Ethiopian Health Insurance Servic Gondar Branch

Ethiopian Health Insurance Servic Gondar Branch Serving over 4.5m Beneficiaries.

Established to ensure the Implementation of both SHI and CBHI (Social & Community Based Health Insurance) Service, operates in all the 59 CBHI woredas of Gondar (7 zones, including Gondar and Debre Tabor Metro Towns).

25/11/2025
13/11/2025
13/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

06/10/2025
05/10/2025

‹‹ላይጠግን አይሰብርም›› እንዲሉ፣የገንዘብም ሆነ የሚረዳኝ ቤተሰብ አለመኖሬን አይቶ: ጤና መድኅንን አመጣልኝ።
25/01/2018 ኢጤመአ
አቶ ገዳሙ አበበ የ35 ዓመት ጎልማሳና የሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ትዳርም ሆነ ልጅ ስለሌላቸው ወደ ህክምና ተቋማት የሚሄዱት ብቻቸውን ነው። የህመምን ሸክም ብቻውን መሸከም ለሚገደድ ሰው፣ የገንዘብ ችግር ሲጨመርበት ኑሮ እጅግ ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ይሁንና፣ አቶ ገዳሙ ይህን ከባድ ፈተና ለመቋቋም ትልቅ ድጋፍ አግኝተዋል፤ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት።
አቶ ገዳሙ፣ አገልግሎቱ በሰንዳፋ ከተማ ሲጀመር አባል ሆነው መጠቀም ጀምረዋል። በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት አማካኝነት፣ ለህክምና ወደ ሰንዳፋ ጤና ጣቢያ የመጡበትን አጋጣሚ ተጠቅመን፣ የጤና መድህኑ በግል ሕይወታቸው ያመጣውን ፋይዳ እንዲገልጹልን ጠይቀናቸው።
አቶ ገዳሙ በግልጽ ለመናገር በሚከብድ ከባድ ህመም ምክንያትና በሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች በተደጋጋሚ እንደሚያማቸው እና ከጤና ጣቢያ እስከ ሆስፒታል ድረስ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን ነገሩን። በተለይ ደግሞ ዛሬ አዲስ ህመም እንዳለባቸው ስለተነገራቸው፣ የማይቋረጥ መድሃኒት እየወሰዱ ይገኛሉ። "ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በቅብብሎሽ እየሄድኩ እዚያም እየታከምኩ ነው፤ እዚህ መድሃኒት ለመውሰድ የመጣሁት የመድሀኒት ወጪዬን የጤና መድህን ስለሚሸፍንልኝ ነው፡፡" ይላሉ።
አቶ ገዳሙ የጤና መድህኑ ለእሳቸው ያለውን ጠቀሜታ "በተለይም ለኔ አይነቱ ገንዘብም ሆነ የሚረዳው ቤተሰብ ለሌለው ሰው የጤና መድህን ጠቀሜታ ለመግለጽ ይከብዳል" በማለት የልባቸውን የሞላውን፣ ገበና ጎጇቸውን የሸፈነውን የጤና መድህን ስርዓት ያመሰግናሉ፡፡
በጤና ጣቢያው መድሃኒት በማይኖርበት ጊዜ ከግል ፋርማሲዎች መድሃኒት የመግዛት አጋጣሚ ሲፈጠር፣ ሁሉንም ህክምና በቀጥታ ከኪስ ቢከፍል፣ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው የማይችለው መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡
አቶ ገዳሙ በየሁለት ወይም በሶስት ወራት ምርመራ ያደርጋሉ፤ ሁለት ዓይነት መድሃኒት ይወስዳሉ። ይህ ሁሉ የህክምና ወጪ የሚሸፈነው ያለምንም የቀጥታ የኪስ ክፍያ በጤና መድህን ነው፡፡ የጤና መድህኑ በአስቸጋሪ የጤና ጊዜያት የገንዘብ ሸክሙን በማቅለል፣ በህክምናው ላይ እንዲያተኩሩ አስችሏቸዋል።
የአቶ ገዳሙ አበበ ተሞክሮ እንደሚያሳየው፣ የጤና መድህን በተለይ ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ከህክምና ወጪ በላይ የህይወት ዋስትና ነው።
Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buuu1l

25/08/2025

የጤና መድኅን የቤተሰቦቼ ዋስትና ነው
18/12/2017ዓ.ም ኢጤመአ
አቶ ተማም ሸህሞክሼ የ40 ዓመት ጎልማሳ፣ የ6 ቤተሰብ አስተዳዳሪና በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ናቸው ፡፡ ነዋሪነታቸውም በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ሀላባ ዞን ወይራ ወረዳ ሙዳዲኖቆሳ ቀበሌ ነው ፡፡ ልጃቸውን ወጣት ፎዝያ ተማምን ስላመማት በአካባቢያቸው ባለው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ሙዳ ጤና ጣቢያ ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን ፎዝያ ከህመሟ ስላልተሸላት ወደ ሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በሪፈር መጥታ እየታከመች ነው፡፡ ልጃቸውን የሚያሳክሙት አቶ ተማም ስናገኛቸው የጤና መድኅን የቤተሰቦቼ ዋስትና ነው ብለው የገለጹት፡፡
አቶ ተማም የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል ከሆኑበት ጀምሮ እሳቸው፣.ባለበታቸው ወ/ሮ ጉርሸዳ ሃቢብ እና ለጆቻቸው እነ ፈቲያ ተማም በጤና መድኅን እየታገዙ በአካባቢያቸው በሚገኘው ሙዳ ጤና ጣቢያ አገልግሎት ሲያገኙ ቆይተዋል፡፡ ባገኙት የጤና መድኅን ድጋፍ አመስግነው ሳይጨርሱ ልጃቸው ፎዝያ ከሙዳ ጤና ጣቢያ ወደ ሀላባ ቁሊቶ ሪፈር ተደርጋ አገልግሎቱን ስታገኝ በወጪ በከፍተኛ ደረጃ ስለታገዙ ጤና መድኅንን የቤተሰባቸው ዋስትና መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በጤና መድኅን እንደ አቅማቸው አዋጥተው እንደ ህመማቸው በሀገር ውስጥ ባሉት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎቱን እንደሚያገኙ የተረዱት አቶ ተማም በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደረገላቸው አገልግሎት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የወይራ ወረዳ ፣ ሙዳዲኖቆስ ቀበሌ የአየር ጸባዩ ሞቃታማ ነው ያሉት አቶ ተማም በርካታ ሰዎች በተለያዬ ህመም ስለሚጠቁ በጤና መድኅን እየታገዙ ሙዳ ጤና ጣቢያ በሚገባ አገልግሎቱ ያገኛሉ፡፡ እንደሳቸው ልጅ በሽታው ሲበረታ ደግሞ ትልልቅ ሆስፒታሎች በመሔድ እንደህመሙ ደረጃ በአገልግሎቱ ይታገዛሉ፡፡ ሰለዚህ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን አባል ያልሆኑት፣ አባል እንዲሆኑ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በማግኘት ጤና መድኅንን የቤተሰባቸው ዋስትና እንዲያደርጉ አቶ ተማም ይመክራሉ፡፡
በመጨረሻም አቶ ተማም ሸህሞክሼ ጤና መድኅን የቤተሰባቸው ሙሉ ዋስትና እንዲሆን አልፎ አልፎ የላብራቶሪ ምርመራ እና የመድኃኒት አቅርቦት አለመሟላት ይታያል፡፡ስለዚህ በየደረጃው ያለው መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ አካል ትኩረት ተሰጥቶ አቅርቦቱ እንዲስተካከል ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buuu1l

Address

L Shape Street
Gondar

Telephone

+251581119028

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health Insurance Servic Gondar Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Health Insurance Servic Gondar Branch:

Share