02/09/2026
በጊምቦ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በ2018 ዓ.ም ወረዳው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን ስያከናውን በቆየባቸው መንገዶች ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መለየት እንዲሁም የአመራሩ ቁመና ጠንካራ እንዲሆን የሚረዳ መድረክ ነው ሲሉ የካፋ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ ተናግረዋል::
የግምገማውና የምዘናው ዓላማ አመራሩ በተሰማራበት መስክ ቁርጠኛ ሆኖ ሁለንተናዊ ልማቶችን ውጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል::
በተመሳሳይ መልኩ በፓርቲ መሪነት በየወቅቱ የሚወርዱ የኢኒሼቲቭ ስራዎችን እና ሌሎች የልማት ስራዎች ውጤታማ ማድረግ የሚችል ጠንካራ አመራር በመፍጠር የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ እውን ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ታከለ ታምሩ ተናግረዋል::
ግምገማውና ምዘናው በወረዳው እየተሰሩ ያሉ ጠንካራ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም ጉድለቶችን ለማረም የምረዳ ከመሆኑ ባሻገር በአስተሳሰብና በተግባር አንድነት የተገነባ ጠንካራ አመራር መፍጠር ላይ ተግባር የመፈጸም አቅም፣የስነምግባርና ሌሎች ጉዳዮችን በማጥራት ውጤታማ እንዲሆኑም ይረዳል ብለዋል::
ምስል:-በአቤል ተስፋዬ
የጊምቦ ወረዳ መን/ኮሚ/ጉዳ/ጽ/ቤት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/gimbogovtcommunicationaffairs
የቲክቶክ ቻናላችን
https://tiktok.com/
ይቀላቀሉ::