Geze Gofa Woreda Education Office

Geze Gofa Woreda Education Office Education

 ✍️በዕጩ መምህርነት መንግስት አወዳድሮ ለማስተማር ይፈልጋል።የምዝገባ ቀን ከህዳር 1-5 ነው።
04/11/2025

✍️
በዕጩ መምህርነት መንግስት አወዳድሮ ለማስተማር ይፈልጋል።
የምዝገባ ቀን ከህዳር 1-5 ነው።

ዛሬ በቀን 07/02/2018 ዓ/ም በገዜ ጎፋ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከ17ቱ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ጋር የ2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ውይይት ...
17/10/2025

ዛሬ በቀን 07/02/2018 ዓ/ም በገዜ ጎፋ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከ17ቱ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ጋር የ2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱ የትምህርት አመራሩ በቀረበው ግብረ መልስ በጥንካሬ እና በድክመት የቀረቡ ተግባራት ላይ በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በተቀመጠው ጊዜ ለመሥራት ከመግባባት ደርሰናል።

16/10/2025
ትምህርት ሚኒስቴር የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብን አሳወቀ*******ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ እና በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ከ49.5 በመቶ በታች አስመዝ...
07/10/2025

ትምህርት ሚኒስቴር የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብን አሳወቀ
*******

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ እና በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ከ49.5 በመቶ በታች አስመዝግበው፤ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አሳውቋል። በዚህም መሰረት᎓-

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግሥት ተቋማት) የሪሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33 ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግሥት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግሥት ተሸፍኖ) የሪሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ ብሏል ሚኒስቴሩ።

የመቁረጫ ነጥብ፦

🔥የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216
🔥የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204
🔥ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች
ለሁለቱም ጾታ 198
🔥የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198
🔥ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

 ! #የአማሮና የጃውላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች:- ተማሪ ደግነት  ዮሐንስ  #381 ተማሪ ሰለሞን አለማየሁ  #338 እንዲሁም ተማሪ ምስጋናው ፈለቀ  #303 ውጤት ከማህበራዊ ...
15/09/2025

!

#የአማሮና የጃውላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች:-
ተማሪ ደግነት ዮሐንስ #381 ተማሪ ሰለሞን አለማየሁ #338 እንዲሁም ተማሪ ምስጋናው ፈለቀ #303 ውጤት ከማህበራዊ ሳይንስ በ2017 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ያስመዘገቡ ስሆን በፎቶ ግራፍ የምትመለከቱ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ናቸው። በመሆኑም ለተማሪዎቹ ለወላጆች ፣ላስተማሩ መምህራንና ለህብረተሰቡ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!!

በዞናችን የመማር ማስተማር ሥራ የፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል ፦ አቶ ሞገስ መኩሪያ ላሃ ፣ መስከረም 4/2018ዓ.ም በጎፋ ዞን የመማር ማስተማር ሥራ የፊታችን ሰኞ ...
14/09/2025

በዞናችን የመማር ማስተማር ሥራ የፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል ፦ አቶ ሞገስ መኩሪያ

ላሃ ፣ መስከረም 4/2018ዓ.ም

በጎፋ ዞን የመማር ማስተማር ሥራ የፊታችን ሰኞ መስከረም 5/2018 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞገስ መኩሪያ አስታውቀዋል።

በዚህም የዞኑ ትምህርት መምሪያው ኃላፊ እንደገለጹት ‎የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ ከጅምሩ በአግባቡ ትምህርት መጀመር እንዲሁም የትምህርት ይዘትን ተከታትሎ ማጠናቀቅ ለትምህርት ውጤታማነት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

‎የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ የመጀመሪያ ቀን ትምህርት መስከረም 5 ዕለተ ሰኞ በዞኑ ስር በሚገኙ በሁሉም በመንግሥት እና ግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀምርም ገልጸዋል።

‎በትምህርት ውጤታማ ለመሆን ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ የትምህርት ብክነትን መከላከል፣ አጠቃላይ የትምህርት ይዘት በአግባቡ ተከታትሎ ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

‎መስከረም 5 ዕለተ ሰኞ የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት የሚጀምሩበት በመሆኑ የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ እንደሚገባቸውና አጠቃላይ የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት እንዲገኙ በአጽንኦት አሳስበዋል።

‎የትምህርት ብክነት ከአንድ ክፍለ ጊዜ የሚጀምር በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል የትምህርት ብክነት እንዳይኖር የበኩላቸውን እንዲወጡ የመምሪያው ኃላፊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በትምህርት ዘርፉ ላይ የተመዘገቡ ለውጦችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራውን መስከረም 05/2018 ዓ.ም በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አመራሮችና የትምህርት ባለሙያዎች በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ ተገኝተው የሚያስጀምሩ ይሆናል።

#ጎፋ ዞን ኮሙኒኬሽን

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች አለፉአዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከተፈተኑት 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ...
14/09/2025

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች አለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከተፈተኑት 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)።

የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዳሉት፤ ዘንድሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑት መካከል 8 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት አልፈዋል።

በዚህም በአጠቃላይ ዘንድሮ 48 ሺህ 929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ጠቁመዋል።

ባለፈው ዓመት አማካይ ውጤት 29 ነጥብ 7 እንደነበር አስታውሰው÷ ዘንድሮ 31 ነጥብ 67 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል ነው ያሉት።

በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 11 ነጥብ 4 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 5 ነጥብ 2 በመቶ በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ነጥብ 4 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት ማለፋቸውንም አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ሀረሪ እና አማራ ክልል በአማካኝ ከፍተኛ ተማሪዎች ያሳለፉ ሆነው መመዝገባቸውን አመልክተዋል።

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ከ600፤ 591 ሆኖ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ ከ600፤ 562 ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።

እንዲሁም 2 ሺህ 384 ተማሪዎች ከ500 በላይ ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከፈተና ጋር በተያያዘ በመስረቅ እና በኩረጃ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ተማሪዎች ፈተና ባለመውሰዳቸው ማን በትክክል ለዩኒቨርሲቲ ብቁ መሆኑን መለየት አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሰው÷ በዚህ ዓመት ግን 120 ተማሪዎች ብቻ በዚህ መልኩ መያዛቸውን አውስተዋል።

ሁሉም ት/ቤቶች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ማስተማር ይጀምራሉአዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከመጪው መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ...
12/09/2025

ሁሉም ት/ቤቶች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ማስተማር ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከመጪው መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የዘንድሮው ዓመት የመማር ማስተማር ሥራ ይጀመራል።

ለ2018 የትምህርት ዘመን በየደረጃው ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ ቁሳቁስን ጨምሮ የተለያዩ የዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትና ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራንና የዘርፉ ባለድርሻዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡ የሚታወስ ነው።

ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ተማሪ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌትና የትኛውንም የትምህርት ሥራ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድርና አዋኪ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ይዞ መገኘት ተከልክሏል፡፡

ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ምዝገባ እና ተጓዳኝ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ከ7 ሚሊየን በላይ ሕጻናት በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው፡፡

ወላጆች ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ልጅን ወደ ት/ቤት አለመላክ እንደሚያስጠይቅ አውቀው የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እንዲወጡ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Address

Gofa
Gofa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Geze Gofa Woreda Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Geze Gofa Woreda Education Office:

Share