በመድረኩ ባለፉት ሶስት የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ የተሰሩ የሙስና መከላከል ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በበርካታ መልካም አስተዳደር ችግሮች በታየባቸው የተቋማት አሰራር ሥርዓት ላይ የሙስና መከላከል ጥናቶች ተጠንተው ለተቋማት በምክረሐሳብ መልክ ቀርበዋል። በአስቸኳይ ሙስና መከላከልም በሀገርአቀፍ ደረጃ 4,588 በሚሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ መስራት ተችሏል። በዚህም፣ የሙስና ወንጀል ሳይፈጸም በሂደት ላይ እያሉ ማቋረጥ እና ወደ ትክክለኛው አሰራር ሥርዓት እንዲገቡ ተደርጓል።

እንዲሁም በአገርአቀፍ ደረጃ 3,282 የሚሆኑ የሀብት ምዝገባ ትክክለኛነት የማጣራት ስራ ተከናውኗል።

ከዜጎች በሙስና ወንጀል መረጃነት 1,835 ያህል ቀርበው ለተገቢው ምርመራ ሥራ ለፍትህ አካላት ተልኳል። በቂ ማስረጃ የተገኘባቸውም ወደክስና ክርክር እንዲሁም የፍርድ ውሳኔ አሰጣጥ ደረጃ የደረሱ አሉ።

በመድረኩ በቀጣይ የሚሰጡ የሥነምግባር ግንባታ ስልጠናዎች ጥራትና ተገቢነት እና የሙስና መከላከል ስራዎች ውጤታማነት እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅት ይበልጥ እንዲጠናከሩ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በምክክር መድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ፣ የፍትህ ሚኒስቴር የዓቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ም/ኃላፊ፣ የፌደራል ዋና ኦዲተር ከፍተኛ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ከፍተኛ ዋና ዳይሬክተር፣ የፌዴራል፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነሮች እና ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የፌደራል ተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

"ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!"
ዘገባው የፌ .ሥ.ፀ.ኮ.ነው

#የነፃ ስልክ መስመር 8623
://www.facebook.com/profile.php?id=61569995963416&mibextid=ZbWKwL

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ቱት ንዑት እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት!  *** ***** ***** ******( ጋ.ሥ.ፀ.ኮ 03/08/...
11/04/2026

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ቱት ንዑት እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት!
*** ***** ***** ******
( ጋ.ሥ.ፀ.ኮ 03/08/2018 ዓ.ም )
የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ቱት ንዑት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የትንሳኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ድኅነት ሲል የመስቀልን መከራ ተቀብሎ፣ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበትና ለዓለም ሁሉ የተስፋ፣ የድልና የመታደስ ብርሃን የታየበት ታላቅ ዕለት ነው። ይህ በዓል ከጥላቻና ከመለያየት ይልቅ ፍቅርንና አንድነትን እንድንመርጥ የሚያስተምረን በመሆኑ፤ እኛም በትንሳኤው ብርሃን ታግዘን ለሀገራችን ሰላም መሣሪያ በመሆንና በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ለመገንባት በጋራ ልንቆም ይገባል። በዓሉን ስናከብርም የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ማዕድ በማጋራት፣ የወንድማማችነት እሴቶቻችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል።
ከፈተናዎች በኋላ ስኬት፣ ከሞት በኋላም ሕይወት እንዳለ ሁሉ፤ እኛም በጽናትና በአንድነት በመቆም ለሀገራችን ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልፅግና የምናደርገውን ጉዞ በድል እንደምናጠናቅቅ ሙሉ እምነታችን ነው። በዓሉ የሰላም፣ የደስታና የብልፅግና ይሁንላችሁ!

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ***  **** ***** ****** (ጋም.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 27/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ባለፉት ዘ...
05/04/2026

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

*** **** ***** ******

(ጋም.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መጋቢት 27/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወነ ሰፊ የሙስና ወንጀል ምርመራ በስልጣን አላግባብ መገልገል እና በእምነት ማጉደል ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በከባድ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አሳምነው ሙላት እንደገለፁት ፖሊስ በዞኑ የመንግስትንና የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው ባዋሉ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ ትኩረት በማድረግ ባከናወነው ጥብቅ የምርመራ ስራ ውጤት ተመዝግቧል።

የኩታበር ወረዳ ማዘጋጃ ቤት የስራ ኃላፊዎች በስልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰው የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከፍተኛ ቅጣት ተጥሎባቸዋል፦

በዚህም፣ አቶ አሊ ከበደ የቀድሞ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ1,000 ብር ቅጣት፣ አቶ ሙህድን አሊ ምክትል ኃላፊ በ4 ዓመት እስራት እና በ2,000 ብር ቅጣት፣ አቶ አቦል አሸብር በ4 ዓመት ከ5 ወር እስራትና በ2,000 ብር ቅጣት እና አቶ ሙሉጌታ በሪሁን በ5 ዓመት እስራትና በ2,000 ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

በተጨማሪም አቶ ኑረዲን መሀመድ ጨምሮ አምስት የማናጅመንት አባላት በሌሉበት በተካሄደ ክርክር እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ፅኑ እስራትና በ5,000 ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል። ተከሳሾቹ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ውለው በደሴ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ አዛዡ አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ የምርመራ መዝገብ ኢ/ር ምህረት አያሌው የአድማ መከላከል ሻምበል አዛዥ የነበረ በከባድ የእምነት ማጉደልና በስልጣን አላግባብ መገልገል ሙስና ወንጀል ተከሶ በሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የ9 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።

አቶ እንድሪስ ይመር አሊ የመነሀሪያ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ የነበረ ከ950 ሺህ ብር በላይ በኦዲት በመጥፋቱ በ5 ዓመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት እና በ5,000 ብር ቅጣት ተቀጥቷል። አቶ ሰይድ ሀሰን ሁሴን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ የነበረ የደንበኞችን 5 ሚሊዮን 150 ሺህ ብር በመውሰዱ በ5 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ኮማንደር አሳምነው ሙላት አክለውም ፖሊስ ሙስናን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን እያካሄደ ያለውን ጥብቅ ክትትልና ምርመራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የክልሉ ፖሊስ በፌስቡክ ገጹ መረጃውን አጋርቷል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

#የነፃ ጥቆማ የስልክ መስመር 8623 https://www.facebook.com/profile.php?id=6156999 #5963416&mibextid=ZbWKwL

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተገኙ የኦዲት ግኝቶችን መነሻ በማድረግ ከክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ***  **** ***** *******( ...
03/04/2026

የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተገኙ የኦዲት ግኝቶችን መነሻ በማድረግ ከክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ጋር የጋራ ውይይት አካሄደ
*** **** ***** *******
( ጋም.ሥ.ፀ.ኮ መጋቢት 25 2018ዓ.ም)
የጋምቤላ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተቋማዊ አሰራሩን ይበልጥ ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ፣ በ2016/17 በጀት ዓመት በቀረቡ የሁለት ዓመት የኦዲት ግኝቶች ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ቱት ንዑት፣ ከክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኦዲተሮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታደሠ እና ከፍተኛ የኦዲት ከዋኝ ወ/ሮ ጥሩሰው አምሳሉ እንዲሁም የኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ኮሚሽኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት በነበረው የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር እንቅስቃሴ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት፣ በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻሻለና ከስህተት የጸዳ አሰራር እንዲሰፍን ለማስቻል መሆኑን ከክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኦዲተሮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ በመግቢያ ንግግራቸው ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ቱት ንዑት በበኩላቸው፤ በቀረበው የኦዲት ሪፖርት ላይ የተመለከቱ ግኝቶችን ኮሚሽኑ በጸጋና በሙሉ ድምፅ እንደሚቀበላቸው ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፣ “እንደ ሥነ-ምግባር ተቋም በኦዲት የተለዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማረም ለሌሎች መሥሪያ ቤቶች አርአያ መሆን ይጠበቅብናል” በማለት፣ የተጠቀሱት የአሰራር ግድፈቶች በአፋጣኝ እንዲስተካከሉ ተቋማዊ ቁርጠኝነት መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ የጋራ ውይይት ኮሚሽኑ የክልሉን የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትግል ከመምራት ባለፈ፣ በውስጥ አሰራሩም ግልፅነትንና ሕጋዊነትን ለማስፈን ያለውን ዝግጁነት ያሳየ መሆኑ ተገልጿል።

#የነፃ ጥቆማ የስልክ መስመር 8623 https://www.facebook.com/profile.php?id=6156999 #5963416&mibextid=ZbWKwL

Address

Gambella
Gambela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Region Ethics&Anti-Corruption Comission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share