Gofa Zone Revenue Department

Gofa Zone Revenue Department ይህ የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ፌስቡክ ገፅ ነው ስለ ግብር እና ታክስ ጉዳዮች ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ እንድደርስዎ ገፁን ላይክ እና ለወዳጅ ጎደኛ ያጋራ ❗️❗️

30/07/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች  በአርባ ምንጭ 'ገበታ ለትውልድ' ኮንፈረንስ ሪዞርት እና አዞ ራንችኝ ጎበኙየቢሮው ማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች በ2019  በጀ...
29/07/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በአርባ ምንጭ 'ገበታ ለትውልድ' ኮንፈረንስ ሪዞርት እና አዞ ራንችኝ ጎበኙ

የቢሮው ማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች በ2019 በጀት ዓመት የታቀደውን የ48.2 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳት በሠራተኞች መካከል የትብብርና የአንድነት የሥራ መንፈስ ለመፍጠር ታቅዶ በገበታ ለትውልድ አርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ፕሮጀክት እና የአዞ ራንች የተደረገ ጉብኝት ነው።

ሠራተኞች የ'ገበታ ለትውልድ' እና አዞ ራንችን በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን፣ ይህም በ2019 የተያዘውን የ48.2 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የጋራ መንፈስን የሚያድስና ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

ቢሮው በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ያቀደውን 32.4 ቢሊዮን ብር ገቢ መቶ በመቶ አሳክቶ በማጠናቀቅ በተያዘው 2019 በጀት ዓመት 48.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል።

የጉብኝት መርሃ-ግብሩ ይህንን ትልቅ ግብ ከዳር ለማድረስ አመራሩና ባለሙያው በአዲስ የሥራ መንፈስ እና በከፍተኛ ተነሳሽነት ወደ ስራ እንዲገባ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ በዝግጅቱ ላይ ተጠቁሟል።

በዝግጅቱ ላይ የቢሮው አመራሮችና ባለሙያዎች ለ2019 አዲሱ በጀት ዓመት ለመሰብሰብ የታቀደውን 48.2 ቢሊዮን ብር ገቢ ክልሉ ካለው እምቅ ጸጋ አንጻር የታክስ ከፋዩን ግንዛቤ በማስፋት በፈቃደኝነት ግብር መክፈል የሚችል ግብር ከፋይ መፍጠር ዕቅዱን እንደሚያሳኩ ቃል ገብተዋል።

"በ2018 በገቢ ዘርፍ የመተዘገበውን ስኬት በማላቅ፤ ወጪን በራስ አቅም ከመሸፈን ባለፈ የውስጥ አቅምን በማጎልበት ለህዝብ አዳጊ የልማት ጥያቄዎች ብቃት ያለው ምላሽ ለመስጠት በ2019 የበጀ...
28/07/2026

"በ2018 በገቢ ዘርፍ የመተዘገበውን ስኬት በማላቅ፤ ወጪን በራስ አቅም ከመሸፈን ባለፈ የውስጥ አቅምን በማጎልበት ለህዝብ አዳጊ የልማት ጥያቄዎች ብቃት ያለው ምላሽ ለመስጠት በ2019 የበጀት ዓመትም ለገቢ አሰባሰብ ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል።

ለዚህም ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሃዊ ገቢን በአግባቡ ከመሰብሰብ ባሻገር በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ተጠቅሞ ተጨማሪ ሀብት በማፍራትና የገቢ አማራጮችን በማስፋት፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመደጋገፍ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የልማት ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም በማጠናቀቅ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መስራት ቀዳሚ ተግባር ይሆናል።"

ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በ2019 በጀት ዓመት ገቢን ከዕቅድ በላይ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ...
27/07/2026

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በ2019 በጀት ዓመት ገቢን ከዕቅድ በላይ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡-

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የተመለከተ ሴክቶራል ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በብቃትና በጥራት በመመለስ ጠንካራ ሀገር፤ ክልል እና የበለፀገ ኅብረተሰብ መፍጠር የሚቻለው፤ የገቢ አማራጮችን በማስፋት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በተቀናጀ አግባብ አሟጦ በመሰበሰብ ብቻ መሆኑን ተናግረው ለተያዘው ግብ ስኬት ከወዲሁ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለገቢ ስራዎች ማነቆ ተብለው በርዕሰ መስተዳድሩ ከተዘረዘሩ መካከል፡- የህብረተሰቡ የገቢ የግንዛቤ ውስንነት ፣ ያልተመዘገቡ የኢኮኖሚ ማዕቀፎች ፣ ዝቅተኛ የታክስ መሰረት የወጣውን ያለመበግበር፣ ታክስ ማጭበርበር እና ማሸሽ ፣ የታክስ አስተዳደር አቅም ውስንነት፣ የታክስ ህጎችን የማስፈፀም አቅም ማነስ ፣ የህገወጥ አሰራር እና የተጠያቂነት ድክመት፣ ህገወጥ ንግድ ዝውውርና ኮንትሮባንድ እነዚህን ለማረም የሚያስችሉ የአሰራር ስረአትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ አፅኖት ሰጥተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻ ከላይ የተጠቀሱ ማነቆዎችን በመፍታት በ2019 ገቢን ከዕቅድ በላይ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል እነዚህም፡-

ጠንካራ የአመራር ስረዓት መገንባት፡- አመራሩ በገቢ ዙሪያ በአመላካከት የተሰተካከለ፤ ትጋት፣ ብቃት፣ ፅናትና እውቀት ኖሮት መፈፀም እንዲችል ማብቃት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ጠንካራ ተቋም በሰው ሀይልና በቁሳቁስ በማሟላት ማደራጀት፣ መረጃን ማዘመንና ማደራጀት፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

የህግ በላይነት ማስከበር የወጡ ደንቦች እና መመሪዎች ተግባራዊ ማድረግ፤ በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ በአፅኖት ገልፀዋል፡፡

የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና የግንኙነት አግባብት በማሻሻል ግብር መክፍል የሁሉም ዜጎች የውዴታ ግዴታ መሆኑንን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር መስራት እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል።

በዚህ ረገድ የብዙኀኑን ልፋት የሚያበላሹና በገቢ አሰባሰብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጥቂት ሕገወጦች መኖራቸውን አስረድተው፣ በእነኚህ ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚደረገውን ጥረት የፍትሕ አካላት ሊደግፉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በአጠቃላይ የገቢ አጀንዳ የሁሉም አጀንዳ በማድረግ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ መስራት ይገባል በማለት መድረኩን አጠቃለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢ ስራዎች  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮች እና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠበ2018 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ 32 ቢሊዮን 354 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ በ...
27/07/2026

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮች እና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ

በ2018 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ ከ 32 ቢሊዮን 354 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የዘመኑን ዕቀድ ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉ፤ በክልሉ በገቢው ዘርፍ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የማሻሻያ ስራዎች ውጤታማነት የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ለቀጣይ የዘርፉ የተሻለ አፈጸጸም አቅም የሚፈጥር መሆኑ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለትም በ2018 በጀት ዓመት በገቢ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መዋቅሮች ፣ ባለሙያዎች ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ እጅ እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል እነዚህም፡-

ከዞኖች፡- አንደኛ ጋሞ ዞን እና የአሪ ዞን፣ ሁለተኛ የደቡብ ኦሞ ዞን እና የወላይታ ዞን እንዲሁም ሶስተኛ የኮንሶ ዞንና የጌዴኦ ዞን በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል።

ከ3 ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች፡- ዲላ አንደኛ በመሆኑ ተሸላሚ ሆኗል።

"በ2019 በጀት ዓመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ  የህዝብን የልማት ጥያቄ በብቃት ለመመለስ የሚያስችል ስራ ይሰራል  "  - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን...
27/07/2026

"በ2019 በጀት ዓመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የህዝብን የልማት ጥያቄ በብቃት ለመመለስ የሚያስችል ስራ ይሰራል " - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የተመለከተ ሴክቶራል ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ፡-በክልሉ 2018 የበጀት ዓመት በብዙ መልኩ የስኬት ዓመት እንደነበር ጠቅሰው፤ በክልሉ ህዝብ ባለቤትነት በሁሉም የልማት አውታሮች በተከናወኑ በርካታ ስራዎች፤ ክልሉን የሰላም፤ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ውጤታማ ጉዞን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ አመርቂ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ከምርጫ ማግስት በሙሉ አቅም ወደ ስራ የገባንበት የ2019 የበጀት ዓመት በተመሳሳይ፤ በሁሉም ዘርፍ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ለህዝባችን ዳግም ቃልን በተግባር የምናረጋግጥበት ሊሆን ይገባል ሲሉም አክለዋል፡፡

በዚህ ረገድ የውስጥ አቅምንና ፀጋን በአግባቡ በመለየት እና ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ የህዝብ የልማት ጥያቄዎችንና አዳጊ ፍላጎቶች በብቃት መመለስ መሠረታዊ ብቻ ሳይሆን ከአንድ ጠንካራ መንግስት የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ክልላዊ የሰላምና የብልጽግና ራዕይን በተሟላ መልኩ ማሳካት የሚቻለው የውስጥ ገቢ አቅምን ማሳደግ እና የክልሉን የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት ሲቻል ብቻ መሆኑንም አያይዘው ተናግረዋል፡፡

ለዚህም የክልሉ መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉን ህዝብ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር፤ ለክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም፤ የዘላቂ ልማትና የሁለንተናዊ ብልጽግና ትልም ስኬት ለገቢ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ባለፉት ዓመታት ለገቢው ዘርፍ ውጤታማነት የተለያዩ ሪፎርሞችን በማድረግ፤ የህግ ማዕቀፎችን አዘጋጅቶ በመተግበር እና የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ለማዘመን በተደረጉ ጥረቶች በክልሉ የዉስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት በከፍተኛ ደረጀ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 32.4 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለተመዘገበው ስኬት የተጉ የገቢው ዘርፍ አመራሮች፤ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት መሰብሰብ የተቻለው ገቢ ከ2017 በጀት ዓመት ሲነፃፀር የ13.1 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱ፤ ፍትሃዊ ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ በጠንካራ ተቋማዊ ማዕቀፍ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ከተቻለ በክልሉ ገና ያልተነካ ገቢ የማመንጨት አቅም መኖሩን በተጨባጭ የሚያሳይ መሆኑንም አስምረዋል።

ያለፈው ዓመት ስኬት በቀጣይ ሴክተሩን በተለየ በመደገፍና ያልሰበሰብናቸው የገቢ አቅሞች ላይ በማተኮር ባለን ፀጋ እና አቅም ልክ ቢሰራ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚቻል ያመላከተ በመሆኑ በ2019 በጀት አመት 48.2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እቅድ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

በርካታ መዋቅሮች ተግተው በመስራት ፍታሃዊ ገቢን ከእቅድ በላይ በመሰብሰብ ያሳኩ መዋቅሮችም መኖራቸውን ያህል ከእቅድ በታች በመሰብሰብ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው መዋቅሮች መኖራቸውን ገልፀው በጉባኤው የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በብቃትና በጥራት በመመለስ ጠንካ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከ32.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀሐምሌ 20/2018 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓ...
27/07/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከ32.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ያቀደውን የገቢ መጠን መቶ በመቶ በማሳካት ከ32.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምነሽ ደመቀ ገለጹ።

ኃላፊዋ በ2018 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ክልላዊ ጉባዔን አስመልክቶ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ክልሉ በአዲስ መልክ ከተደራጀበት ከ2016 በጀት ዓመት ጀምሮ የክልሉን ወጪ 57 በመቶ ለመሸፈን በሚል 19 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ ከተገባበት ጊዜ አንስቶ፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት በየዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል።

በ2018 በጀት ዓመት 32.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በተደረገው ርብርብ ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉን ወ/ሮ ዓለምነሽ ገልጸዋል ።

በክልሉ ለተመዘገቡ ስኬቶች የህግና የአሰራር ስርዓቶች መሻሻላቸውና ተግባራዊ መደረጋቸው፣የሰው ኃይል ምርታማነትን ማደግ ፣ ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ የሰው ኃይል ማደራጀት ተቋማዊ ሪፎርም እና የገቢ አሰባሰቡን ከሰው ንክኪ ነፃ በማድረግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መስፋፋት አስተዋጻኦ ማበርከታችውን ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት የክልሉን ወጪ 75 በመቶ በራስ አቅም በገቢ ለመሸፈን ትልቅ ግብ መጣሉን የገለጹት ኃላፊዋ ፤ ይህንንም ለህዝብ የገባነውን ቃል በተገቢው ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ሀብት የመፍጠር ተግባር ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር፣ የባለድርሻ አካላትና የገቢ ተቋማት በጋራና በቅንጅት እንዲሰሩ ወ/ሮ ዓለምነሽ ደመቀ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል

27/07/2026
የክልሉ መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉን ህዝብ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።''- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ...
27/07/2026

የክልሉ መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉን ህዝብ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።''
- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የተመለከተ ሴክቶራል ጉባኤ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ከሰሰ መስተዳድሩ በመክፈቻ ንግግራቸው
የክልሉ መንግስት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉን ህዝብ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ይገባል ተብለዋል።

በዞን አስተዳዳሪዎችና በሪጅዮፖሊስ ከተማ ከንቲባዎች ለገቢ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንዳለባቸው አቶ አሳስበዋል፡፡

በክልሉ 2018 የበጀት ዓመት በብዙ መልኩ የስኬት ዓመት እንደነበር ጠቅሰው፤ በክልሉ ህዝብ ባለቤትነት በሁሉም የልማት አውታሮች በተከናወኑ በርካታ ስራዎች፤ ክልሉን የሰላም፤ የመቻቻልና የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ውጤታማ ጉዞን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ አመርቂ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ክልላዊ የሰላምና የብልጽግና ራዕይን በተሟላ መልኩ ማሳካት የሚቻለው የውስጥ ገቢ አቅምን ማሳደግ እና የክልሉን የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት ሲቻል ብቻ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ያለፈው ዓመት ስኬት በቀጣይ ሴክተሩን በተለየ በመደገፍና ያልሰበሰብናቸው የገቢ አቅሞች ላይ በማተኮር ባለን ፀጋ እና አቅም ልክ ቢሰራ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ እንደሚቻል ያመላከተ በመሆኑ በ2019 በጀት ዓመት 48.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እቅድ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በብቃትና በጥራት በመመለስ ጠንካራ ሀገር፤ ክልል እና የበለፀገ ህብረተሰብ መፍጠር የሚቻለው፤ የገቢ አማራጮችን በማስፋት ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በተቀናጀ አግባብ አሟጦ በመሰበሰብ ብቻ መሆኑን አስምረው፤ ለተያዘው ግብ ስኬት ከወዲሁ ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የገቢ ጉዳይ ለአንድ ሴክተር ብቻ ተለይቶ የሚሰጥ ተግባር አለመሆኑንም ጠቅሰው፤ አመራሩ፣ ባለሙያው፤ ማህበራዊ ተቋማት እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለግብር ዘመኑ የገቢ አሰባሰብ ሥራ ስኬታማነት በጋራ የተቀናጀ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ፍትሃዊና ተአማኒ ገቢን ሰብስቦ በአግባቡ ልማት ላይ ማዋል ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ በተያዘው ዓመትም 75 በመቶ ወጪን በዉስጥ ገቢ የመሸፈን ዕቅድ ተጠናክሮ የሚሰራበት መሆኑን አረጋግጠዋል።

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በክልሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ደግፌ እየቀረበ ይገኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የምክክር ጉባዔ በመካሄድ ጀመረበመድረኩ የክልሉ ርዕሰ  መስተዳድር  ጥላሁን ከበደ...
27/07/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የምክክር ጉባዔ በመካሄድ ጀመረ

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ፣የክልል አመራሮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች ፣ የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የገቢ መዋቅር የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

Address

Gofa
Gofa

Telephone

+251903283881

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gofa Zone Revenue Department:

Shortcuts

Share