Gedeb Woreda Government Communication Service

Gedeb Woreda Government Communication Service ይህ የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው

‎የአየር መዛባት ተከትሎ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ በገደብ ወረዳ ጎቲት ከተማ የፋጭኤ እና የፀሎት መርሃ ግብር አካሄዱ‎‎ #ገደብ ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ...
03/09/2026

‎የአየር መዛባት ተከትሎ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ በገደብ ወረዳ ጎቲት ከተማ የፋጭኤ እና የፀሎት መርሃ ግብር አካሄዱ

‎ #ገደብ ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ባንቆ ጎቲት ከተማ የአየር መዛባት ተከትሎ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ ባሊ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የፋጭኤ እና የፀሎት መርሃ ግብር አካሂዷል።

‎የጌዴኦ ህዝብ የእራሱን ቋንቋ ፣ ፋጭኤ ማድረግ ስርዓት እና ድርቅ ስከሰት በመፀለይ የራሱን የጋዳ ስርዓት ያለው መሆኑን አባጋዶ ቢፎም ዋቆ ተናግሯል።

‎የራሱን ስርዓት ይዘው በመሄድ ለምድራችን ሰላም እንዲሰፍን ፡ ረሃብና ቸነፈር ከምድራችን እንዲጠፋ ፡ ምዲርቱ ፍሬ እንዲያፈራ እና የበረከት ዝናብ እንዲዘብ ፡ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ ፋጭኤ እና ፀሎት አድርገዋል።

‎የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ታደሴ ፡ ፈጣሪ ለምድራችን ምህረትና የበረከት ዝናብ እንዲሰጥልን በሁሉም እምነት ተቋማትና በባህላዊ ሾንጎዎች ፀሎት እንዲደረግ መልዕክታቸውን አስተላልፏል።

‎የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አቶ ከበደ ገራ በበኩላቸው ፈጣሪ ምድራችንን በምህረቱ እንዲሸፍን እና የበረከት ዝናብ እንዲሰጥልን ሁሉም መፀለይ እንዳለባቸው አሳስቧል።

‎በመርሃ ግብሩ አባ ጋዳ ቢፎሚ ዋቆ ባሊ ፣ የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ሲሳይ ታደሴ ፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ገራ ፣ ባህላዊ ሽማግሌዎች እና የጎቲት ማህበረሰብ ክፍል በተገኙበት የፋጭኤ ስነስርዓት ተደርጓል።

‎@የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።

‎በወረዳው የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት የግምገማ መድረክ ተካሄደ‎‎ #ገደብ፦ ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የ2019 ዓ....
03/09/2026

‎በወረዳው የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት የግምገማ መድረክ ተካሄደ

‎ #ገደብ፦ ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮሙኒኬሽን)

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

‎የተማሪዎች ቅበላ ላይ አመራሩና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ትልቅ ድርሻ በመዉሰድ ተግባሩን ለማሳለጥ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተጠቁሟል።

‎የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ታደሴ ፡ የትምህርት ሥራዎችን ለማሳለጥ እና የተማሪዎች ቅበላን ለማሳለጥ አመራሩና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መምራት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

‎የትምህርት ዉጤታማነትን ለማረጋገጥ በ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥተው መመራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ገራ ፡ የትምህርት ዘመን የቅበላ የእስካሁን አፈፃፀም ስታይ ክፍተት የታየበት በመሆኑ በቀሩ ቀናት ልዩ ትኩረት ተሰጥተው መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ጉበና ፡ የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ የደረሰበት ሁኔታ ሪፖርት አፈፃፀም አቅርበዋል።

‎በመድረኩ የወረዳው ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ጨምሮ የወረዳ አጠቃላይ አመራሮችና የ13ቱም ቀበሌያት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፏል።

‎@የገደብ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

በዞኑ የትምህርት ስርዓቱን ለማሳለጥ ያለስስት መምራት እንደሚገባ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) አስታወቁ ‎‎( #፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም)‎‎የትምህርት ስርዓቱን በዞኑ ለማሳለጥ ያለስስት ዘርፉን ...
02/09/2026

በዞኑ የትምህርት ስርዓቱን ለማሳለጥ ያለስስት መምራት እንደሚገባ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) አስታወቁ

‎( #፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም)

‎የትምህርት ስርዓቱን በዞኑ ለማሳለጥ ያለስስት ዘርፉን መምራት እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) አስታዉቀዋል

‎አስተዳዳሪዉ ይህንን ያስታወቁት የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ አፈፃፀምን ከዘርፉ ባለድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን በገመገሙበት ወቅት ነዉ ።

‎መምሪያው የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላና ወቅታዊ የትምህርት ተግባራት አፈፃፀምን በጥልቀት ተመልክቷል ።

‎የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍሌ የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላና ወቅታዊ የትምህርት ተግባራቶች አፈፃፀምን አቅርበዋል ።

‎በዚህም የተማሪዎች ቅበላ ላይ አመራሩና የትምህርት ባለድርሻዎች የአንበሳዉን ድርሻ በመዉሰድ ተግባሩን በተጠያቂነት ሊመራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

‎መድረኩን የመሩት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በንግግራቸው በዞኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅበላ የእስካሁን አፈፃፀሞችን ስንመለከት ሊቀረፉ የሚገቡ ተግባራቶች መኖራቸውን ገልፀዋል ።

‎በዚህም በዋናነት የትምህርት ቅበላ ስርዓቱን በአጭር ቀናት በማጠናቀቅ ተግባሩ በባለቤትነት መምራት እንደሚገባም አስተዳዳሪው ያሳሰቡት ።

‎አክለዉም የትምህርት ዘርፍ ፍትሀዊ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ተገቢዉ ክትትልና ድጋፍ ሊደረግባቸዉ እንደሚገባም ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልፀዋል ።

‎የትምህርት ምዝገባ ስርዓቱን በተሳለጠ መንገድ መምራት የተሻለ ትዉልድን ለመፍጠር ይረዳል የሚሉት አስተዳዳሪው ይህም በየደረጃው ያሉትን የዘርፉን ችግሮች በመቅረፍ እየተስተዋሉ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ይረዳል ብለዋል።

‎የትምህርት ዉጤታማነትን ለማረጋገጥ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅበላ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘርፉ ሊመራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ተመስገን ጥላሁን የጠቆሙት ።

‎በመድረኩ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ዋና አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች፣ የፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎@ዘገባው ገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!






‎በወረዳው ወቅታዊ በሆኑ ዝርዝር ተግባራት ዙሪያ የአመራሮች ውይይት መድረክ ተካሄደ‎‎ #ገደብ፦ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም  ኮሙኒኬሽን ‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ወቅታዊ የፓርቲው እና መንግስ...
02/09/2026

‎በወረዳው ወቅታዊ በሆኑ ዝርዝር ተግባራት ዙሪያ የአመራሮች ውይይት መድረክ ተካሄደ

‎ #ገደብ፦ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ኮሙኒኬሽን

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ወቅታዊ የፓርቲው እና መንግስታዊ የሥራ ተግባራት ዙሪያ የአመራሮች ውይይት መድረክ ተካሂዷል

‎መድረኩን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ገራ እና የወረዳው ምክትል አስተዳደር አቶ አድሱ አበራ በጋራ መርቷል።

‎ወቅታዊ መደበኛ ተግባራት ላይ ውጤታማነትን ለማስቀጠል የአመራሮች ከፍተኛ ሚና እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

‎እንድሁም እየተመዘገቡ ያሉ ለውጥ በቀጣይነት አጠናክሮ ለማስቀጠልና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ተሰጥተው መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።

‎በውይይቱ የወረዳው አስተባባሪዎች ፣ የሁሉም ሴክተር መስሪያቤቶች ኃላፊዎች ተሳትፏል።

‎@የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

‎‎በወረዳው ባንቆ ጎቲት ከተማ የሴቶች ልማት ህብረት ለአቅም ደካሞች ድጋፍ አደረጉ‎‎ #ገደብ ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም ኮሙኒኬሽን‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በባንቆ ጎቱት የሴቶች ልማት ህብ...
01/09/2026


‎በወረዳው ባንቆ ጎቲት ከተማ የሴቶች ልማት ህብረት ለአቅም ደካሞች ድጋፍ አደረጉ

‎ #ገደብ ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም ኮሙኒኬሽን

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ በባንቆ ጎቱት የሴቶች ልማት ህብረት አቅም ደካሞች እና ለተጋላጭ ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድረጓል።

‎"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " የተጀመሩ ኢንሼቲቭ ሥራዎችን ለማሳለጥ በወረዳው ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

‎በመርሃ ግብሩ የወረዳው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ የወጣቶችና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ፡ የወረዳው አመራር አካላት እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፏል።

‎የገደብ ወረዳ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሀብታሟ ጉሚ ፡ በሴቶች ተሳትፎ የክረምት በጎ ተግባራትን ከፍ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መሆኑን ተናግሯል።

‎የበጎ ሥራዎችን ስንሰራ ከፈጣሪ በረከት የምናገኝ ስሆን ይህንን ተግባር ቀጣይነት ባለው መልኩ መሰራት እንዳለበት አሳስቧል።

‎የወረዳው ወጣቶችና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ፡ አቶ ስንታየሁ በየነ ፡ የበጎነት ተግባር የህልና እርካታ የምናገኝ ስሆን ይህንን ተግባር ባህል አድረገን መሄድ እንዳለበት አሳስቧል።

‎በወረዳው በ18 ዘርፍ የክረምት በጎ ተግባራትን ለማሳለጥ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ እንዳለ አስረድተዋል።

‎በዕለቱ የተለያዩ ሥራዎች የተከናወኑ ስሆን ለ90 አቅም ደካሞች እና ተጋላጭ ለሆኑ 126 ህፃናቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና በደም እጦት ለሚሰቃዩ እናቶች የደም ልገሳ እንድሁም የዲጃታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ተከናውኗል።

‎በመጨረሻም ጽ/ቤቱ በተግባራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉት አካላት የሰርተፍኬት ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

‎@ዘገባው የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው!

‎በገደብ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ታላቅ የምህረት ጸሎት አካሄዱ‎‎ገደብ ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን)‎‎በገደብ ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን ...
31/08/2026

‎በገደብ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ታላቅ የምህረት ጸሎት አካሄዱ

‎ገደብ ፦ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን)

‎በገደብ ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን በነቂስ በመውጣት በስታዲየም ውስጥ ታላቅ የጸሎትና የሱባኤ ስነ-ስርዓት አካሄዱ።

‎የወቅቱ የአየር ንብረት መዛባት ያስከተለውን የዝናብ እጥረት ምክንያት ፈጣሪን ምህረት ለመለመን ህዝበ ክርስቲያኑ በፅኑ መንፈስ የተማጽኖ መርሃግብር ነው ያካሄዱት ።

‎ህዝበ ክርስቲያኑ ከአለም ምኞት ተለይቶ በጸሎት፣ በጾም እና በፍጹም ትህትና ወደ አምላክ በመቅረብ ምህረትን፣ በረከትን እና መልስን የሚጠይቅበትን የጉባኤ ስነ-ስርዓት በጋራ አከናውኗል።

‎ዘገባው ፦ የገደብ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ነው

በገደብ ወረዳ "ለምናልማት ሀገር ትውልድ ቀራጩ መምህር" በሚል መሪ ቃል የመምህራኖች ውይይት መድረክ ተካሄደ‎‎ነሃሴ፦ 25/2018 ዓ.ም መንግስት ኮሙኒኬሽን‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የትም...
31/08/2026

በገደብ ወረዳ "ለምናልማት ሀገር ትውልድ ቀራጩ መምህር" በሚል መሪ ቃል የመምህራኖች ውይይት መድረክ ተካሄደ

‎ነሃሴ፦ 25/2018 ዓ.ም መንግስት ኮሙኒኬሽን

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት "ለምናልማት ሀገር ትውልድ ቀራጩ መምህር" በሚል መሪ ቃል የመምህራኖች እና የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎የትምህርት ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ ሁሉም የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።

‎የትምህርት ጥራትን በማሻሻል የመምህራን ሙያዊ አቅም በማጎልበት በሀገር ደረጃ እያጋጠመው የሚገኘውን የትምህርት ስብራት መጠገን እንደሚቻል ተጠቁሟል።

‎የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ሲሳይ ታደሴ ፡ በትምህርት ሥራዎች ውጤታማነትን ለማስጠበቅ ሁሉም ከወትሮ በበለጠ ትኩረት ተሰጥተው መስራት እንዳለበት አስረድቷል።

‎የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ጎበና ፡ የመማርና ማስተማር ሥራዎችን በማሻሻል እያሽቆለቆለ ያለውን የተማሪዎች ውጤት ማሳደግ እንደሚቻል አስረድቷዋል።

‎የዞኑ የትምህርት መምሪያ የስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ኃላፊ ፡ የትምህርት ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ መምህራኖች ትልቅ ድርሻና እንዳለባቸው ተናግሯል።

‎በመድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ የትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የዞኑ አካላት ፣ ርዕሰ መምህራኖች ፣ መምህራኖች እና የጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አካላት ተሳትፏል።

‎@ ዘገባው የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

የሚዲያ አጠቃቀም እውቀትና ክህሎትን በማሳደግ መረጃን በኃላፊነትና በሥነ-ምግባር መጠቀም ይገባል፦የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ‎‎( #ገደብ ፣ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም) የጌ...
29/08/2026

የሚዲያ አጠቃቀም እውቀትና ክህሎትን በማሳደግ መረጃን በኃላፊነትና በሥነ-ምግባር መጠቀም ይገባል፦የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

‎( #ገደብ ፣ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም) የጌዴኦ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኮቾሬ ወረዳና ለጨለለቅቱ ከተማ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ስለ መንግስት ኮሙኒኬሽን ተግባርና የሚዲያ አጠቃቀም በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

‎የጌዴኦ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ወይዘሮ ዜና ማሞ፦ የስልጠናው ዓላማ የሚዲያ አጠቃቀም እውቀትና ክህሎትን ማሳደግ፣ መረጃን በኃላፊነትና በሥነ-ምግባር መጠቀም እንዲሁም ትክክለኛና ወቅታዊነቱ የተረጋገጠ መረጃን ለህዝብ በተገቢው መንገድ ቸማድረስ የሚያግዝ መሆኑን ተገልጿል።

‎የሚዲያ መረጃዎችን ከማጋራት በፊት ምንጫቸውንና ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ፣ ህብረተሰቡን ሊያደናግሩ ከሚችሉ ሐሰተኛና አሳሳች መረጃዎች መቆጠብ እና የሚዲያ አጠቃቀምን ከሥነ-ምግባር ጋር ማጣጣም እንደሚገባም ወይዘሮ ዜና ማሞ አሳስበዋል።

‎መንግስት የያዘቻቸውን እቅዶችን ከግቢ ለማደረስ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ተቋማት አስፈላጊ ድጋፍ ሊደረጉ እንደሚገባ ኃላፊዋ አንስተዋል።

‎የኮቾሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን አለሙ በበኩላቸው፣ አመራሩ ለህዝብ ተጠቃሚነት በቀን ከሌት የሚሰራቸውን ተግባራት በሚዲያ በማሳጀብ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በተላበሰ መልኩ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።

‎አመራሩ እንደሀገር የሚተገበሩ ስር ነቀል ለውጦችን ወደ ተጨባጭ ተግባር በመቀየር ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት፣ የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነትን በማጠናከርም የሚታይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ጠቁመዋል።

‎በጌዴኦ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አቶ ደጀኔ ተፈራ የስልጠና ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት፦ ተቋሙ መንግሥትንና ህዝብን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆን በሁለትዮሽ የተግባቦት ሂደት መረጃን በፍጥነትና በአግባቡ ለህዝብ ማድረስ ዋና ተግባሩ መሆኑን ገልፀዋል።

‎አቶ ደጀኔ እንዳሉት፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ተግባራትን ለህዝብ ከማስረዳት ባለፈ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ብዥታን ሊፈጥሩ የሚችሉ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማጥራት ግልፀኝነትን ማስፈን ይገባዋል።

‎በስልጠናው ኮሙኒኬሽን ተቋሚ ሚናና ኃላፊነት፣ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲሁም ሐሰተኛና አሳሳች መረጃን የመለየትና የመከላከል መንገዶች ላይ ግንዛቤ ማግኘታቸውን የስልጠና ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

‎@የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት!

‎በገደብ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል‎‎ #ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ገደብ መንግስት ኮሙኒኬሽን‎‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ...
29/08/2026

‎በገደብ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል

‎ #ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ገደብ መንግስት ኮሙኒኬሽን

‎በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ተግባር በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በወረዳው ሁሎ ባርቲ ቀበሌ ለአንድት አቅም ደካማ እናት የቤት ግንባታ በብሎኬት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎በመርሃ ግብሩ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖሊስና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ሀይሉ ፣የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር በቀሌ እና የወረዳው የወጣቶችና በጎ ፍቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ በየነ እንድሁም የጽ/ቤቱ የማኔጅመንትና ባለድርሻ አካላት ተሳትፏል።

‎በዕለቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከለል ለአንድት እናት የመኖሪያ ቤት በብሎኬት ፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ፣ ለአረጋዊያን የማዕድ ማጋራት እና የአልባሳት ድጋፍ ተከናውኗል።

‎በወረዳው ክረምት በጎ ተግባራት በ18ቱ ዘርፍ የትኩረት መስኮች ውጤታማነት ለማሳደግና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትን ከፍ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

‎"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል ቃል የተጀመረው የኢንሼቲቭ ሥራዎችን ለማሳካት ከሁሉም የሚጠበቅበት መሆኑን ተጠቁሟል።

‎@የገደብ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልገሎት!

Yannatike jeeja'n Aadatixxi geedhe gadabexxe songo'n faaci'e assat xeeni gane citabaak nage'i kado'a aadatixxi kadha ass...
29/08/2026

Yannatike jeeja'n Aadatixxi geedhe gadabexxe songo'n faaci'e assat xeeni gane citabaak nage'i kado'a aadatixxi kadha assende'en.

( 23/2018 G.W) Ga/Ro/Mo/Koomunikeshiinen.

Gede'inxe Zoone'n gadabexxe songo'n aadatixxi geedhe yannate'ni hedheeke jeejuwwa'n faaci'e assat xeeni ganeexxi nage'i bira sa'aasha fixeensik fullexxi mageno kadhante'en.

Faaci'e qabbe'na qeexxali giwwisoole magenikinna kadha laqeexxi baggexxe butta'a xeena uwwaan. Huurotanna hanto fuggoxxa madde abidaan.

Gadabexxe songoke hayyichcha Aaddi Kifile Jabokixxe akeettenni aadatixxi geedhe, Gadabeke rogixxinna qachchiinxe galchaxxi kaabinuwwanna sooreyyuwwa gonfi-butata qorri harca'ebaaki songote'n fullexxi faaci'e me'inseexxi xeeni ganaasha mageno kadhante'en.

Tenne yanna'n dadende kadate'n hexxeexxe diidallotixxe rakko'a hissichchi faaci'etenna mageno kadhaten hiyyeek hayyichchi Aaddi Kifile Jaboki assendeexxe faaci'e'n dhugaa magenoke uwwati dhugaatik anni buttate xeena uwwaasha mageno kadhante'en.

Odo Ga/Ro/Mo/Koomunikeshiinexxen.

Address

Gedeb

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gedeb Woreda Government Communication Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share